@user7654328902345: 🌹#ቅዱሳን አብርሃ ወአፅብሃ🌹 ☞ወር በገባ በ 4 ቅዱሳን ነገሥታት ወንድማማቾች አብርሃ እና ወአጽብሓ ወርሐዊ መታሰቢያቸው፡፡ ☞ አባታቸው ታዜር እናታቸው ሶፍያ ይባላሉ፡፡ ☞መንትዮቹ የሆኑት እነዚህ ቅዱሳን የተወለድት በክርስቶስ ልደት ታኀሳስ 29ቀንበ312 አ'ም ነው፡፡ ☞በታላቁ አባት በአቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሀን እየተማሩ በእሳቸው እጅ በ330 አ'ም መጋቢት 29 ቀን ተጠመቁ፡፡ ☞አብርሃ ወጽብሓ ከመንግስት አስተዳደሩ ጋር ክርስትናንና ሥርአዓተ ቤተክርስቲያን በመላው ኢትዮጵያ በማዳረስ እጅግ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርገዋል፡፡ ☞ካህናትንና ዲያቆናትን ይዘው በመላው ኢትዮጵያ ሐዋርያዊ ጉዞ በማድረግ ሕዝቡን ሁሉ እያስተማሩ ሃይማኖትን እያጸኑ ሥርዓተ ጥምቀትን እያስፋፋ ብዙ አባያተ ክርስቲያን አንጸዋል፡፡ ☞በሀገራችን በአራቱም አቅጣጫ ወንጌልን አሰተምረዋል አስፋፋተዋል፡፡ ሕግም ሠርተዋል፡፡ ☞አብርሃ ወአጽበሐ በእግዚአብሔር ፈቃድ የሚፈጽሙት ሐዋርያዊ አገልግሎት የሠመረ ሥራቸው ሁሉ የማረ ሲሆን በዚሁ ሐወወርያዊ ጉዞ ተምቤን ተሻግረው ገርዓልታ ከሚባል ቦታ ካነፆቸው መካከል ደብረ ማርያም የበላ ቤተክርስቲያን፤ ከዚህ ቤተክርስቲያን ሌላ በእመቤታችን በቅድስ ድንግል ማርያም ስም አንፁ ዓይባ በተባለው ቦታ ጉልባሽ በተባለ ተራራ ሥር በእመቤታችን ስም መቅደስን ሠሩ፡፡ ከዚያ አልፈው ሐርማት በተባለ ቦታ በሐውዜን ቤተመቅደስ ሠሩ ይህም በአሁን ጊዜ በአቡነ ተክለሃይማኖት ስም የሚጠራ ነው፡፡ ☞የአብርሃ ወአጽብሐ ሓዋርያዊ ጉዞ በጎጃም ክፍለ ሀገር ቀጠለ ዛሬ በከፍተኛ ደረጃ የምትታወቀው የመርጦ ለማርያምን ቤተክርስቲያን አነፁ፡፡በጎጃም ሕዝቡ አስተምረው አጥምቀዋል፡፡ ☞አብርሃ ወአጽባሐ አሥራ ስምንት አመት በኅብረት ወንጌልን እያሰተማሩ ኢትዮጵያን ዞሯት፡፡አንዱ በትግራይ አንዱ በሸዋ በተቀመጡ ጊዜም ምንም እንኳን በአኗኗር ቢለያዮም በመንፈስ ቅዱስ በሐሣብ አንድ እንዲሆኑ ሰላደረጋቸው በመንፈስ አልተለያዪም ነበር፡፡ሥራቸውን ሁሉ ያከናዉኑ ነበር እንጂ የተያየ ተግባር አላከናወኑም ነበር፡፡ ✞ቃል ኪዳን☞ጌታችን ወዳጄ ሆይ ዝክርህን የዘከረ፤ ሰምህንም የጠራ ምሬልሀለው በስምህ ቀዝቃዛ ውኃ ያጠጣ እኔ የሕይወት ውኃ አጠጣዋለሁ፤ በስምህ ለተራበ ቁራሽ እንጀራ የሰጠ ያበላ የሕይወት እንጀራ አበለዋለሁ፤ በስምህ ታረዘውን ያለበሰ የጽድቅ ልብስ አለብሰዋለሁ፤በስምህ ማኅሌት የቆመ የመላዕክትን ማኃሌት አሰማዋለሁ አለው፡፡ አብርሀሃም ይህን በሰማ ጊዜ እየሰገደ ይህን የማይገባኝን ታላቅ ክብር የሰጠህኝ ሰምህ ይባረክ ለአገልጋይ ለወንድሜ ለአጽብሐም አጋንንት እንዳይበረታበት እናት አባት ወንድም ሁነው በማለት ፈጣሪውን አመሰገነ ተማፀነ፡፡ ☞ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እኔ ለአጽብሐ በረድኤት አልልየወም አንተ በሥጋ ብትለይ በመንፈስ ከሱ ጋር ትኖራለህ፡፡ ☞ታላቁ አብርሀም በ364አ'ም ጥቅምት 4እሁድ ዕለት አረፈ፡፡ከ13አመት በኃላ ታናሹ አጽብሓ በ379 ዓ'ም ጥቅምት 4ቀን አረፈ፡፡ ዓመቱ ይለያይ እንጂ ልደታቸውም ዕረፍታቸውም አንድ ቀን ነው፡፡ የተቀበሩትም እራሳቸው በሳነፁት ውቅሮ በሚገኘው ፍልፍ ዋሻ ነው፡፡ ☞በዚህ ቤተመቅደስ ነሐሴ 13 ቀን በበዓለ ደብረታቦር ጥቅምት 4ቀን የሁለቱ ነገሥታት በዓለ ዕረፍት በሚከበርበት ጊዜ ዓምዶቹ እነሠ ቤተ መቅደሱ ማር እና ወተት ውኃ ያፈልቃሉ በዚህም ተአምራዊ ጸበል ብዙ ሕሙማን ፈውስ ያገኛሉ፡፡ ☞ጸበልሙ የሚፈልቀው በአብዛኛው ጊዜ ነሐሴ 12በዋዜማው መፍለቅ ይጀምር እና ነሐሴ 14 ቀን ይደርቃል፡፡ ጥቅምት 3 ቀን በዋዜማው ይፈልቅና ቅዳሴ ተጠናቅቆ እትው እንደተባለ መድረቅ ይጀምራል፡፡ይህ ታአምር ነበር የሚባል ሳይሆን ዛሬም ድረስ አለ በአይን ይታያል፡፡ ☞የንግስና ስማቸው ኢዛና እና ሳይዛና ይባላል፡፡ ☞ከሁለቱ ደግ አባት የበረከታቸው የቃልኪዳናቸው ተካፍ ያድርገን፡፡ ☞ደጃቸውን ለመርገጥ ያብቃን፡፡ ☞የጽሁፍ ምንጭ☞(ታሪአ ነገስታት አብርሃ ወ አጽብሐ) በመምህር ኃይለ ሥላሴ ከተጻፈ የተወሰደ፡፡ ☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ

🌏እማ ህይወቴ💚💛❤
🌏እማ ህይወቴ💚💛❤
Open In TikTok:
Region: AE
Thursday 11 July 2024 03:47:12 GMT
1427
174
16
4

Music

Download

Comments

demsasheayele
ደምሣሽ :
🥰🥰🥰
2024-07-11 03:58:53
0
useyehuna1
masre mmmm :
❤❤❤
2024-07-11 04:38:52
0
user555630704788
ወረቱቃብረሀን :
🥰🥰🥰
2024-07-11 06:42:27
0
meronmesikile
Meron Mesikile :
❤❤❤
2024-07-11 07:25:59
0
itszainaba0
ሀበሻዊት ❤ :
🥰🥰🥰🥰🙏🙏🙏
2024-07-11 07:31:06
0
alemayehuayele1
alemayehuayele1 :
🥰🥰🥰
2024-07-11 07:53:37
0
yordiyekiya
ኪያዬ 🌏ህያቤ የኔ👑🌞👩‍👧 :
🥰🥰🥰
2024-07-11 09:21:36
0
darertu14
Darertu21 :
🥰🥰🥰
2024-07-11 09:24:07
0
mesi32906
user81822293146 :
❤❤❤
2024-07-11 09:39:30
0
talema.yedera
ቅዱስ ሚካኤል አባቴ 1️⃣2️⃣ :
🥰🥰🥰
2024-07-11 13:32:45
0
user9222879326585
ሁሉ በግዚሀብሄር ሇነ :
🥰🥰🥰
2024-07-11 13:40:07
0
user6561760003805
masii :
🥰🥰🥰
2024-07-11 13:52:47
0
ekzaebher
astergoteom :
🥰🥰🥰
2024-07-11 17:17:08
0
alym..tktk
አለም :
🤲🤲🥰🥰🙏🙏❤️❤️
2024-07-11 17:22:29
0
user1597815874999
የማርያም ልጅ :
🥰🥰🥰
2024-07-12 02:12:21
0
meaza.asnake
Meaza Asnake :
አሜን በእዉነት
2024-07-13 18:35:56
0
To see more videos from user @user7654328902345, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About