@mom2kind: ዘጠኝ ቁጥር ስምንት ቁጥርን በጥፊ መታው ስምንት ቁጥርም ለምን ትመታኛለህ ብሎ ሲጠይቀው ከኔ በታች ሰለሆንክ ብሎት እርፍ። ይሄን የሰማ 8 ቁጥር 7 ቁጥርን በጥፊ ይመተዋል ምን አደረኩኝ ቢለው ከኔ በታች ስለ ሆንክ ይለዋል ። ሰባትም በተራው ስድስትን ስድስትንም አምስትን፣አምስት አራትን ፣አራት ሶስትን፣ሶስት ሁለትን ፣ሁለት አንድን የበታቼ ነህ እያሉ ይመታቱ ጀመር ።ከሁለት ቁጥር የመመታት አደጋ የደረሰበት አንድ ቁጥር 0ን ሊመታ አሰበና ለምን በፍቅር አላሸንፈውም ብሎ ና ከጎኔ ቁም ቢለው 10 ሆኑና በልጠው እና ልቀው ተገኙ።ከፍቅር የማይገኝ ትርፍ የለም!! የሰው ልጅም እንድሁ ነው።በልቡ ፍቅር ከለለ ተራጋጭ አህያ ተናካሽ ውሻ ይሆናል። ፍቅር ከለለበት ምቾት ፍቅር ያለበት ብቸኝነት ይሻላል። የሰው ልጅ ብቸኛ የሚሆነው የፈጣሪ ፍቅር ሲርቀው ነው።ወዳጄ ሆይ በዙሪያህ ሰው ያጣህ ቀን ራስህን ወዳጅ የሌለው ብቸኛ ሰው አርገህ በፍፁም እንዳትጨነቅ ፤ ሰው ብቸኛ ነው የሚባለው ከሰው ሳይሆን ከእግዚአብሔር ሲርቅ ነውና ፤ ወዳጄ አንተ እንደ መፃጉ ሰው የለኝም ብለህ ተስፋ ቆርጠህ ይሆናል ግን አስተውል " አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም" ተብሎ ተፅፏል።ትናንት አጃቢ የበዛልህ ሰው ነበርክ ዛሬ ግን ብቻህን ቁመህ ይሆናል በዚህም ብዙ አትደነቅ ከክርስቶስ እጅ እንጀራ እና አሳ በበረከት ሲበሉ የነበሩ ሰዎች መች በመከራው ጊዜ በቀራንዮ አደባባይ ከርእሱ ጋር ቆሙ ታዲያ ሕይወት ለሰጣቸውና ምግበ ነብስ ምግበ ሥጋ ለሆነላቸው ለክርስቶስ ያልሆኑ ሰወች እንዴት ለእኔ አልሆኑም ብለህ ትገረማለህ ? አይንህን ገልጠህ ልብህን ከፍተህ አስተውል #ሰው ማለት ሸንበቆ ነው ከተደገፍከው ይሰበራል።ተሰብሮ እንኳ አይተውህም። ስለተደገፍከኝ ነው የተሰበርኩት ብሎ ስባሪውን አሹሎ ውስጥህ ድረስ ይወጋሀል ፤ እናም ወዳጄ በጆሮህ ሳይሆን በልብህ ስማኝ ዘመድ ወይም ታማኝ ጓደኛ ላይኖርህ ይችላል። ነገር ግን ከሁሉ በላይ ሆኖ ሁሉን የሚገዛ #አልፋና_ኦሜጋ ኋለኛው እና መጨረሻው እኔ ነኝ ያለው አንተን ከፍ አርጎ የሚሾምህ እግዚአብሔር ስላለህ ወዳጅ አዝማድ ስለማጣትህ በፍፁም እንዳትጨነቅ። ዮሴፍን ወንድሞቹ በግፍ ሸጠውት ወደ ግብፅ ሲወርድ ማንም ሰው አልነበረውም #እግዚአብሔር ግን በባዕድ ሀገር ገዥ አድርጎ ሾሞታል ። ባለንበት ዘመንም ዛሬም ድረስ በሰዎች ተንኮል ብዙዎች ይሸጣሉ ፣ ይገፋሉ ፣ ይሰደዳሉ። እግዚአብሔር ደግሞ በፍቅሩ ገዝቶ መገፋትህን ገፍቶ በምድሩ ይሰበስብሃል እናም ወዳጄ ጊዜን አይቶ የማይከዳ ዘመን የማይለውጠው ምንጊዜም ሰው ለሌላቸው ቀድሞ የሚደርስና ስላንተ ካንተና ከሰወች በላይ የሚጨነቅልህ የነብስህ ጌታ የሆነው ዘለአለማዊው እግዚአብሔር አለህና ስጋህን አይተው ለሚቀርቡህና ለሚርቁህ ስጋ ለባሽ ፈራሽ ሰወች ስለማጣትህ በጭራሽ የሰናፍጯን ቅንጣት ታክል ጭንቀት እንዳይገባህ።በሱ በፈጠረህ ብቻ የሰናፍጯን ቅንጣት ታክል እመን ያኔ ብቻህን ሆነህ እልፍ ትሆናለህና።ባይሆነ አንተ በየተኛውም ሁኔታ ውስጥ ሁን። ለህሌናህ እና ለፈጣሪህ ታመን። ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ ደግሞ ፍፁም በጎነት ነው አንተም ይህ አሁን ያነበብከው ከተመቸህ ሌሎች እንዲማሩበት ሸር አድርግላቸው። እግዚአብሔር ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋር ይስጠን አሜን🙏እግዚአብሔር ብርሃኔና-መድሃኒቴ ነው።

Zelalem Official
Zelalem Official
Open In TikTok:
Region: US
Saturday 21 September 2024 13:30:31 GMT
122816
6656
334
1736

Music

Download

Comments

enatna.lij
enatna lij :
Mnm tyake yelewm
2024-10-13 17:37:50
2
fikrebirhanu
Birhanu gone :
best advice for all human being
2024-10-19 10:31:02
1
melakugobena
Melaku :
May God bless you
2024-10-31 12:00:29
0
mellyhdt
Melon :
very true
2024-09-23 00:12:07
2
bitsemezpsp
faith wins :
thank u 🙏
2024-10-17 18:25:37
1
www.wollo.12
@.ashenefe 🇪🇹 !! :
thanks bor 🙏
2024-09-21 15:49:45
1
1tokkummaa86ffgf0
ኤሷ ነኝ የደራ ልጅ muslim girl👌☪️🕋 :
it'is wonderful
2024-10-03 04:34:31
1
aswabsayid
𝐄𝐦𝐮𝐞 𝒚𝒏𝒂𝒕𝒆𝒘𝒐𝒂✝️🙏 :
you are right bro🙏🥺
2024-09-21 19:45:23
2
user54163640368174
user5416364036817 Niguse Tadel :
thank you so much bro god bless you 🙏
2024-09-21 21:33:17
1
firaol.hana
𝐑𝐞𝐛𝐢𝐫𝐚𝐇𝐚𝐧𝐚@𝐟𝐢𝐫𝐚 :
exactly thanks alot God bless you.
2024-09-22 14:02:24
1
enderasieadmasu5
ቀዳማዊ እንደራሴ :
wow😍
2024-09-26 17:37:39
1
hiwat.yaqaxalal
hiwat ♥️ yanetuu nafeqii♥️🥰🥰 :
awnta new👌👌
2024-09-22 16:47:53
1
user806759610701halu
Ğèñì❤️💛🦋 :
ewnte new
2024-09-22 21:28:02
1
seni_mm
Seni_MM :
Ewnet new Enamesegnalen❤❤❤
2024-09-21 15:48:51
1
tinabeke2
user8962568797880 :
🙏🙏🫶🫶🥰🥰
2024-09-21 14:14:32
1
7905l
𝓶𝔂 𝓵𝓲𝓯𝓮-- 𝓵𝓲𝓷𝓮 🆉🦅 :
👌👌👌You are Right🥰🥰🥰🥰😎
2024-09-21 14:21:36
1
hiwotfantu4
love Ethiopian :
true ❤😭🙏
2024-09-22 20:45:27
1
user74826674786
user74826674786 :
right
2024-09-21 16:11:17
1
sas.004
☞ሳይለቷ 📵 ዱርዬ..✍ :
Yes 💔😭
2024-09-23 18:38:46
1
ketema1221
ketema :
thank you🥰🥰🥰
2024-09-21 20:04:33
1
atifieyenwdjie
i ሰው :
wow 🙏🙏🙏🙏🙏
2024-09-28 07:13:35
1
ggffl623
ይኹን ደሓን :
very🥺
2024-09-23 02:15:53
1
melatchani2
mom 1🥲 :
ewnte new
2024-09-21 13:45:47
1
debra.amado
Debra Amado :
popse Lokshne shop Suth afrika Limopopo 🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰 porosa Be fr🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖
2024-10-24 10:41:37
0
To see more videos from user @mom2kind, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About