@dawit_tilahun_5: #ተዓምረ_ቅዱስ_ገብርኤል "ልጅ እያለሁ ገና በስድስተኛ ወሬ አቅፋኝ ከነበረች ሠራተኛ ወድቄ እግሬ ተሰበረ። ያኔ ታዋቂ ወደ ነበረው ወደ አርሾ ሆስፒታል (?) ወሰዱኝ። ሙሉ ምርመራ አድርገው "እግሩ መቆረጥ አለበት" ተባልኩ። እናቴ "አላስቆርጥም" አለች።"እስከ አምስተኛ ዓመቴ ድረስ በእናቴ ጀርባ ታዝዬ ነበር ከቦታ ቦታ የምንቀሳቀሰው። ዕድሜዬ እየሄደ ምንም እንቅስቃሴ ሳላደርግ የምመገበው ክብደቴ እየጨመረ ለእናቴ ሸክም የማልመች ሆንኩ።"አምስት ዓመት ሲሞላኝ ከሰባተኛ እዚህ ግቢ ገብርኤል ድረስ በታክሲ ሳይሆን በጀርባዋ አዝላ አመጣችኝ። ቤተክርስቲያኑ ጋ እንደ ደረሰች ውስጥ ገብታ 'ቅዱስገብርኤል አሁንስ እንዳደረክ አድርገው' ብላ እዛው ጥላኝ ወጣች። የንግሥ በዓል ስለነበረ ሰው ይዞኝ እንዳይወጣ በሩ ላይ ቆማ ትጠብቀኛለች።" "ለአንድ ሰዓት ተኩል ያህል ቤተክርስቲያኑ ውስጥ ከቆየሁ በኋላ #በሁለት_እግሬ #ቆሜ እየሮጥኩ ወደ እናቴ ሄድኩ። እናቴ ማመን አቃታት፤ ዕንባዋን እያፈሰሰች ቅዱስ ገብርኤልን አመሰገነች። ያየ ሰው ሁሉ ዕልል አለ ቅዱስ ገብርኤልን አመሰገነ!" "እናቴ ይዛኝ በእግሬ ከግቢ ገብርኤል እስከ ሰባተኛ ወሰደችኝ" (ተራምዶ የማያውቅ እግር ለመጀመሪያ ጊዜ ይህን ያህል ርቀት ያውም የ5 ዓመት ሕፃን በሰው ዘንድ የማይታሰብ ነው። ለሱማ ምን ይሳነዋል?!) "ይኸው ያ ሁሉ አልፎ ትልቅ ሰው ሆኜ ትዳር ይዤ የሦስት ልጆች አባት ሆኜ የመጀመሪያ ልጄን በነቀምት ገብርኤል፣ ሁለተኛ ልጄን በአዲስ አበባ ቅዱስ ሩፋኤል ክርስትና አስነሥቼ ሦስተኛ ልጄን ይኸው ዕድል ገጥሞኝ ድኅነት ባገኘሁበት፣ ቆሜ በተራመድኩበት ቤተክርስቲያን ክርስትና ላስነሣ ነው።""ይህንን ምስክርነት ለመስጠት እያሰብኩ እስካሁን ተሳክቶልኝ አያውቅም። ዕድል እስኪመቻችልኝ እናንተ ላገኛችሁት #ንገሩልኝ " ስላለን ይኸው ይህንን ድንቅ ተአምር ለእናንተ አደረስኩ። ለወንድማችንና ለእናቱ የደረሰ ተራዳኢው መልአክ ለእኛም ይድረስልን። አሜን። ሐምሌ 19 @እልአሮድዮን @eyositeshe @nardos @ዘብሥራት #ገብርኤል_ስለው_ሰምቶ_መጣ_ወደእኔ_ፈጥኖ

Dawit Tilahun
Dawit Tilahun
Open In TikTok:
Region: ET
Thursday 25 July 2024 07:58:51 GMT
113835
29681
168
1618

Music

Download

Comments

mercy3679
mercy :
voice 🥺🥰 esu yetbkeh ❤️🙏
2024-07-25 19:47:21
29
arsema2319
ARSEMA MAYA🌹🌹 :
🥹🥹caption 🙏🏽🙏🏽yene abat absariw kidus Gabriel 🥰🥰🥰
2024-07-25 18:51:23
16
seblekibatu
seble🧚‍♀️ :
All Eyes on Gofa
2024-07-26 13:49:02
1
missshekorina
Winta :
19❤️🙏
2024-08-01 04:15:58
1
user1959079982774
ሰላሴ :
good voice
2024-07-27 12:21:44
0
maki_habeshawit
Maki Habeshawit Gel :
የኔ ፈጥኖ ደራሽ ቅድስ ገብርኤል 🥰 አንተን የሰጠን ልዑል እግዚአብሔር ይመስገን 🥰🥰🥰
2024-07-25 18:43:01
111
shebri58
shebri :
በቤቱ ያቆይክ ዝማሬ መላዕክት ያሰማህ🙏🙏
2024-07-25 09:19:20
71
yeabkaldesalegn1
yeabkal :
Devoye betam yamral መላኩ ቅዱስ ገብርኤል ይጠብቅህ🙏🙏🙏🙏
2024-07-25 08:18:09
10
To see more videos from user @dawit_tilahun_5, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About