@bwbereket3: ንስር አሞራ እስከ 70 ዓመት የሚኖር የእድሜ ባለፀጋ ነው። ነገር ግን 70 ዓመት ሙሉ በደስታ ከመኖሩ በፊት በእድሜው አጋማሽ ማለትም ከ35 – 40 ባለው እድሜው ላይ ከባድ ነገር ይገጥመዋል። የመጀመሪያው ምግቡን ለማደን የሚገለገልበት ጥፍሮቹ ከመጠን በላይ ስለሚያድጉ ምግቡን ከመሬት ላይ ማንሳት ያቅተዋል። ሁለተኛው አጥንትን ሳይቀር የመስበር አቅም ያለው አፉ (መንቁሩ) ስለሚታጠፍና ስለሚጣመም ምግቡን እንደወትሮው መመገብ ይሳነዋል። ሶስተኛው ክንፉና በአካሉ ላይ ያሉ ላባዎቹ ስለሚከብዱት ያ ሰማየ ሰማያትን እየሰነጠቀ ይበር የነበረው ኃይሉ ይከዳዋል። እነዚህ ሶስት ከባድ ነገሮች ንስር አሞራ በእድሜው አጋማሽ የሚያጋጥሙት ከባድ ችግሮች ናቸው። አሁን ንስር አሞራ ያለው ምርጫ ሁለት ነው። ወይ ካረጀ አካሉ ጋር ዝም ብሎ ተቀምጦ ሞቱን መጠበቅ አልያም ደግሞ አምስት ወር የሚፈጅ ስቃይና መከራ ያለበት መስዋዕትነትን ከፍሎ ቀሪውን 35 ዓመት በደስታ ማሳለፍ። የመጀመሪያውን ከመረጠ በእድሜው አጋማሽ ይሞታልና ታሪኩ እዛ ጋር ያበቃል። ሁለተኛውን ምርጫ ከመረጠ ግን የሚቀጥሉት አምስት መስዋዕቶች ማለፍ ይጠበቅበታል። በመጀመሪያ ከፍተኛ ተራራ ላይ በመውጣት የብቻውን ጎጆ ይቀልሳል። ቀጥሎ ጎጆ ከቀለሰ በኋላ የመጀመሪያ ስራው የአፉን መንቁር ከአለት ጋር በማጋጨት ነቅሎ ይጥላል። ይህን ካደረገ በኋላ አዲስ መንቁር ይወጣለታል። መንቁሩ እስኪያድግ ድረስ ታግሶ በጎጆው ምንም አይነት ምግብ ሳይመገብ መቆየት ግዴታው ይሆናል። አዲስ መንቁር ከበቀለለት በኋላ በአዲሱ መንቁሩ የገዛ እግሩን አሮጌ ጥፍር ነቃቅሎ ይጥለዋል። አዲሱ የእግር ጥፍር ከበቀለለት በኋላ ደግሞ ይህንን አዲስ ጥፍር እንደ መሳሪያ በመጠቀም በሰውነቱ የተጣበቁትን፣ እንዳይበር እንቅፋት የሆኑትን፣ የገዘፉና ያረጁ ላባዎችን ነቃቅሎ ይጥላል። በምትኩ አዲስ ላባ ያበቅላል። ይህን አምስት ወር በዚህ መልኩ በጀግንነት ከተወጣ በኋላ እንደገና ራሱን በራሱ ወልዶና ወጣት ሆኖ ወደ ንስሮች መንደር ብቅ ይላል። አንተም በተመሳሳይ መንገድ አልፈህ በአዲስ ሕይወት ከፍ ብለህ መብረር ትችል ዘንድ ከንስር አሞራው ሕይወት ትምህርት መውሰድ ይኖርብሃል። አየህ በብዙ ችግሮች ተተብትበህ ሊሆን ይችላል። ግን ደግሞ ከችግሮችህ ተላቀህ አዲስ ሕይወት መምራት ትፈልጋለህ። አዲስ ሕይወት ለመምራት ደግሞ የውሳኔ ሰው መሆን ይጠበቅብሃል። ግን ደግሞ ለመወሰን ብዙ ታመነታ ይሆናል። ብዙ ሰበብ ትደረድር ይሆናል። ለውሳኔ ግዜው አሁን አይደለም፤ ትክክለኛ ግዜ ሲመጣ እወስናለሁ ልትልም ትችላለህ። በውሳኔ ደግሞ ግዜው አልደረሰም የሚል ነገር የለም። ሁሌም ቢሆን የውሳኜ ግዜው አሁን ነው፤ ዛሬ ነው። ለመሆኑ ችግርህ ምን ኖራል? ከተቀጣሪነት ተላቆ የራስን ቢዝነስ መጀመር ነው?፣ ካለብህ ሱስ መላቀቅ ነው?፣ ትዳር መመስረት ነው?፣ ትምህርት መማር ነው? መንፈሳዊ ሕይወትህ ላይ መጠንከር ነው? ጤናህን መጠበቅ ነው? ወይስ ሌላ ችግር? ብቻ በሕይወትህ እስከመጨረሻው ድረስ መለወጥ የምትፈልገው አንድ ነገር ይኖራል፡ ፡ ጥያቄው ይህን ነገር እንዴት ታሳካዋለህ የሚለው ነው። ለዚህ ደግሞ ከላይ የተነሳው የንስር አሞራ ሕይወት ጥሩ ምሳሌ ይሆንሃል። ልብ ብለህ ከሆነ ንስር አሞራው ሰባ ዓመት መኖር የሚችለው ሰላሳ አምስት ዓመቱ ላይ ሲደርስ ቆራጥ ውሳኔ ማሳለፍ የሚችል ከሆነ ብቻ ነው። አለበለዚያ ግን ሰባ ዓመት የመኖር እድል አያገኝም። ተፈጥሮ የሰጠችውን እድል ከዳር ማድረስ አይችልም። አንተም ቢሆን አስካሁን ድረስ በሕይወትህ ትርጉም ያለው ለውጥ አላመጣህ ይሆናል። በስራህና በገቢህ ደስተኛም ላትሆን ትችላለህ፣ የጤንነትህ ሁኔታም አደጋ ላይ ሊሆን ይችላል። ትምህርትህ፣ የፍቅር ግንኙነትህም ጥቁር ጥላ አጥልቶበት ሊሆን ይችላል። እናም አሁንም አልረፈደምና ሕይወትህን እስከወዲያኛው ድረስ ለመቀየር ከፈለክ እንደ ንስር አሞራው አሁኑኑ መወሰን ይኖርብሃል። ይህ ሲባል መጥፎ ልማዶች ካሉብህ ማቆም፣ ጤናህ አደጋ ላይ ከሆነ ስፖርት መስራት፣ ተቀጣሪነት ከሰለቸህ በራስህ ቢዝነስ ለመፍጠር ዝግጁ መሆንና ወዘተ የመሳሰሉትን ለማድረግ ፍቃደኛ መሆን ይጠበቅብሃል። ይህን ለማድረግ ዝግጁ ከሆንክና ካደረከው ደግሞ ልክ እንደ ንስር አሞራው አሁን የገጠመህን ችግር ቀርፈህ በቀጣይ የተሻለ ሕይወት የመኖር እድል ይኖርሃል። አይተህ ከሆነ ንስር አሞራው በእድሜው አጋማሽ ላይ የገጠመውን ችግር ለማለፍ ብርቱ መሰዋዕትነትን መክፈል አለበት። ስለዚህ አንተም የምትልግው የሕይወት ደረጃ ላይ እስከምትደርስ ድረስ ዋጋ መክፈል አለብህ። ውጣ ውረዶችን ማለፍ ይጠበቅበሃል። ለችግሮች እጅ መስጠት የለብህም። ያለበለዚያ ግን በተለመደው የሕይወት መንገድ ለመቀጠል ወስነሃልና በሕይወትህ አዲስ ነገር አይኖርም። ተመሳሳይ ሕይወት ነው የምትኖረው። የሚቀየርነገር አይኖርም። ስለዚህ ምርጫው ያንተ ነው። ወይ ትንሽ ተሰቃይቶ በዘለቄታው ሕይወትህን መቀየር፤ አልያም ደግሞ አሁን ያለውን ሕይወትህን ተቀብለህ መኖርና ይችን ምድር ተሰናብቶ መሄድ! የንስር አሞራውን የመጀመሪያ ውሳኔ ከመረጥክ የተሻለና ዘላቂ ሕይወት ለመኖር ወስነሃልና ልክ ንስር አሞራው ደረጃ በደረጃ ከባድ መስዋዕትነትን በሕይወትህ መክፈል ይጠበቅበሃል። ከራስህ ጋር ምከር። የሚጠቅምህንና የሚጎዳህን ላይ። በዙሪያህ ያሉና ተተብትበው የያዙህ ችግሮች ምን እንደሆኑ እወቅ። አለስራህ ያሉህ እንቅፋቶች የትኞቹ እንደሆኑም አንድ በአንድ ለያቸው። ከዛም ለውሳኔ ዝግጁ ሁንና ወደተግባር ግባ። አይተህ ከሆነ ንስር አሞራው 35 ዓመቱ ላይ ሲደርስ እንደልብ እደዳያድን ካደረጉት የሰውነት ክፍሎች ውስጥ አንዱ መንቁሩ ነው። ስለዚህ በልቶ ለመኖር መንቁሩ ወሳኝ ነውና አዲስ መንቁር እንዲበቅልለት መንቁሩን ከአለት ጋር እያጋጨ ነቅሎ ጥሎታል። በምትኩም አዲስ መንቁር በቅሎለታል። አንተም ብትሆን ከዚህ በፊት አላሰራ ያለህን መጥፎ ልማድ ተውና በአዲስ ተካው። ትሰራለህ፣ ትደክማለህ ግን በስራህ ውጤት አይኖርህ ይሆናል። ስለዚህ መነቀል ያለባቸውና ያረጁና ያፈጁ አሰራሮችን የምትከተል ከሆነ እነርሱን ተዋቸውና አዲስ፣ ቀላልና ብልህነት የታከለባቸው አሰራሮችን ተከተል። ይህ በስራህ ብቻ ሳይሆን በግል ሕይወትህ ላይም ጭምር ሊሰራ ስለሚችል ተግባራዊ አድርገው። ያኔ ሕይወትህ እየተለወጠ እንደመጣ በግልፅ ይታይሃል። ንስር አሞራው መንቁሩ ካደገለት በኋላ ለማደን ይገለገልባቸው የነበሩትንና አሁን ግን ያረጁትን ጥፍሮቹን ለመንቀያነት ይጠቀምባቸዋል። ጥፍሮቹ ሲያድጉ ደግሞ ለመብረር የከለከሉትን ክንፎቹን ነጭቶ ይጥልበታል። አየህ ! አንተጋም ያሉት ችግሮች ተደራራቢ ሊሆኑ ይችላሉ። ለአፍታም አስቸጋሪ ሆነው ሊታዩህ ይችላሉ። ነገር ግን በሕይወትህ አዲስ ነገር ለማምጣት እስከፈለክና እስከወሰንክ ድረስ አንዱ ችግር ስትፈታ ሌላኛው ይቀረፋል። ብቻ አንዱን ችግር ለመፍታት አንተ ቁርጠኛ ሁን እንጂ የአንዱ ችግር መፍትሄ ለሌላውም መፍትሄ የማይሆንበት ምንም ምክንያት አይኖርም። #like #moreview #copylink #share #ሠላም_ፍቅር_ለሠው_ልጆች_ሁሉ🙏
Beki Mereja/ቤኪ መረጃ
Region: ET
Thursday 09 May 2024 14:29:07 GMT
Music
Download
Comments
Zed💝🍀 :
aesredagn
2026-06-12 19:30:11
0
kasahun menge :
እና መሰግናለ እደዚህአይነቶች ቤቀጥሉ !!!
2024-05-11 16:15:40
3
ፊዳከ አቢ ወኡ يارسولله 🇸🇦የመቅደላው :
ዛሬ ተይዟል
2025-09-29 20:11:30
0
habte man :
ልክክክክክክክክክክክክ
2026-01-02 16:16:24
0
የአማራፋኖ :
ስም ፅፌ የአባት ስም አልፅፍአለኝ ለመሰጀል
2025-03-31 18:18:27
0
ሐበሻ ስማርት ገብያ :
እንዴት
2024-05-10 17:07:27
0
𝙙𝙖𝙫𝙚🌹ፍቅርነው መንገዴ‼️🇪🇹 :
አወ ማሪያምን
2025-10-30 07:16:58
0
zenawigebreyesus :
mn malet new
2024-07-01 23:46:20
0
@እማ @በፀሎትሽ :
😳😳😳
2024-05-09 20:05:12
2
abdell7079 :
🙏🙏
2024-05-13 07:37:18
1
ፋሲል የእሰቴ ዴንሳው :
🥰🥰🥰
2024-05-13 12:09:40
1
user8240544247777 Ymy :
🥰🥰🥰
2024-06-02 13:22:53
0
ክፉነት ለማንም ደግነት ለሁሉም :
🥰
2025-11-29 12:14:06
0
ጊዜ ዳኛው :
🥰
2025-10-16 14:07:08
0
Lij ሢሣይ 🦅🤴 :
🦅🤴
2026-05-09 20:07:51
0
esmael_møhammed :
🥰🥰🥰
2025-03-10 07:43:48
0
stamalangstamal15 :
👍👍👍
2024-08-11 08:11:02
0
ማርታ ወለተ ሃና 🥰🥰☦️ :
🙏
2025-08-21 11:23:27
0
👉Hunter-Life⛈️ :
👌👌
2026-04-09 18:42:56
0
eskew@12-the Michayel :
neger gen endeniser mebrer kefelgeh ende dakeye atewagn
2024-07-21 11:01:49
0
malt spr :
10Q
2024-05-12 12:39:28
0
To see more videos from user @bwbereket3, please go to the Tikwm
homepage.