@qumuli.com: 5 nisha ne shkoll, baba mka qit pi shpis, jeta tum shku borllog,fm um ka lan, edhe apet se apet sum han loqja #cima #humor #fyp #dhezipahiri #viral #dhezipahiremdoket😂

qumuli.com
qumuli.com
Open In TikTok:
Region: XK
Thursday 12 September 2024 07:31:34 GMT
70156
857
11
824

Music

Download

Comments

lh69609
LH ☕ :
LH😢😢😢
2024-10-08 10:28:25
0
fitim.iseni1
FITIM.BARUTI. :
😂
2025-10-28 12:51:47
0
apple.user994522
Apple User994522 :
😁😁
2025-05-13 11:34:35
0
mustiberisha1
🖤🥷 :
😂😂😂😂😂😅
2024-12-07 09:38:07
0
lavdrimismani4
💙 :
😂😂😂
2024-11-12 20:29:29
0
sadikkryezi
Sadik Kryezi :
😂😂😂😂😂
2024-10-06 10:13:16
0
banipn10
/¥BANI¥\ :
🤣🤣
2024-09-17 05:12:33
0
roniiiiiii_02
roniiiiiii_02 :
🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣
2024-09-16 13:39:26
0
eyooo.ar
️ :
🤣🤣😂😂
2024-09-12 16:10:17
0
meti_meti9519
meti_meti :
Tu i kerku dhent🤣🤣
2025-11-16 23:09:08
0
didyoueatmycake
Coldbreezy :
❤️❤️❤
2025-10-15 17:40:03
0
To see more videos from user @qumuli.com, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

አንጋፋው የቅኔና የመጽሐፍ  #መምህር  #ዐረፉ !  ታላቁ የቅኔ ሊቅ የኔታ ሊቀ ጠበብት መሠረት ዓለሙ ጥቅምት 27 ቀን  2019 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ ዐርፈዋል።      #ሊቀ ጠበብት #መሠረት መሠረት ገብረ ሕይወት መባል ሲገባቸው ፡በቀለም አባታቸው   በታላቁ ሊቅ   በሊቀ ኀሩያን  ዓለሙ  ዘቃጨና ኢየሱስ   ስም ይጠሩ ነበር  ፡፡      ሊቀጠበብት መሰረት ዓለሙ  በተወለዱ በ፰ ዓመታቸው   የቤተሰብ  ከብቶችን እየጠበቁ  ነበር ያደጉት  ፡፡ ለ፲፰  ዓመታት  ከልዩ ልዩ መምህራን  በተማሪነት  ሕይወት  ቀለም እየሸመቱ  ቆይተዋል፡፡የአባትነትን ውኃ ልክ የማይባቸው አባቴ ነበሩ።    ከልዩ ልዩ ሊቃውንተ  ቤተ ክርስቲያን   ውዳሴ ማርያም ፤ቅዳሴ ማርያም  ዳዊትና ነገሥት በአንድምታ   ተምረው አሰመስክረዋል፡፡      በስማዳ ወረዳ  ውስጥ ኮሽ  ቅዱስ ገብርኤል   ከሚባል የገጠር ከተማ  ለ፪ ዓመታት፤ ጋይንት ወረዳ ለ፰ ዓመታት፤ ስማዳ ወገዳ ጊዩርጊስ  ለ፲፪ ዓመታት ፤ወረታ ደብረ ገነት በዓታ ለማርያም ለ፪ ዓመታት ፤ በወረታ ደብረ  ብስራት  ቅዱስ ገብርኤል  ለ ፳  ዓመታት  በቅኔ መምህርነት  በአጠቃላይ  ለብዙ ዓመታት  በቅኔ መምህርነት ብዙ ደቀ መዛሙርትን እና እጅግ ብዙ የቅኔ መምህራን  አፍርተዋል። ሊቀ ጠበብት መሠረት ዓለሙ እንደ ሰማዕታት ወንበር ተክለው ባስተማሩበት ሁሉ መከራ ሲቀበሉ የኗሩ እውነተኛ መናኝ ናቸውተ         በአሁኑ ወቅት  በተለያዩ   የሀገሪቱ   ክልሎች   ከሊቀጠበብት   መሠረት ዓለሙ  ተምረው  በርካታ የቅኔ መምህራን  ወንበር ዘርግተው   እያስተማሩ ይገኛሉ ፡፡    ከሊቀጠበብት መሠረት ዓለሙ  ተምረው በአዲስ አበባ ከተማም  በልዩ ልዩ  አድባራትና ገዳማት   ወንበር ዘርግተው   የሚያስተምሩ  የቅኔ  መምህራን   አሉ ፡፡    ሊቀጠበብት መሠረት ዓለሙ በትምህርት አሰጣጣቸው ትጋት ሁሌ እደነቃለሁ። በተማሪ ቤት  ሳሉ መጽሐፈ ነገሥትና መጽሐፈ ሳሙኤል፤ ውዳሴ ማርያም ፤ ቅዳሴ ማርያም  ዳዊትና ነገሥት  አንድምታ   በእጃቸው ጽፈዋል፡፡  ከሐምሌ   5  ቀን 2000 ዓ.ም  ጀምሮ  እስከ አሁን ድረስ በወረታደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል በቅኔ   መምህርነት   በማገልገል ላይ  ነበሩ ።       የቤተ ክርስቲያናችን  ሳይንስ ከሚሰጥባቸው የቅኔ  ጉባኤ ቤቶች  የወረታ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል የቅኔ ጉባኤ ቤት  አንዱ ነበር ።      በዘመናቸን  አብያተ ክርስቲያናት  በብሎኬት  እየተገነቡ ነው፡፡ እነዚህን አብያተ ክርስቲያናት  የሚያገለግሉ ሊቃውንት የሚፈልቁባቸው የአብነት ትምህርት ቤትች ግንባታ ግን  ብዙ ትኩረት አልተሰጣቸውም  ነበር  ፡፡ ይባስ ብሎ የወረታ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ሰበካ ጉባኤ የሣር ጎጆዎችን ለዐፀደ ሕፃናት ማስፋፊያ  በሚል ስበብ  የአብነት ተማሪዎቸን በትኖባቸው እጅግ መሪሪ ኅዘን  ያዘኑበት ወቅት ነበር።     ዛሬ  የሊቃውንቱ  መፍለቂያ የሆኑት የአብነት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን የልብ ትርታቸውን የሚያዳምጡ  አስተዳዳሪዎች  ቤተ ክርስተያናችን  ማግኘት  እየተሳናት ነው ፡፡ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን  ጠበቆችን  ለማፍራት የጉባኤ ቤቶችን  ማገዝ ግድ ነበር ፡፡ ይኸው እንደ አዘኑ ተጠሩ !ሊቀ ጠበብት መሠረትን ያንገላታችሁ አስከሬን ይዛችሁ ተማጸኑ!!      የቅኔ ምሥጢሩ  እንደ ወራጅ  ውኃ የሚፈስበት  በምግብ  የደለበን አእምሮ  ፍቀው የምሥጢር ጓዳ   እንዲሆን የሚያደርጉበት  የወረታ ደብረ ብስራት  ቅዱስ ገብርኤል  የቅኔ  ጉባኤ ቤት  ሰበካው አፈራርሶ ራቁቱን አስቀርቶት እኔም በአካል በመገኘት ችግሮችን ለመፍታት ሞክሬ ነበር። ሰሚ ግን አልተገኘም ነበር። መምህራን ማሳዘን  ግብረ መልሱ ከባድ ነው።     አንድ ወቅት ሊቀ ጠበብት መሠረት ዓለሙን ተማሪውን  ርኃቡ እንዴት አድርጎታል  የኔታ ስላቸው ሊቀጠበብት መሰረትን  “#በክረምት ተማሪውን የሚያስጨንቀው የሚመገበውን ማጣቱ ሳይሆን የማኀበር ቤታቸው መፍረሱ ነው” ነበር  ፡፡ እሱንም ተባብረን ማሠራት ችለን ነበር። በወቅቱ የነበሩት   ጉባኤ አባላት   አልተደሰቱም ነበር ።        ሊቀ ጠበብት መሰረት  እንዲህ አሉኝ “ተማሪ እንደራበው አይበላም ፤እንደጠማው  አይጠጣም ። በነገራችን ላይ ሊቀ ጠበብት  መሠረት ዓለሙ  ፍጹም የጸሎት ሰው ፤ከአፋቸው  መቼም ቢሆን ክፉ  ነገር የማይወጣቸው መጽሐፍ ከመመልከት  የማይቦዝኑ ታላቅ አባት ናቸው፡፡     በየቀኑ ውዳሴ ማርያምና ቅዳሴ ማርያም ጠዋትና ማታ  በአንድምታ፣ በዜማ፤  በንባብ ሳይጸልዩ  ምግብ አይቀምሱም ፡፡     መምህራቸው ከዚህ ዓለም ድካም ሲያርፉ ሊቀጠበብት መሠረት ዓለሙ ሰለመምህራቸው ቅኔ ሲቀኙ፡
አንጋፋው የቅኔና የመጽሐፍ #መምህር #ዐረፉ ! ታላቁ የቅኔ ሊቅ የኔታ ሊቀ ጠበብት መሠረት ዓለሙ ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ ዐርፈዋል። #ሊቀ ጠበብት #መሠረት መሠረት ገብረ ሕይወት መባል ሲገባቸው ፡በቀለም አባታቸው በታላቁ ሊቅ በሊቀ ኀሩያን ዓለሙ ዘቃጨና ኢየሱስ ስም ይጠሩ ነበር ፡፡ ሊቀጠበብት መሰረት ዓለሙ በተወለዱ በ፰ ዓመታቸው የቤተሰብ ከብቶችን እየጠበቁ ነበር ያደጉት ፡፡ ለ፲፰ ዓመታት ከልዩ ልዩ መምህራን በተማሪነት ሕይወት ቀለም እየሸመቱ ቆይተዋል፡፡የአባትነትን ውኃ ልክ የማይባቸው አባቴ ነበሩ። ከልዩ ልዩ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ውዳሴ ማርያም ፤ቅዳሴ ማርያም ዳዊትና ነገሥት በአንድምታ ተምረው አሰመስክረዋል፡፡ በስማዳ ወረዳ ውስጥ ኮሽ ቅዱስ ገብርኤል ከሚባል የገጠር ከተማ ለ፪ ዓመታት፤ ጋይንት ወረዳ ለ፰ ዓመታት፤ ስማዳ ወገዳ ጊዩርጊስ ለ፲፪ ዓመታት ፤ወረታ ደብረ ገነት በዓታ ለማርያም ለ፪ ዓመታት ፤ በወረታ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ለ ፳ ዓመታት በቅኔ መምህርነት በአጠቃላይ ለብዙ ዓመታት በቅኔ መምህርነት ብዙ ደቀ መዛሙርትን እና እጅግ ብዙ የቅኔ መምህራን አፍርተዋል። ሊቀ ጠበብት መሠረት ዓለሙ እንደ ሰማዕታት ወንበር ተክለው ባስተማሩበት ሁሉ መከራ ሲቀበሉ የኗሩ እውነተኛ መናኝ ናቸውተ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች ከሊቀጠበብት መሠረት ዓለሙ ተምረው በርካታ የቅኔ መምህራን ወንበር ዘርግተው እያስተማሩ ይገኛሉ ፡፡ ከሊቀጠበብት መሠረት ዓለሙ ተምረው በአዲስ አበባ ከተማም በልዩ ልዩ አድባራትና ገዳማት ወንበር ዘርግተው የሚያስተምሩ የቅኔ መምህራን አሉ ፡፡ ሊቀጠበብት መሠረት ዓለሙ በትምህርት አሰጣጣቸው ትጋት ሁሌ እደነቃለሁ። በተማሪ ቤት ሳሉ መጽሐፈ ነገሥትና መጽሐፈ ሳሙኤል፤ ውዳሴ ማርያም ፤ ቅዳሴ ማርያም ዳዊትና ነገሥት አንድምታ በእጃቸው ጽፈዋል፡፡ ከሐምሌ 5 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በወረታደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል በቅኔ መምህርነት በማገልገል ላይ ነበሩ ። የቤተ ክርስቲያናችን ሳይንስ ከሚሰጥባቸው የቅኔ ጉባኤ ቤቶች የወረታ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል የቅኔ ጉባኤ ቤት አንዱ ነበር ። በዘመናቸን አብያተ ክርስቲያናት በብሎኬት እየተገነቡ ነው፡፡ እነዚህን አብያተ ክርስቲያናት የሚያገለግሉ ሊቃውንት የሚፈልቁባቸው የአብነት ትምህርት ቤትች ግንባታ ግን ብዙ ትኩረት አልተሰጣቸውም ነበር ፡፡ ይባስ ብሎ የወረታ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ሰበካ ጉባኤ የሣር ጎጆዎችን ለዐፀደ ሕፃናት ማስፋፊያ በሚል ስበብ የአብነት ተማሪዎቸን በትኖባቸው እጅግ መሪሪ ኅዘን ያዘኑበት ወቅት ነበር። ዛሬ የሊቃውንቱ መፍለቂያ የሆኑት የአብነት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን የልብ ትርታቸውን የሚያዳምጡ አስተዳዳሪዎች ቤተ ክርስተያናችን ማግኘት እየተሳናት ነው ፡፡ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ጠበቆችን ለማፍራት የጉባኤ ቤቶችን ማገዝ ግድ ነበር ፡፡ ይኸው እንደ አዘኑ ተጠሩ !ሊቀ ጠበብት መሠረትን ያንገላታችሁ አስከሬን ይዛችሁ ተማጸኑ!! የቅኔ ምሥጢሩ እንደ ወራጅ ውኃ የሚፈስበት በምግብ የደለበን አእምሮ ፍቀው የምሥጢር ጓዳ እንዲሆን የሚያደርጉበት የወረታ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል የቅኔ ጉባኤ ቤት ሰበካው አፈራርሶ ራቁቱን አስቀርቶት እኔም በአካል በመገኘት ችግሮችን ለመፍታት ሞክሬ ነበር። ሰሚ ግን አልተገኘም ነበር። መምህራን ማሳዘን ግብረ መልሱ ከባድ ነው። አንድ ወቅት ሊቀ ጠበብት መሠረት ዓለሙን ተማሪውን ርኃቡ እንዴት አድርጎታል የኔታ ስላቸው ሊቀጠበብት መሰረትን “#በክረምት ተማሪውን የሚያስጨንቀው የሚመገበውን ማጣቱ ሳይሆን የማኀበር ቤታቸው መፍረሱ ነው” ነበር ፡፡ እሱንም ተባብረን ማሠራት ችለን ነበር። በወቅቱ የነበሩት ጉባኤ አባላት አልተደሰቱም ነበር ። ሊቀ ጠበብት መሰረት እንዲህ አሉኝ “ተማሪ እንደራበው አይበላም ፤እንደጠማው አይጠጣም ። በነገራችን ላይ ሊቀ ጠበብት መሠረት ዓለሙ ፍጹም የጸሎት ሰው ፤ከአፋቸው መቼም ቢሆን ክፉ ነገር የማይወጣቸው መጽሐፍ ከመመልከት የማይቦዝኑ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ በየቀኑ ውዳሴ ማርያምና ቅዳሴ ማርያም ጠዋትና ማታ በአንድምታ፣ በዜማ፤ በንባብ ሳይጸልዩ ምግብ አይቀምሱም ፡፡ መምህራቸው ከዚህ ዓለም ድካም ሲያርፉ ሊቀጠበብት መሠረት ዓለሙ ሰለመምህራቸው ቅኔ ሲቀኙ፡ " እንዴት አፈራ ለወፍ ቃጨና ኢየሱስ ዛፍ ሊቀ ኀሩያን ፍሬው በቀኝ በግራ ሲረግፍ "ብለው ነበር ። አሁን ግን አንጋፋው የቅኔ መምህር ተጠያቂው ሊቅ ዐረፉ ። ከመምህር ተመስገን ዘገየ የፌስ ቡክ ገጽ የተወሰደ

About