@enochenok.eth: ሠላሳ ዓመት ከጌታ ጋር ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እመቤታችን ጌታን ጸንሳ ከወለደችው በኋላ እስከ ሠላሳ ዓመቱ ድረስ እንደ ልጅነቱ እያገለገላት ፣ እንደ አምላክነቱ እያገለገለችው አብራው በአንድ ቤት ውስጥ ኖራለች፡፡ ሌላውን እንተወውና ይኼ ነገር ብቻ ለማሰብ ያስጨንቃል! ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ አንድ ቤት ውስጥ መኖር እንዴት ያለ ነገር ነው? ልብ በሉ ድንግል ማርያም ጠዋት ከእንቅልፍዋ ስትነቃ "እንዴት አደርህ?" የምትለው ፈጣሪዋን ነበር:: ማታ ስትተኛ "ደህና እደሪ" የሚላትም አምላክዋ ነበር:: የማይተኛው ትጉሕ እረኛ በተኛች ጊዜ ሕፃን ሆኖ ከአጠገብዋ ያደረ ከእመቤታችን በቀር ማን አለ? ኪሩቤልና ሱራፌል ቅዱስ ቅዱስ የሚሉትን አምላክ እንደ እናት "እሹሩሩ" ብላ ያስተኛች እርስዋ ነበረች:: ምድርን  በአበባ ልብስ የሚያስጌጠውን ጌታ በተኛበት ያለበሰችውም እርስዋ ነበረች:: ዓለምን በእጆቹ የያዘውን ጌታ ክንዶችዋን ያንተራሰችው እርስዋ ነበረች:: እነዚያን ሌሊቶች ድንግል ማርያም እንዴት አሳልፋ ይሆን? በሕልምም በእውንም ከፈጣሪ ጋር ማሳለፍ እንዴት ያለ ጸጋ ነው? ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ነው፡፡ እመቤታችን ከልጅዋ ጋር ለሠላሳ ዓመታት አብራ በአንድ ቤት ስትኖር የነበራቸው ንግግር ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር እንደመሆኑ ጸሎትም ጭምር ነበር፡፡ የጠዋትና ማታ ጸሎትሽ ከልጅሽ ጋር ማውራት የሆነልሽ : ልጅሽ የሚሠጥሽ መልስ የፈጣሪ መልስ የሆነልሽ እመቤቴ ሆይ ስላንቺ ክብር ማሰብ ምንኛ ያስጨንቃል? እስቲ ረጋ ብላችሁ አስቡት! እመቤታችን እና ጌታችን በእነዚያ ሁሉ ዓመታት ምን ሊነጋገሩ ይችሉ ነበር? ከእርስዋ በቀር ማን ይነግረናል? ድንግል ሆይ አንቺ ካልነገርሽን ማን ይነግረናል? ለማዕድ ስትቀመጡ ምን ብሎ ጸልዮ ይሆን? እንደ ሐዋርያቱ ቆርሶ ሠጥቶሽ ይሆን? ውኃን እንዲጠጣ ሞልተሽ ስትሠጪው ውቅያኖስን እንዴት በውኃ እንደሞላ ነግሮሽ ይሆን? በእርግጥ በእነዚያ ዓመታት ክርስቶስ ለእናቱ ምን ምን ሲነግራትስ ኖሮ ይሆን? ስለየትኛውስ ምሥጢር ሲገልጥላት ነበር? ገና የዐሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ሳለ በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ያነጋገሩት የአይሁድ መምህራን ‹በማስተዋሉና በመልሱ ሲገረሙ ነበር› እመቤታችን ከሕጻንነቱ ጀምሮ እስከ ሠላሳ ዓመቱ ድረስ አብራው ስትኖር በስንቱ ነገር ስትደነቅ ኖራ ይሆን? /ሉቃ. ፪፥፵፯/ እንደ መንፈሳዊት እናት ድንግል ማርያም ለልጅዋ የትኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እየነገረች አሳድጋው ይሆን?  ሙሴ ስላያት ዕፀ ጳጦስ ታሪክ አልነገረችው ይሆን? ታሪኩን ሰምቶ "ያቺ ዕፅ አንቺ ነሽ እሳቱ ደግሞ እኔ ነኝ"ብሏት ይሆን? ውኃ ስለፈለቀበትና እስራኤል ስለጠጡበት ዓለት ነግራው ይሆን? እርሱስ "ያ ዓለት እኮ እኔ ነበርሁ" ብሎአት ይሆን? ብሉይን ስታነብ ሐዲስን እየተረጎመ እንደ ኤማሁስ መንገደኞች ልብዋን አቃጥሎት ይሆን? ሉቃ. ፳፬፥፴፪/ ጠቢበ ጠቢባን ሊቀ ሊቃውንት ኢየሱስ ክርስቶስ በቤትሽ ጉባኤ የዘረጋብሽና ያስተማረሽ ድንግል ሆይ አንቺ እንደሆንሽ በልብሽ ከመጠበቅ ውጪ ብዙ አትናገሪም:: ሆኖም ልጅሽ ምን ምሥጢር ነግሮሽ ይሆን? ኤልሳቤጥ እንኳን ዮሐንስን ጸንሳ ስለጽንሱ የምትለው ብዙ ነገር ነበራት:: ፈጣሪ በአንቺ ዘንድ ያደረ ድንግል ሆይ አንቺስ ምን ትነግሪን ይሆን? "የመለኮት እሳት በሆድሽ ባደረ ጊዜ ልብሱ እሳት ቀሚሱ እሳት ነው:: እንደምን አላቃጠለሽም? የኪሩቤል ዙፋን በሆድሽ ውስጥ ወዴት ተዘረጋ? በግራ ነው ወይንስ በቀኝ? ታናሽ አካል ስትሆኚ ይህ ሁሉ እንዴት ሊሆን ይችላል?" እያልን ከአባ ሕርያቆስ ጋር እንጠይቅሻለን:: እንዳንቺ ፈጣሪውን የሚያውቅ ፍጡር የለምና የዓለም የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት : የነገረ መለኮት ምሁራን : የወንጌሉ ተንታኞች ሁሉ ከአንቺ እግር ወድቀው እንደ አዲስ ስለ ክርስቶስ ሊማሩ ይገባቸዋል:: #ዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ #እመቤቴ_ማርያም_እለምንሻለው #ድንግል_ማርያም_እናቴ #ማርያም #ኦርቶዶክስ⛪ተዋህዶ⛪ለዘለዓለም🙏ትኑር🙏 #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ፀንታ_ለዘለዓለም_ትኑር #ኦርቶዶክስ

✥ ሔEኖOክ ✥
✥ ሔEኖOክ ✥
Open In TikTok:
Region: DE
Saturday 17 February 2024 07:48:40 GMT
174420
45093
1251
6884

Music

Download

Comments

hanaha8632
hanaha :
migrimii new maryamin🥰🥰🥺
2024-02-19 05:43:04
187
selam2434
Selam :
yenakush hulu wede igirish chama yisegdalu ameen emebeetee hoyy
2024-02-28 11:11:20
71
user232997278665
𝑠𝑒𝑛𝑎𝑖𝑡የማርያም የክርስቶስእስርኛ☦️ :
𝑒𝑛𝑎𝑡𝑒 𝑚𝑎𝑟𝑖𝑦𝑎𝑚➋➊❤❤❤❤
2024-02-21 13:48:01
13
user9876551707053
user9876551707053 :
enate
2024-03-19 01:22:38
2
edeay73
ed :
Enate Maryam❤
2024-02-21 14:48:14
6
yosef1891
yosef :
enate maryam
2024-02-18 15:40:52
34
bezalemtamiru
Banchu Best :
enate emebete❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
2024-02-21 12:51:04
17
merrydd21
👸Merry @21 :
😍😍😍😍😍 enate mariyam 😍😍😍
2024-02-17 14:29:42
83
abebaabu3
Abeba :
Enate emebete kdst dngl maryam enatee🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🙏🙏🙏🙏
2024-02-19 09:54:39
38
kakodg123
Kakodg123 :
enate emebete21
2024-02-18 20:09:04
37
titi03980
titi :
yene enat mariyam
2024-02-19 19:35:14
17
teme2114
Tetemke Fisha :
enate maryam 21 🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2024-02-18 21:12:18
20
teka2008gebres
user15376520605974 :
Etsub Dinq enji
2024-02-20 05:33:55
9
teruye6
teruye6 :
Enate
2024-02-19 13:08:51
29
user72725556707951
G best :
amen amen amen amennnnnnnnnnn🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2024-02-19 17:29:42
6
tititigraweyti11
ሓፍቲ ንጉስ♥✓ :
🕊️Emebrhan 🤍🤍🙏
2024-04-16 22:22:25
2
ethiopiaagere2716
ለሁሉም ጊዜ አለው :
Enatachin.dingili maryam tileyalechi🙏🥰🥰😍🥰
2024-02-22 10:49:21
10
flemon44
fi &Fi🕊🌹✍️ :
maryam enate yezlalme bet hwte 🕊🥰🥰🥰🙏🙏🙏
2024-02-19 11:20:53
9
maki121213
mekdi–ab :
😍😍😍😍😍 enate mariyam 😍😍😍
2024-02-19 18:59:36
4
destalove76
Desta የማሪያም ልጅ🇪🇹 🇺🇬 🇨🇦 :
Enate🙏🙏🙏❤️❤️❤️❤️❤️❤️🥰🥰
2024-02-29 18:57:52
3
rutanagetoch
Rutana Getoch :
Enate Maryamye 🥰🥰🥰🥰
2024-05-03 06:57:19
1
mekdis.fikir
Mekdis fikir :
enate misteregnaye
2024-04-02 18:59:14
5
haymanot.teklemed
hyab@@@ teklemedhin :
enate maryam 21🥰🥰🥰🥰🙏
2024-03-23 21:11:07
4
zeneb779
አድራሻየ ከመስቀሉ ስር☦️💒🤌 :
Amen Amen Amen kale hiwote yasmalin 🙏kibere misgana yigba hulme enate 🥰🥰🥰🥰🥰
2024-03-25 09:58:56
3
mimi.esral.salto
mimi esral :
hiiiii
2024-02-19 11:53:27
7
To see more videos from user @enochenok.eth, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About