@jy_780: #اكسبلورexplore بترجعين مدري متى؟😢

شعور
شعور
Open In TikTok:
Region: SA
Thursday 02 May 2024 00:43:11 GMT
2797
59
0
4

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @jy_780, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

✝️ ነቅዕ ንፅሕ ዝውእቱ ዜና ሐዋርያት ንፁሐን  ሐምሌ 5 የቅዱስ ጴጥሮስና የቅዱስ ጳውሎስ የሰማዕትነት መታሰቢያ በዓላቸው ነው።                      ✝️<ቅዱስ ጴጥሮስ>  ጌታችን ለቅዱስ ጴጥሮስ ፍቅሩን አሳይቶ እምነቱን በእርሱ ላይ የበጎቹን ጠባቂ እንዲሆን ከሾመው በኋላ ያሟሟቱንም ነገር በግልጥ እንዲህ ብሎ ነግሮታል። <<እውነት እውነት እልሃለሁ ጎልማሳ በነበርህበት ጊዜ አንተ ወገብህን ታጥቀህ ወደምትወደው ትሔድ ነበር በሸመገልህ ጊዜ ግን እጅህን ታነሳለህ ሌላውም ያስታጥቅሃል ወደማትወደውም ይወስድሀል  >>  ይህ ቃል የምሳሌ ንግግር ነው።  ጎልማሳ የሆነ ሰው ዝናሩን አንስቶ ታጥቆ ቆላም ይወርድ እንደሆነ ደጋም ይወጣ እንደሆነ እንደወደደ ያደርጋል። አንድም ጎልማሳ ጨብጦ ማጥበቅ ሮጦ ማምለጥ ይችላል። ሽማግሌ ግን ዝናሩን አንስቶ ለመታጠቅ እጁ እየተንቀጠቀጠ ጉልበቱ እየተብረከረከ አይችልምና   የሌሎችን ሰዎች እገዛ ይሻል። እንደዚህ ሁሉ ቅዱስ ጴጥሮስ የመንፈስ ቅዱስን ኃይል እስኪለብስ ድረስ ወገብ ልቦናውን በፍርሃት ዝናር ታጥቆ እኔ የናዝሬቱን ኢየሱስን አላውቀውም ብሎ ክዶ ነበር።የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ከለበሰ በኋላ ግን ለመስቀል እጁን ዘርግቶ ስለሰጠ የልቡ ትዕግስትና ብርታቱ ወደማይወደው ወደ ሞት ወስዶታልና በመስቀል ቁልቁል ተሰቅሎ መሞቱን ሲያመለክተው ሌላው ያስታጥቅሃል ብሎ ነገረው።  ጌታችን እኔ ቸር ጠባቂ ነኝ ቸር ጠባቂም ስለበጎቹ ሕይወቱን ይለውጣል ብሎ እደተናገረ ሕይወቱን ስለ በጎቹ ለውጦ በመስቀል ተሰቅሎ ነበርና ቅዱስ ጴጥሮስም በጎቼን ጠብቅ ተብሎ ከተሾመ በኋላ እንደ ቸር ጠባቂ በመስቀል ቁልቁል ሐምሌ አምስት ቀን ተሰቅሎ መሞቱ በመከራው ሁሉ ጌታውን መምሰሉን ያስረዳናል።  የሚሰቀልበት ሰዓት በደረሰ ጊዜ ከግዞት ቤት አውጥተው ሲወስዱት ከጌታዬ ከኢየሱስ ክርስቶስ እኩል እንዳልሆን ራሴን ወደታች ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ ብሎ ለመነ። እኛ ብንሆን ምን ብለን እንለምን ይሆን?  አስከምን ድረስ እንታመን ይሆን?  ፪ጴጥ ምዕ ፩÷፭ <<ትጋትን ሁሉ እያሳያችኹ በእምነታችኹ በጎነትን ጨምሩ>>እንደተባለ ለአገልግሎት በተጋን ቁጥር ልናስተውል ይገባል። በመጨረሻም ቅዱስ ጴጥሮስን እንደ ሮማውያን ሥርዓት አስቀድመው ገርፈው በኋላ ራሱን ወደ ታች እግሩን ወደ ላይ አድርገው ሰቅለው ገደሉት። ከሞተም በኋላ መርቄሎስ የሚባለው ደቀ መዝሙሩ ከመስቀል አውርዶ እንደ ሀገሩ ልማድ ሥጋውን በወተትና በወይን አጥቦ ሽቱ ቀብቶ በነጭ ልብስ ገንዞ ማር በተመላ ሣጥን ውስጥ አግብቶ ዛሬ ባቲካን በሚባለው ስፍራ በክብር ቀበረው።                        ✝️ <ቅዱስ ጳውሎስ>  ቅዱስ ጳውሎስና ኔሮን ቄሣር በማናቸውም ነገር የማይስማሙ አጥፊና ጠፊ ነበሩ። ኔሮን ቄሣር ከሃዲና ጨለማ በቃኝ የማይል ንፉግ ስስታም የሰይጣን ማደሪያ ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ ግን ሃይማኖታዊና ቸር የመንፈስቅዱስ ማደሪያ ነበር። በሮሜ ከተማ ቅዱስ ጳውሎስ ያሳመናቸው ክርስቲያኖች እየበዙ ትምህርታቸውም እየሰፋ መሔዱ በቅዱስ ጳውሎስ ምክንያት መሆኑን ኔሮን ቄሣር ስለተረዳው ይልቁንም ከቤተመንግስቱ ሹሞች ወገን ብዙ ሰዎች በክርስቶስ ስለ አሳመነበት ኔሮን ቄሣር በጣም ተቆጥቶ ነበር። ቅዱስ ጳውሎስን ለፍርድ እንዲያቀርቡት አዘዘ። ቅዱስ ጳውሎስም በኔሮን ቄሣር ፊት በቀረበ ጊዜበቀረበ ጊዜ በቀኝ እጁ ከሰንሰለቱ ጋራ መስቀሉን ይዞ ሳይፈራ የክርስቶስን ነገር መሰከረ። ኔሮን ቄሣርም በቁጣ ቃል ይሞት ዘንድ ፈረደበት።  ለልማዱ ሮማውያን በወንጀለኛ የሞት ፍርድ ሲፈርዱ የተፈረደበት ሰው የውጭ አገር ዜጋ ከሆነ አሰቀድሞ በግርፋትና በሌላም በልዩ ልዩ ሥቃይ ካሠቃዩት በኋላ በመስቀል ወይም በሰይፈ ይገድሉት ነበር። ቅዱስ ጳውሎስ ግን በጠርሴስ ተወላጅነቱ የሮማውያን ዜጋ ስለ ሆነ ሥቃዪ ቀርቶለት ባንድ ቅጣት ብቻ በሰይፍ እንዲሞት ተፈረደበት። ቅዱስ ጳውሎስ ወደ መሞቻው ስፍራ ሲወስዱት በንግግሩና ባስተያየቱ ሁሉ ምንም ፍርሃት አልነበረበትም።ፊቱም በደስታ እያበራ ለገዳዮቹ የኃጢአት ሥርየት ይለምንላቸው ነበር።በመግደያውም ስፍራ ምናልባት በንግግሩና በታምራቱ ሌሎች ሰዎች ወደ ክርስቲያንነት እንዳይመለስ ተብሎ ስለተፈራ ሌሎች አረማውያን በፈቃዳቸው እንዳይሄዱ ተከልክለው ነበር። ቅዱስ ጳውሎስም ዓይኑን ወደ ሰማይ አቅንቶ የእግዘብሔርን ክብር ይመለከት ነበር እንጂ የሚሞትበትን ሰይፉን ወይም ደሙ የሚፈስበትን መሬቱን አይመለከትም ነበር።ይልቁነም የያዕቆብ መሰላል ተዘርግቶ መላእክትና ሰማዕታት ጻድቃንም ሲወጡበትና ሲወርዱበት ይታዩት ነበርና በእነዚያ መካከል ለመሆን ይቸኩል ነበር።  ከዚህም በኋላ ሐምሌ ፭ አንገቱን አመቻችቶ በሰጠ ጊዜ ወታደር ቀርቦ ራሱን ካንገቱ ላይ ቆርጦ ለብቻው ጣለው።ወደጆቹ ክርስቲያኖች ራሱን ከወደቀበት አንስተው ከአንገቱ ጋር አጋጥመው ለመቃብር በተፈቀደው ስፍራ ወስደው ቀበሩት።  በአባቶቻችን በቅዱስ ጴጥሮስና በቅዱስ ጳውሎስ ጸሎት ይማረን! ሐምሌ 5/2016ዓ.ም#ተዋህዶ #ethiopian_tik_tok #habeshatiktok #orthodox #ኦርቶዶክስ

About