@jerusalem446: + ሳምራዊቷ ሴት + ሳምራዊቷ ሴት ነኝ።የምጠራው በአገሬ እንጂ በግለሰብነቴ ስም የለኝም።ዜግነት የጨዋነት ሽልማት አይደለም ፤ ሁሉም ክርስቲያን ባይሆንም ሁለም ዜጋ መሆን ይችላል።ወገኖቼ ሳምራውያን ገፍተውኝ እርሷ ባጠለቀችበት ጉድጓድ እኛ አንቀዳም ብለው ተፀይፈውኝ በሰማርያ ቃጠሎ በቀትር እገሰግሳለሁ ፤ ፀሐይ ከሰው አፍ በላይ አያቃጥለኝም።ትንሹ ድሃ ትልቁን ድሃ ይንቃል ፤ ትንሹ ኃጢአተኛም ትልቁን ኃጢአተኛ ይጠላል።የጉድጓዱ አፍ በትልቅ ቋጥኝ የሚዘጋ ፤ በኀብረት ካልሆነ ብቻ የማይንከባለል ነው።እኔ ግን ብቻየን አንከባልለዋለሁ።ውኃው እየጎደለ ከጥልቅ መሙላት ተቸግሬአለሁ። በየዕለቱ በንቀት ፣ በቃጠሎ ፣ በጥልቀት እኖራለሁ።ጌታ ሆይ ጉድጓዱ ጥልቅ ነው ፣ ጥልቁ ሰው የቆፈረው ነውና።ቁሜም ተምበርክኬም የማልደርስበት ወደ ጉድጓዱ በግማሽ ገብቼ ጭላጭ የምሰፍርበት ጉድጓዱ ጥልቅ ነው። ተናገር ጌታዬ የቀትር ጓደኛዬ ፤ ሰው የዘረጋው የኑሮ መዋቅር ፣ ከጥልቁ የወጣው ጥልቅ ዘዴ ፣ ስደርስበት የሚርቀው ጥላው ኑሮዬን ተናገረው።ተናገረኝ ኤፍታህ በለኝ! ድካሙ ብዙ ፣ እርካታው ትንሽ የሆነውን ጉድጓድ አስጥለኝ።ካለሁበት ድረስ የመጣኸው አንተ ምንጭ ኢየሱስ ሆይ! ፍለቅ።ዓለት ኃይልህን በበትር ሲመቱህ ለእስራኤል የፈለቅህ አንተ የበረሃው እርካታ ዛሬ ፍለቅ።እንደገና ከሰው ጉድጓድ እንዳልመላለስ አንተ ብሩኽ ምንጭ በሆዴ ፍለቅ።የቀዱት ያልቃል ፤ የማታልቅ ምንጭ ሆይ! ዛሬ በነፍሴ ፍለቅ።ከጥያቄዬ በላይ መልስ የሆንከው የማትደፈርሰው ምንጭ ሆይ! ዛሬ በደረቀው ነገሬ ላይ ፍለቅ።ፍለቅ ፥ ፍለቅ ፥ ተፍለቅለቅ የደስታ ነዶ ፥ የብርሃን ጎርፍ ሆይ! ፍለቅ ፣ ከማለቅ የምታድን ፍለቅ ፣ ስስት የሌለብህ ወደ ራስህ የማታስቀር ሆይ! ፍለቅ ፣ የማትጨረስ ቸርነት ኢየሱስ ሆይ! ፍለቅ።ጉድጓዱ ጥልቅ ነው ፣ አንተ ግን ፍለቅ..........። " እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ፡ አላት። " (ዮሐንስ 4:14) 🙏 #እግዚአብሔር_ብርሃኔና_መድኀኒቴ_ነው #ኦርቶዶክስ⛪ተዋህዶ⛪ለዘለዓለም🙏ትኑር🙏 #orthodox
እየሩሳሌም ☦
Region: KW
Thursday 21 November 2024 19:50:46 GMT
Music
Download
Comments
Getahun Lema :
ለሳምራዊቷ ሴት የሠጣሀትን የህይወት ውሀ ለኔም ስጠኝ አምላኬ አሜን
2024-11-23 06:16:04
346
Konjit Getachew :
ለሳምራወቶ የገባህላትን የህይወት ውሃ ልኔም ስጠኝ
2024-11-22 10:24:42
154
sentayehu :
ለሳምራዊቶ የሰጠካትን የህይወት ውሀ ለኔም ስጠኝ ጌታ ሆይ🥰🥰😂
2024-11-23 13:41:12
2
𝐌𝐢𝐬𝐬 𝐥𝐨𝐯𝐞😜 :
እግዚአብሔርን ከሚያማርሩት ሰዎች ውስጥ አንዷ እኔ ነኝ ያደረገልኝን ማየት አቅቶኝ ለምን እኔ የምፈልገውን አታደርግልኝም ብዬ አማርረዋለው እርሱ ግን ታጋሽ ነውና እስከ ዛሬ ታገሰኝ አቤቱ ጌታዬ ሆይ ስለመተላለፊ ይቅር በለኝ አሜን 🙏
2024-12-20 06:30:03
5
senu :
እውነት ነው እሷን የተረዳ አምላክ እኛንም ይማረን ወደ ልቦናችን ይመልሰን
2024-12-15 06:16:48
28
eyoy neny :
le samirawit set yesexehat ye hiwot wuha lanem sixeny amlake amen
2024-12-13 10:07:25
13
user3191048293762 :
ለሣምራይቶ የደረሥክ ለኛም ደረሥልን ፈጣሪሆይ 🥰🥰🥰
2024-11-24 05:33:05
28
Teshe man :
አሜን
አሜን
አሜን
2024-11-22 16:43:29
10
To see more videos from user @jerusalem446, please go to the Tikwm
homepage.