@efsunizm_:

Efsunizm
Efsunizm
Open In TikTok:
Region: TR
Thursday 01 August 2024 18:43:19 GMT
1528
43
0
2

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @efsunizm_, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

ታማችሁ አንድን ሰው መኪና እንዲነዳልህ ወይም ሰርቶ ገንዘብ እንዲያስገባላችሁ ልትቀጥሩት  ትችላላችሁ፣እየተሰቃያችሁበት  ያለውን ህመም እንዲሸከምላችሁ ግን ልትቀጥሩት  አትችሉም!! ምድራዊ የሆኑ ቁሳቁሶች ሁሉ ሊጠፉ ፣ዳግም ሊገኙም ይችላሉ፥ አንድ ጊዜ ካመለጠ ደግመህ ልታገኘው የማትችለው አንድ ነገር ግን አለ… እርሱም #ህይወትህ ነው።አንድ ሰው የቀዶ ጥገና ወደሚደረግለት ክፍል ሲገባ አንብቦ ያልጨረሰው አንድ መጽሃፍ ትዝ ቢለው የመጽሐፉ ርዕስ
ታማችሁ አንድን ሰው መኪና እንዲነዳልህ ወይም ሰርቶ ገንዘብ እንዲያስገባላችሁ ልትቀጥሩት ትችላላችሁ፣እየተሰቃያችሁበት ያለውን ህመም እንዲሸከምላችሁ ግን ልትቀጥሩት አትችሉም!! ምድራዊ የሆኑ ቁሳቁሶች ሁሉ ሊጠፉ ፣ዳግም ሊገኙም ይችላሉ፥ አንድ ጊዜ ካመለጠ ደግመህ ልታገኘው የማትችለው አንድ ነገር ግን አለ… እርሱም #ህይወትህ ነው።አንድ ሰው የቀዶ ጥገና ወደሚደረግለት ክፍል ሲገባ አንብቦ ያልጨረሰው አንድ መጽሃፍ ትዝ ቢለው የመጽሐፉ ርዕስ "ጤናማ ህይወት የመኖር ሚስጥር" የሚል ሊሆን እንደሚችል ጥርጥር የለውም።በየትኛውም የህይወት ከፍታ ላይ ብንሆን የህይወታችን መጋረጃ የሚዘጋበትን ቅጽበት ፊት ለፊት የምንጋፈጥበት አንድ ቀን መምጣቱ አይቀርም። ለቤተሰብህ፣ለትዳር አጋርህ እና ለጏደኞችህ የፍቅርን ውርስ አስቀምጥላቸው፣ራስህን ተንከባከብ ፣ ከሌሎች ጋር መልካም ግንኙነት ይኑርህ።እያደግን ስንሄድና የህይወት ትርጉሙ ሲገባን ውድ ሰዓትም አሰርን ርካሽ ሰዓት ሁለቱም የሚነግሩን ጊዜ እኩል መሆኑ ይገባናል።በኪሳችን ውድ ቦርሳም ያዝን ርካሽ ቦርሳ ፣በውስጡ የሚኖረውን የገንዘብ መጠን አይቀይረውም።የኣንድ ሚሊዮን ብር መኪናም ነዳን የሶስት መቶ ሺህ ብር መኪና ፣የመንገዱ ርዝመት አይቀየርም፣ አቅጣጫውም ያው አንድ ነው፥፥የምንደርሰውም ያው እዚያው ቦታ ነው። 👉ውድ መጠጥም ጠጣን ርካሽ መጠጥ፣ ስካሩና አድሮ የሚያመጣው ራስ ምታት ለውጥ የለውም፣ሰፊ ግቢ ውስጥ ኖርንም ጠባብ ቤት፣ ብቸኝነቱ ያው እኩል ነው፣የውስጥ ደስታ በቁሳቁስ እንደማይገኝ ያን ጊዜ ይገባሃል።አውሮፕላን ላይ የክብር ቦታም ተቀመጥክ ወይም ተራ ቦታ፣አውሮፕላኑ ከተከሰከሰ እኩል ቁልቁል ትወርዳለህ።እውነተኛው ደስታ የሚገኘው ከቤተሰብህ፣ከጓደኞችህ፣ከዘመዶችህ ጋር በሚኖርህ ውብ ጊዜኣት ብቻ ነው።ከእነርሱ ጋር በምታሳልፈው ጊዜ፣በምትጫወተው ጨዋታ፣ በምትዘምረው መዝሙር፣በምትስቀው ሳቅ እውነተኛ ደስታን ታገኛለህ። ሊካዱ የማይችሉ የህይወት እውነታዎች አሉ።ልጆችህ ሀብታም እንዲሆኑ አታስተምራቸው። ይልቅ እንዴት ደስተኛ መሆን እንደሚችሉ አስተምራቸው። ሲያድጉ የነገሮች ዋጋ ሳይሆን ጥቅማቸው ይገባቸዋል።ምግብህን እንደ መድሃኒት ውሰድ ካልሆነ መድሃኒት እንደምግብ ትወስዳልህ።ሰውን ውደድ ለሰው ትልቅ አክብሮት ይኑርህ። ለቃልህ ታመን፣በህይወትህ ለአንድ ሰው ፅኑ ፍቅር ይኑርህ። የሚወድህ ሰው በቀላሉ አይለይህም፣ከአንተ ለመለየት 99 ምክንያት ቢኖረው እንኳ መለየት በማይችልባት አንዲት ነገር ላይ ፀንቶ ይቆማል። "ሰው ሆኖ በመፈጠር"ና "ሰው በመሆን" መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። ይህ የሚገባቸው ጥቂት ሰዎች ናቸው።ስትወለድ ውድ ነበርክ፣ስትሞትም ውድ ትሆናለህ፣በመካከል ያለውን ማስተካከል ያንተ ፋንታ ነው።በፍጥነት ለመሄድ ከፈለክ ብቻህን ሂድ፣ሩቅ ለመድረስ ከፈለግህ ግን ከሌሎች ጋር አብረህ ተጓዝ። ሁልጊዜም ለሰው ቅን አስብ። ለሰዎች ክፋ ማሰብ በራስ ላይ መርዝ መነስነስ ነው። ከተንኮል እርቀህ ራስህን በቅን ተግባር ሱስ አሲዘው። ያኔ በሰማይ በምድር ትባረካለህ። 👉በዓለም ላይ ያሉ #ስድስቱ ፈዋሽ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው… ✨የፀሃይ ብርሃን ✨እረፍት ✨ስፖርት ✨ጥሩ ምግብ ✨በራስ መተማመን እና ✨ጓደኛ እነዚህን አጥብቀህ ያዝ። ደስተኛ ህይወትን አጣጥም!! መልካም ጊዜ! ሸር ይደረግ! እግዙአብሔር ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋር ይስጠን አሜን🙏እግዚአብሔር ብርሃኔና-መድሃኒቴ ነው።

About