@saviolazeki: እንዲህ እንደዛሬው በጎሳ ፖለቲካ አገር ሳትመሰቃቀል ፥ እርስበርሳችን በአይነ ቁራኛ ሳንተያይ በፊት ... እቃቃ ፈረሰ ዳቦ ተቆረሰ ተባብዬ የእቃቃ ሚስቴ ጋ በመተፈፋፈር መተያየት የጀማመረኝ ሰሞን ፥ ከታላቅ ወንድሜ በተረፈው ፐርም ፀጉሬን ማለስለስ በጀማመርኩ ጊዜ ... ዘመድ ጥየቃ ከአላማጣ ወደ መቀሌ በድሮው ሰላም ባስ ለመሄድ በመስኮት በኩል መጋረጃውን ከፍቼ ተቀምጫለሁ ። በ1996 ዓ.ም ፥ የሐምሌ ወር ጠዋት ። በዚያ ብርዳማ ጠዋት መኪናው መንቀሳቀስ ሲጀምር ነበር ፥ ለመጀመርያ ጊዜ ሙዚቃዋን አጣጥሜ መስማት የጀመርኩት ። ከመኪናው ስፒከር ልብ የሚያሽኮረምመው ድምፅዋ መፍሰስ ጀመረ ... "ሱፍ ገበርዲን ለብሰህ ናልኝ አልልህም... የዘመኑን ካፖርት ደርብ አልልህም " የማውቀው... የራያ ሜዳዎችን እያየሁ በሐሳብ ሩቅ ሀገር ጭልጥ እንዳልኩ ነው ። የማውቀው ደረቴ ሲረበሽ ፥ ነፍሴ ሲተራመስ ነው ። መኪናው ወደፊት እኔ ወደ ማላውቀው ቦታ ስሄድ ይሰማኛል ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በአስቴር አወቀ ሙዚቃዎች ተለከፍኩ ። በመኪናው መስኮት ውጭ ውጩን እያየሁ ... የሆነውን ሁሉ አስባለሁ ። እውታቸውን ነው እላለሁ... ህዝቡ "አስቴር አስቴር የሚለው ፥ በባንዲራው መሐል ያለውን ኮከብ ትተው የአስቴርን ፎቶ ቢያደርጉ ፥ ወደ መድረኩ ነጩን ቀሚሷን ለብሳ ብቅ ስትል እንደ ቤተስኪያን አማትበው ቢሳለሟት ፥ ሃይማኖቶች ሙዚቃ ሐጥያት ነው ቢሉ ( እና አስቴርን ባዳመጠ ጆሮዬ ስብከት ስሰማ ታየኝ እኮ ) ሰራዊት ፍቅሬ አስቴር አዲስ አልበም ስታወጣ የአዘቦት ልብሴን ወዲያ አሽቀንጥሬ ሱፌን ቂቅ አድርጌ እለብሳለሁ ቢል ፥ ታላቅ ወንድሜ አስቴር በቴሌቪዥን ስትዘፍን ሰምቷት ሻወር ከሚወስድበት መለመሉን ከነ ሳሙናው ቢመጣ እውነታቸውን ነው አልኩ ። መቀሌ እስክንደርስ በመሀል ሌላ ሙዚቃ ሳይቀላቀል የአስቴርን ብቻ እየኮመኮምን ተጓዝን ። አስቴር ፦ መጋረጃ ሰንጥቃ ገብታ ጉንጭ ላይ የምታርፍ ለስላሳ ጮራዬ ናት ፥ ግራጫ ከሰአቶቼን ቀለም የምትቀባለኝ ቢራቢሮ ፥ የሌቴ ቤድ ታይም ስቶሪ ፥ የራስጌዬ መብራት ፥ የመጀመርያ ፍቅሬን ያጀብኩባት "ብርቱካኔ" ፥ ምርቃናዬን በሙሓባ ያቀጣጠለች የነፍስ ዕጣን ፥ ስካሬን ያደመቀች እብደቴ ( "ስለ ሰው ስለ ሰው ቀድጄ ልልበሰው" ) ፥ ሲከፋኝ የምታፅናናኝ ጣዖቴ ( አወይ ሰው መሆኔ ) ፥ ትጥቄን የምታስፈታ ኪልዮፓትራ ( ከነገሩ ሁሉ ፍቅር ይሻለኛል ) ፥ እሹሩሩ የምላት ሙናዬ ፥ አፖሎና አርጤምስ የሰፈሩባት የሙዚቃ ካብ ናት ። በየትኛውም የሙዚቃ ልኬት ብትለኩ nothing is like when Aster Aweke singing "ካቡ" እኮ ! She is just afuckin living god ! "አይንህ ሲንከባለል የሰው ልብ ያስቀራል አካላትህ ሁሉ ማሾ ነው ያበራል የአመልህም ነገር ... ዝናው ይነገራል እንጎዲህ ካለ አንተ እንዴት ይታደራል : እንኳን እኔን ቀርቶ የምድር ምድሪቷን ጀምበርም ሰው ብትሆን በልተሃል አንጀቷን" አሜን ነው ወይ ??? @Hab HD ✍🏽 . . #onthisday #ConSantanderConecto #InMyBubbleWithBaseus #fypシ #viral #street #photography #streetphotography #ethiopian #cinematography #aesthetic #fy #explorepage✨ #videoviral #fyp #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹ሀገሬ #cinematic #piassa #ፒያሳ #zekisaviola
Zeki Saviola
Region: ET
Wednesday 12 June 2024 16:43:16 GMT
Music
Download
Comments
™ :
1990✌️
2024-08-07 17:25:07
1
Abdu :
🔥🔥
2024-11-17 21:00:23
0
KalkidanWondwossen :
heartfelt!
2024-06-12 17:38:20
6
Beth :
🖤🖤🖤🖤🖤🖤🖤🖤
2024-06-12 19:10:16
3
DaDa’s Tips 📱 :
🖤🖤🖤🖤🖤🖤🖤🖤🤌🏽🤌🏽🤌🏽🤌🏽🤌🏽🤌🏽🤌🏽🤌🏽
2024-06-13 08:56:28
2
Tsion Girma :
❤❤❤❤❤❤
2024-06-12 20:08:32
1
Nebil Elias :
🫠🫠🫠🫠🫠🫠❤️
2024-06-15 08:57:59
1
adom918- adi :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2024-06-20 09:28:07
1
Urightthere :
Ene idk how you guys can write something so beautiful endzi kmr shoutout to you guys 💕✨
2024-07-10 18:58:38
1
ŊĕBæ :
❤️🩹❤️🩹🤌
2024-08-26 15:30:54
1
ⒹⒶ🀄️♣️ :
🖤🥲🥲🥲🥲
2024-08-17 08:45:08
0
liye01 :
🥰🥰🥰
2024-10-31 20:22:50
0
kidi :
Betam jegna lj nek hulunm aychelew likem adrgelew zefen mrchak imejochu ene betam new yewededkut berta
2025-01-06 11:45:47
0
ተመስገን 🙏 :
የ ሀምሌ ወር ጠዋት wooow
2025-01-06 12:02:14
0
To see more videos from user @saviolazeki, please go to the Tikwm
homepage.