@mikiyas1789: ከልጅነቴ ጀምሮ ቤት ዉስጥ ሰላም ፍቅር እያየሁ ነዉ ያደግኩት። የሆነ ጊዜ ላይ ደስታና ፍቅሩ ጭቅጭቅ ወደ ፀብ ተተካ ! አባቴ መስከር ጀመረ። እናቴ ደግሞ የአባቴ ስካር ስላማረራት ትናገረው ነበር። በርግጥ እናቴ የሱ ነገር ሆኖባት እንጂ ጭቅጭቅ አትውድም በዚ የተነሳ ይደባደባሉ ሳይደበድባት ነግቶ አይመሽም። እኔና እህቴም ድብድቡን ክፍላችን መሽገን በጭላንጭል እየተመለከትን አደግን። ፀባቸዉ ገና ሲጀመር እንባዬ ከአይኖቼ ዱብ ዱብ እያለ ክፍሌ ተደብቄ አያለሁ። ሁሌም ሰላም የለኝም። አንዳንዴ የአባቴ ተግባር እኔን ራሱ በጣም ያበሳጨኝ ነበር። እንግዳ በሚመጣበት ጊዜ አመትባል በሆነበት ውቅት አባቴ ያለው መጠጥ ቤት ነው። እንደዚ ከመሆኑ በፊት የሚያስቀና ቤተሰብ ነበርን አባቴ ለእኛ ያለው ክብር ደስ ስለሚል ጓደኞቼ ይቀኑብኝ ነበር። እድሜዬ እየጨመረ ሲመጣ እና ነገሮችን ላቅ ባለ እይታ ማገናዘብ ስጀምር እናቴ የጭቅጭቁን መናሻ ምን እንደ ነበር? አባቴ ለምን እንደዚ እንደሆነ ጠየኳት የአባቴ ሁኔታ ምን ያህል መጥፎ እንደሆነ ስለተረዳሁት የእናቴ መናደድ ሲያንሳት ነዉ ወደሚል ድምዳሜ ደረስኩ። ምንም አባቴ ቢሆንም በፍፁም ለእኛ አርዐያ መሆን እንደማትችል ተረዳሁ። ።እኔ እና ታናሽ እህቴ ታዲያ እህቴ አባቴን በሚላት ነገር ለእናቴ መጥፎ አስተሳሰብ እንዲኖራት አድርጎል የሚጠጣበት ምክንያት ያልሆነውን እየነገራት ለማሚ ፍቅር እንዳይኖራት ባደረገ ቁጥር እቤት ሰላም እየራቀ መጣ አባቴን ምን ያህል አሳፋሪ ድርጊት እያደረገ "ሴት ውደ አባቷ ሆነ እንዴ ሲለኝ ይቺ አባባል የእናትሽ ቢጤ ነሽ ብትል ይቀልሀል እያልኩ። ምክሬን አልቀበልም በፍፁም አልተቀበለኝም። አባቴ ይህም አልበቃ ብሎት በየመጠጥ ቤቱ ስሟን ማጥፋት ጀመረ። ሚስጥሯን መደበቅ እና የጎደለውን መሙላት ሲገባው ያልሆነችውን የሆነችውን ማውራት ጀመረ ። እቤት ውስጥ መናናቅ ሁሉንም ነገር በየግል ውሳኔ መውሰን ተጀመረ የቤተሰቡ መሰረት ተናጋ!ከምንም በላይ የሚገርመኝ የእናቴ ትግስት ፅና ነው .... ለምን አትፈታውን? እኔ ብሆን እንደሷ ይሄን ያክል ጊዜ የምታገስ አይመስለኝም። . እድሜዬ ከፍ ብሎ የአስራሁለተኛ ክፍል ተማሪ ስሆን ቤት መግባት የሚባል ነገር አስጠላኝ። ጠዋት ከቤት እውጣለው በሰበብ አስባቡ ማታ አምሽቼ እገባለሁ ማታ ወደ ቤት ስመለስ ልክ ወደ ሀዘን ቤት የምገባ ይመስለኛል። ወደ ቤት ላለመመለስ ስል ቀኑን በተቻለኝ መጠን ራሴን በተለያዩ ነገሮች ቢዚ በማድረግ አሳልፋለሁ። ከተውሰና ጊዜ በኃላ ከቤተሰቤ የተነጠኩትን ያጣሁትን ፍቅር ከክበቦች ለማግኛት ወደ አርት ውዳለበት አቀናው ብዙዎቹ ጓደኞቼ ቤታቸዉ ዉስጥ ያላቸዉ ሰላም እና የቤተሰብ ፍቅር ምን ያህል ትልቅ ፀጋ እንደሆነ አይረዱትም። "ከሰፈር ስድብና አሽሙር ችዬ ሁሉንም በፍቅር ሳያቸው " ሲመለከቱ በጥንካሬዬ ይገረማሉ። እኔ ከእዚ የገባሁት ያንን ጭቅጭቅ አለመስማት መሸሸጊያዬ ነው። ቤተሰብ የሁሉም ነገር መሰረት ነዉ። መልካም ባልሆነ ቤተሰብ ዉስጥ ያደገ ልጅ መጥፎ ቢሆን አይገርምም። ጊዜዉ እየገፋ ሲመጣ የምሳተፍባቸው ክበቦች እና የዳንስ ምሽት ለጊዜዉ ከሀዘናን ጭንቀቴን ከማስረሳት በቀር እዚ ሙያ ውስጥ የመቀጠል ሀሳብ እንዳሌለኝ አውቃለው። . እድሜዬ 22 ሲሆን ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተመድቤ ፊዚክስ ዲፓርትመንት መማር ጀመርኩ። ሀዋሳ በጣም ዉብ ከተማ ነች። መንገዶቿ በአረንጓዴ ልማት ያጌጡ እና ፅዱ ናቸዉ ። ከፊቼ ጋር ሲነፃፀር የማይገነኝ ነዉ። ሀዋሳ ከዚ በፊት እኔ አባቴ እናቴ እህቴ ሆነን ለጉብኝት መጥቼባት ነበር ግን ታይታ የማትጥገብ ነች። የላንጋኖ ሀይቅ ታይቶ አይጠገብም ... ብቻ ሁሉም ነገሮ ደስ ይላል። በአንድነት የሰፈሩባት ለምለም ምድር ናት። ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግቢዉም እንደ ከተማዋ አረንጓዴ ነዉ። ዩኒቨርስቲ መግባት ልክ እንደኔ ባልታሰበ ሰዓት ሰላሞን ለተነጠቀ ሰላም ከሌለዉ ቤተሰብ ለመጣ ሰዉ ትልቅ እረፍት ያለዉ ቦታ ነዉ። ትምህርት ተጀምሮ ጥቂት ወራት እንደተማርን ከክፍል ተማሪዎች ጋር መግባባት ጀመርኩ። ውራቶች የፈጀብኝ እኔ ቶሎ ስለማልግባባ ነው። አይን አፋር ቢጢ ነኝ። ሲጀመር ግቢው ውስጥ ያሉ ልጆች ቅልብን ይስባሉ የሴቶች አለባበስ የውንዶች ቁመና እረ ስንቱን.........።..።."" ያንን ቤት ማስታውስ አልችልም ... ሳሚ ፣ ናቲ እና አሮን ጓደኞቼ ሆኑ እኔ ምንም አይን አፋር ነገር ብሆንም ግን ከተግባባን በኃላ ለቀቀኝ። ከእህቴ ልጅ እቤት በተፈጠረው ነገር መልካም ቅርርብ ስላልነበረኝ የወንድምነትን የህትነትን ሁለቱንም ፍቅርን ከነሱ ለማግኘት ብዬ በደንብ ቀረብኳቸዉ። ሳሚ ን ረጋ ብዙም ወሬ የማይውድ ቀይ ድሬ ልጅ ነው። ከአሮን ጋር ያንድ ሀገር ልጆች ነን ከፊቼ ነው የመጣው ። . ናቲ የሀዋሳ ልጅ ነው እድል ሆኖ ባገሩ ደረሰው ...... ቀስ እያልን እየተላመድን መጣን ከመላመድም አልፎ ምግብ አብረን እየተጎራረብን ስንበላ ፍቅራችን ያስቀና ጀመር ። ማናችንም ተነጣጥለን በልተን አናውቅም በፆታ እኔ ብቻ ሴት ነበርኩ። አመሻሽ ላይ ከጓደኞቼ ተለይቼ ውደ ላይብረሪ ለመግባት ስል ማሚ ደውለችልኝ ሰላምታ ከተለዋውጥን በኃላ አባቴ እንዴት ነው ስላት ድምፆ እራቀብኝ ዝምታ ሰፈነ..... . #ይቀጥላል......
Region: ET
Tuesday 27 August 2024 13:01:47 GMT
Music
Download
Comments
kidest Degu የድሬዋ 27 :
በናትሽ ቀጣይ😩😩😩😩😩😩😩
2024-08-28 05:38:08
99
😜ቤኪ እና ሚላ 😍beki & mila :
next pls
2024-09-01 09:36:11
2
@MoM :
next
2024-08-28 08:53:16
1
Nemar :
ሂየን ውሉከማነብትምርቴን ባነብ የት እደርስ ነበር።
2024-11-12 13:34:59
1
𝓽𝓼𝓲𝓷𝓪𝓽𓍢 :
next pls🥰🙏
2024-10-13 01:39:08
1
dave :
please part 2
2024-08-29 16:58:53
3
stotaw ye 21 ljj :
part 2😢😢😢
2024-10-29 21:44:31
1
carter. search.insight :
next place 😔😔
2024-08-27 17:44:49
5
=méļâķù âđãñé🚭🏋🏻♀️💯🔱Ⓜ️ :
ገና ዛሬ እንግሊዝ አለመቻሌን ወደድኩት 😁
2024-10-11 15:52:55
10
betibetibetibetibetibetibetibe :
ቀጥይ
2024-09-01 08:40:58
1
lili yasagadit lje :
ቀጣይ
2024-09-01 17:18:20
1
ቲጂ ወለዬዋ 💥🎼❤️💛💚 :
ቀጣይ😱
2024-08-31 21:48:32
1
አረ ባቲ ባቲ :
ቀጣይ
2024-09-01 15:51:58
1
user2547193352285 :
እረ ቀጣይ
2024-08-31 12:03:37
1
sirgut777 :
ቀጥይ
2024-09-01 13:29:21
1
yabuti2130 :
kexay🙏🥺
2024-08-29 19:05:36
1
@liya12 :
ke menta menged kemil mesaf lay yetewesed ymeslal arif new chershiln please
2024-08-30 22:13:00
3
እናት አለሜ🥰🥰🥰 :
nexst
2024-08-30 18:44:22
1
dawit abebe :
ቀጣዪ
2024-09-01 18:01:21
1
yordanos886 :
Ere ketaye abakishe
2024-08-30 03:58:02
1
💣gemer🤞 :
ቀጣይ ይለቀቅ
2024-09-27 01:00:23
1
Kidy Alemayehu :
ቀጣዩ ይለቀቅ በናትሽ
2024-08-30 19:18:06
1
𝐝𝐚𝐠𝐢𝐢ꨄ :
next pls🙏🙏
2024-08-28 05:54:34
3
rebu :
era ketay🥰🥰
2024-08-30 08:05:01
1
marshet :
ቀጣዩን አፍጥኚው
2024-08-30 23:34:19
1
To see more videos from user @mikiyas1789, please go to the Tikwm
homepage.