@halabazoneprosperity2015: # አርቶ_ፍል_ውሃ አርቶ ፍል ውሃ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ከዞኑ ዋና ከተማ ቁሊቶ በ10 ኪ/ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እጅግ በርካታ ሰዎች ወደ አካባቢው እየመጡ በባህላዊ ህክምና መንገድ እንፋሎቱን በመታጠንና በሙቅ ውሀው በመታጠብ ለፈውስነት ይገለገሉበታል። የፍል ውኃው የሙቀት መጠን ከፍተኛ በሆነው የሙቀት መጠኑ ጎብኝዎች የተለያዩ ሰብሎችን ማለትም... የበቆሎ እሸት ፣ ድንችና የተለያዩ የጥራጥሬ ሰብሎችን በማብሰል የሚመገቡብት ማራኪ ስፍራ ሲሆን ሻይና ቡናንም ቢፈለጉ እዛው እረፍት እያደረጉ በማንቆርቆሪያ የፈላውን ውሃ ብቻ በመቅዳት የተፈጨ ቡና ወይም ሻይ ቅጠልና ስኳር በመጨመር አፍልተው መጠጣት የሚችሉበት ድንቅ ስፍራ ነው። የአርቶ ፍል ውሃ በውስጣዊ እምቅ ሀይሉና በተፈጥሮአዊ ይዘቱ በመታገዝ ወደ ላይ ከ9 እስከ 12 ሜትር ከፍታ ሲዘል ለሚመለከተው ሰው በእጅጉን አስደሳች ስሜትን የሚፈጥር ከመሆኑም ባለፈ ተፈጥሮ ምን ያህል ሚስጥራዊና ድንቅ መሆኑዋን የምንመለከትበት አስደናቂ ስፍራ ነው ። ግንቦትት 28/2016፣ሀላባ ቁሊቶ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ#prosperity #PMOEthiopia

Halaba Zone Prosperity Party
Halaba Zone Prosperity Party
Open In TikTok:
Region: ET
Sunday 09 June 2024 12:04:49 GMT
9523
277
0
105

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @halabazoneprosperity2015, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About