@abdoelamraouii48: Nota | #fypシ #explorepage#notadizzydross #musicmaroc #🇲🇦 #dizzydros

Abdo 48⚡
Abdo 48⚡
Open In TikTok:
Region: MA
Sunday 13 August 2023 17:44:54 GMT
32187
900
9
235

Music

Download

Comments

girlgames85
𝒩𝒜ℰℒ𝒜 :
😻😻😻😩😩
2025-04-23 21:56:53
1
user569209917535
F-Tï-H💜 :
❤❤❤❤
2024-05-08 01:53:05
2
urfavloverman
𝐵𝑒𝒷𝑒𝓀 :
😭😭😭
2025-08-21 09:32:59
0
zakariaz119
zakaria . :
😍
2025-06-16 23:25:34
0
tahalahrouz
𝕿𝖆𝖍𝖆 :
@anas.tfa
2025-06-10 18:59:17
0
user470975428809903
elmiry@_@ :
🥰
2025-05-02 03:31:54
0
omaroboxe01
Omar najim :
💙
2025-04-21 22:41:03
0
najwalaz86
najwa :
😁
2025-03-28 17:55:16
0
muuhaameedfk7
muhamed digo :
@* LõCä * 💝👑
2024-05-10 12:36:15
2
To see more videos from user @abdoelamraouii48, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

ልክ የዛሬ ፵፩ ዓመት፣ ደርግ ከአጼ ኃይለሥላሴ መንግሥት ስልጣን የተረከበበትን ፲ኛ የአብዮት በዓልና የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ (ኢሠፓ) ምስረታ በይፋ የታወጀበት ቀን። ለዓል ማክበሪያ በትንሹ አንድ መቶ ሃምሳ ሚሊዮን ብር ወጪ ሆኗል (በአሁኑ ስሌት 30 ቢሊዮን ብር ሊሆን ይችላል)፡፡ በዚያን ጊዜ፣  በ19 ሚሊዮን ብር የኢሠፓ የጉባኤ አዳራሽ፣ የ“ትግላችን” ሀውልት፣ የአዲስ አበባ ከተማ ደማቅ መብራቶች፣ በልዩ ልዩ መፈክሮች፣ እንግዶች በሚንቀሳቀሱባቸው ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ ያሉ አሮጌ ቤቶች በግንብ አጥርና በትላልቅ የጨርቅ ሽፋኖች እንዲከለሉ ተደርገዋል፡፡ የክፍለ ሀገር ዋና ከተሞችና የአውራጃ ከተሞችም በመፈክሮችና በምስሎች አሸብርቀዋል፡፡ በዋና ዋና መንገዶች ላይ ያሉ የንግድ ድርጅቶችና የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በሶስት ቀለማት (አረንጓዴ፤ ቢጫ፤ ቀይ) የተዘጋጁ አምፖሎችን እንዲያበሩ ታዘዋል፡፡ በየቀበሌው የተቋቋሙ የኪነት ቡድኖችም ኢሠፓን የሚያወድሱ መዝሙሮችን አፍልቀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የነጭና ጥቁር ስርጭቱን ትቶ ወደ ሙሉ ቀለም ስርጭት ተሸጋግሯል። ኢሠፓ የተመሠረተው ጳጉሜ 5/1976 ነው፣ አስረኛው የአብዮት በዓል የተከበረው መስከረም 2/1977 ነው።  በዚያ ክብረ በዓል ላይ  - የምስራቅ ጀርመን ኮሚኒስት ፓርቲ ዋና ፀሐፊና የሀገሪቱ መሪ ጓድ ኤሪኽ ሆኔከር፣  - የየመን ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ (ደቡብ የመን) መሪ ጓድ ዓሊ ናስር አል-ሐሰን፣ - የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ኬኔት ካውንዳ፣  - የዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ፣  - የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ሳሞራ ማሼልና የበርካታ የሶሻሊስትና የአፍሪቃ ሀገራት ልዑካን ተገኝተዋል፡፡  የበዓሉ አከባበር - በኢሠፓ ጉባኤ አዳራሽና በአብዮት አደባባይ በልዩ ትርዒትና ወታደራዊ ሰልፍ፣ “ኢሠፓ” የተመሰረተው ለአምስት ዓመታት ሰፊ ዝግጅት ከተደረገ በኋላ በ5ቀናት ጉባኤ ነው፣ ለፓርቲው ምስረታም በ1972 ዓም “የኢትዮጵያ ሰርቶ አደሮች ፓርቲ አደራጅ ኮሚሽን” (ኢሠፓአኮ) ህዝቡን በሶሻሊስታዊ ስርዓት እንዲያደራጅ ተመስርቶ ነበር፣ ኮሚሽኑን ማቋቋሙ ያስፈለገው “ኢሠፓ'ን ለመመስረት የሚቻለው ህዝቡን በማንቃትና በማደራጀት በአንድ ማዕከል ዙሪያ ካሰባሰቡ በኋላ ነው” በሚለው የኮሚኒስቶች ርዕዮተ-ዓለማዊ መርህ መሰረት ነው፡፡ የዚህ ኮሚሽን ተጠሪ በመሆን በየክፍለ ሀገሩ የተመደቡ ወኪሎች የየአካባቢው የበላይ ውሳኔ ሰጪዎች ነበሩ፣ የኮሚሽኑን ዓላማ “የኢሠፓአኮ ተልዕኮ ይሳካል” በሚል መፈክር የተደገፈ ነው።   በጉባኤው ማጠቃለያ በድርጅታዊ አሰራር የተዘጋጀ ምርጫ ተደርጎ ጓድ መንግሥቱ ኃይለማሪያም የፓርቲው ዋና ጸሐፊ ሆነው ከርሳቸው ጋርም 183 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ተመረጡ፡፡  የኢሠፓ አወቃቀርና አሠራር በሌሎች የሶሻሊስት ሀገራት ከታዩት ኮሚኒስት ፓርቲዎች ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ፓርቲው የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት የበላይ ነው፡፡ የፓርቲውና የአስፈጻሚ አካላቱ ግንኙነት የጎንዮሽ ሳይሆን ከላይ ወደታች የተዘረጋ መዋቅራዊ መልክ ነበረው፡፡ በመሆኑም ኢሠፓ በየትኛውም እርከን ላይ ላሉት አስፈጻሚ አካላት የበላይና አመራር ሰጪ ነው፡፡ ይህ አወቃቀር በሀገር አቀፍ፣ በክፍለ ሀገርና በአውራጃ ደረጃ የተዘረጋ ነው፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ የነበሩት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች አመራር የሚቀበሉት ከኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ነው፡፡ በክፍለ ሀገርና በአውራጃ ደረጃ ያሉ መስሪያ ቤቶችም ከኢሠፓ ጽ/ቤት ነው አመራር የሚሰጣቸው፡፡ በመሆኑም የአውራጃና የክፍለ ሀገር የኢሠፓ ኮሚቴ አንደኛ ፀሐፊ ሆኖ የተመደበ ሰው በፕሮቶኮልም ሆነ በስልጣኑ ከሌሎች ተሿሚዎች ሁሉ ይበልጣል፡፡  የኢሠፓ መዋቅር በኢ-መደበኛ ሁኔታ ሁሉንም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች አዳርሷል፡፡ በያንዳንዱ የመንግሥት መስሪያ ቤት፣ በማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅቶችና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ “የኢሠፓ መሰረታዊ ድርጅት ጽ/ቤት” የሚባል መምሪያ ነበረ፡፡ የዚህ መሰረታዊ ድርጅት ዓላማ የኢሠፓን ርዕዮተ ዓለም ማስተማርና ከበላይ አካል የመጡ መመሪያዎች ተፈጻሚ መሆናቸውን መቆጣጠር ነው፡፡ ለፓርቲ አባልነት ብቁ የሆኑ ጓዶችን መልምሎ የአባልነት መታወቂያ የሚሰጠውም እርሱ ነው፣ ከ100,000 ያላነሱ አባላትም አፍርቷል፣ አባላቱ ከሲቪልም ሆነ ከጦር ሀይሉ የተመለመሉ ነበሩ። ኢሠፓ ፕሮፓጋንዳውን በፓርቲው ልሳን በሳምንታዊ “ሠርቶ አደር” እና በ'መስከረም' መጽሔት በኩል ያስተጋባ ነበር። የፓርቲው አባላት በሁለቱ ህትመቶች በወጡ ጽሑፎች ላይ የመወያየት ግዴታ አለባቸው፡፡ ኢሠፓ የደርግ መንግሥት ከስልጣን እስከተወገደበት ጊዜ ድረስ ለ7 ዓመታት ቆይቷል፣ እያንዳንዱ የፓርቲ አባል በመመሪያ “የሀገር ውስጥ ምርቶችን ማበረታታት አለብን” በሚል መነሻ በስራ ቀናት በቃሊቲ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ በሚመረተው ከካኪ የተሰፋ ሱሪና ኮት የመልበስ ግዴታ አለበት። - የፓርቲው ም/ዋና ፀሐፊ በይፋ ባይገለፅም ጓድ ፍቅረሥላሤ ወግደረስ - የርዕዮተ-ዓለም መምሪያ ሃላፊው ጓድ ሽመልስ ማዘንጊያ  - ጓድ ብርሃኑ ባይህ የውጭ ግንኙነት መምሪያ ሃላፊ - ጓድ ሸዋንዳኝ በለጠ የኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ሃላፊ፤  - ጓድ ተካ ቱሉ የኦዲትና ቁጥጥር ኮሚሽን ሃላፊ፣  - ጓድ ደበላ ዲንሳ የማህበራዊ ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ፣  - ጓድ ሜጀር ጄኔራል ገብረየስ ወልደሃና የወታደራዊ ፖለቲካ ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ ነበሩ - ስልጣናቸው ገንኖ የነበረው ግን የድርጅት መምሪያ ሃላፊው ጓድ ለገሠ አስፋው ናቸው። በወቅቱም ኢሠፓ የምስረታ ጉባኤውን በሚያካሄድበት ከጳጉሜ1- 5/1976) ሀገሪቱ በከፍተኛ ድርቅ ከ5 ሚሊዮን የማያንሱ ዜጎች በትግራይ፣ በወሎ፣ በጎንደር፣ በኤርትራ፣ በሀረርጌና በባሌ ክፍላተ ሀገር በቸነፈር ተጠብሰው በሞት አፋፍ ላይ ነበሩ፡፡ አንዳንድ የሀገር ተቆርቋሪዎች መንግሥት የፓርቲ ምስረታ ጉባኤውን ለሌላ ጊዜ እንዲያስተላልፍና የ10ኛ አብዮት በዓልን እንዲያስቀር ቢወተውቱም ሰሚ አላገኙም፡፡ የወቅቱ መንግሥት የድርቁ መኖር ከታወቀ በአብዮት በዓል አከባበሩ ላይ ጥላውን ያጠላል በማለት የምዕራብ ሀገራት የዜና አውታሮች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ከልክሎአቸው ነበር፡፡ ይሁንና አንዳንድ ሚዲያዎች የዜና ዘጋቢዎቻቸውንና የቪዲዮ ሪፖርተሮቻቸውን በድብቅ ወደ ሀገር ውስጥ በማስረግ የዓለም ህዝብ አስከፊውን ድርቅ እንዲያየው አድርገዋል፡፡ በነዚያ ሪፖርተሮች የተቀረጹ ምስሎችን የተመለከቱ የዓለም ህዝቦች ለድርቅ የተጋለጠውን ኢትዮጵያዊ ረሀብተኛ ለመታደግ በስፋት ተንቀሳቅሰዋል (በሰር ቦብ ጊልዶፍ አስተባባሪነት የተሰባሰቡ የዓለማችን እውቅ አርቲስቶች Live Aid የተባለውን የሙዚቃ ዝግጅት ያቀረቡት ያኔ ነው፡፡ አርቲስቶቹ በዝግጅቱ ላይ በጋራ ያዜሙት We are the world የተሰኘው ዜማ ከምንጊዜም ምርጥ ዜማዎች መካከል አንዱ ሆኖ ተመዝግቧል)፡፡   የደርግ መንግሥት በህጋዊ መንገድ ፈቅዶላቸው የመጡ ጥቂት የሶሻሊስት ሀገራት ዘጋቢዎች ደግሞ “ድርቅ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ህዝብ እየቀጠፈ ለዚህ በዓል ከፍተኛ በጀት መመደብ አግባብ ነውን?” የሚል ጥያቄ በይፋ በማቅረብ የሀገሪቱን ከፍተኛ ባለስልጣናት አጨናንቀዋል፡፡ በመሆኑም የአብዮት በዓሉ ሲፈጸም መንግሥት በድርቅ የተጎዳውን ህዝብ ለመታደግ መንቀሳቀሱ ግድ ሆኖበታል፡፡ ሆኖም የመንግሥት እርምጃ በጣም የዘገየ በመሆኑ አንድ ሚሊዮን የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን በዚያ አስከፊ ድርቅና ረሃብ አልቀዋል።

About