@ebc_tiktok: የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የክዋኔ እና ሂሳብ ኦዲት ጉድለቶች እንደተገኙበት ተገለጸ ************* የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በ2015/2016 በጀት ዓመት የክዋኔ እና ሂሳብ ኦዲት ሲመረመር በርካታ ጉድለቶች እንደተገኙበት በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገልጿል። ቋሚ ኮሚቴው የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የ2015 /2016 በጀት ዓመት የፓስፖርት አገልግሎት አሰጣጥና ውጤታማነትን በተመለከተ የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት እንዲሁም የ2015 የሂሳብ ኦዲት ሪፖርት ላይ ተወያይቷል፡፡ የኢሚግሬሽን አሰራር ሥርዓትን ለማሻሻል ፖሊሲ አመንጭቶ ለሚመለከተው አካል በማቅረብ አጸድቆ ተግባራዊ ያላደረገ መሆኑን አንስቷል። ለፓስፖርት አገልግሎት የዜጎች ቻርተር ሰነድ አውጥቶ እየተከታተለ አለመሆኑ እንዲሁም የፓስፖርት አገልግሎት በምን ያክል ጊዜ ጥራትና መጠን መከናወን እንዳለበት ተለይቶ እንደማይታወቅ የኦዲት ሪፖርቱ አመላክቷል ብሏል ቋሚ ኮሚቴው፡፡ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ተቋማዊ መዋቅር በማጥናትና ለሚመለከተው አካል በማቅረብ በዋናውም ሆነ በቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሰው ኃይል እንዲሟላ አላደረገም ተብሏል፡፡ ተቋሙ ለሰራተኛው የስራ መዘርዝር አውጥቶ ማን ምን መስራት እንዳለበት አላመስቀመጡንም በኦዲት አረጋግጫለሁ ብሏል ቋሚ ኮሚቴው ፡፡ በዓለም አቀፍ የሲቪል አቬሽን ስታንዳርድ መሰረት ጥናት በማድረግ ተቋሙ የቡክሌት ፓስፖርትን ወደ ኢ-ፓስፖርት መቀየር የሚያስችል አሰራር ዘርግቶ ተግባራዊ አለማድረጉም ተነስቷል፡፡ ከድንበርና ከጎረቤት ሀገራት አጠራጣሪ ተገልጋዮች ሲያጋጥሙ ዜግነታቸውን የሚያጣራበት መመሪያ የሌለው መሆኑም ነው የተገለጸው። በተቋሙ የተገልጋዮች የአገልግሎት ስታንዳርድ አለማስቀመጡንና የኦንላይን መረጀዎችን አለማሻሻሉም በኦዲት ሪፖርቱ ተረጋግጧል ተብሏል፡፡ የፓስፖረት ቀነ ቀጠሮ ያለፈባቸውን ተገልጋዮችን የቅጣት ገንዘብ የሚሰበስብበት መንገድ ግልጽ አለማድረጉም እንዲሁ፡፡ የመንግስት የባንክ ሂሳብ ቁጥር የመክፈትና የመዝጋት ስልጣን የገንዘብ ሚኒስቴር ስልጣን ሆኖ ሳለ፣ ተቋሙ የባንክ ሂሳብ በግለሰቦች ስም ከፍቶ ገቢ የሚሰበስብ መሆኑን በኦዲት ሪፖርቱ አረጋግጫለሁ ብሏል ቋሚ ኮሚቴው። የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሺእመቤት ደምሴ (ዶ/ር) የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የክዋኔ እንዲሁም የ2015 የሂሳብ ኦዲት ሪፖርት ላይ ለመወያየት በተጠራው የቋሚ ኮሜቴው ስብሰባ ላይ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት አለመገኘታቸው አግባብ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡ ምክር ቤቱ ከ10 ቀን ቀደም ብሎ የስብሰባውን ቀን እንደሚያሳውቅ ጠቅሰው፤ ቋሚ ኮሚቴው በሚቆጣጠርበት ሰዓት ኃላፊነት የተሰጠው አካል ማብራሪያ አለመስጠቱ ተገቢ አለመሆኑን የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ተናግረዋል። የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጎሳ ደምሴ በምክር ቤቱ የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በተቋሙ ውስጥ ከዚህ በፊት ከ300 ሺህ በላይ የፓስፖርት አገልግሎት ጥያቄዎች እንደነበሩና በየቀኑ የሚቀርቡ በርካታ ፍላጎቶችን ምላሽ ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡ የቡክሌት ፓስፖርት አሰራርን ወደ ኢ-ፓስፖርት ለመቀየር በሂደት ላይ መሆናቸውን አንስተው በቀጣይ ጥር ወር ወደ ተግባር ሊገቡ እንደሚችሉ ተናግረዋል። እስካሁን ባለው ሂደት አጠራጣሪ ተገልጋዮችን ለመለየት በተቋሙ ኮሚቴና አመራር እየተወሰነ እየተለየ የሚሰራበት አግባብ መኖሩንም አንስተዋል፡፡ በተቋሙ ተገልጋዮችን የማስተናገድ አቅም ውስንነት፣ የአገልግሎት ስታንዳርድ አውጥቶ የፓስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችግር ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሺእመቤት ደምሴ (ዶ/ር) ከሂሳብ ኦዲት ግኝቶች ወዲያው ችግሮችን ለማስተካከል እና ወደፊት በስራ ውስጥ ለሚያጋጥሙ ስራዎች ትምህርት ለመውሰድ የሚያስችል ነው ብለዋል። በመሆኑም የዋና ኦዲተር በክትትላቸው እንዲሁም የቋሚ ኮሜቴው በመስክ ምልከታው የተስተካከሉ ጉዳዮችን ወደፊትም እንደሚያረጋግጥ ተናግረዋል። እስከ ጥር 30 ተቋሙ የወሰዳቸውን የእርምት እርምጃዎች በተመለከተ በሪፖርት ለቋሚ ኮሚቴው እንዲያሳውቁ አሳስበዋል። በመሐመድ ፊጣሞ #Ethiopia #ETV #EBC #EBCDOTSTREAM #ኢትዮጵያ #ebc #ኢቢሲ #ebcnews #ኢቲቪ #News #immigration

EBC News
EBC News
Open In TikTok:
Region: ET
Wednesday 27 November 2024 14:25:00 GMT
12196
266
7
12

Music

Download

Comments

user6249168188603
user6249168188603 :
ምን አባሽአገባሽ ትዉጣ
2024-11-28 02:55:02
1
mount600
Mount up :
ስለ ኑሮ ውድነት ዘገባ ስሩ
2024-11-27 14:45:54
1
mesaymatusalarike
mesaymatusalarike :
እች ሴትዬ የሰላማዊት ዳዊትን ስልጣን እንደፈለገች ወይም ቅናት አለባት ወይ ጉድ ተንጨረጨረች እኮ። ሰላማዊት ጎበዝ አመራር ናት።
2024-11-27 18:17:24
0
fasikaaklilu7
Fasika ፍሲካ :
ጠቅላይ ሚኒስትሩም እንደዚህ ግልፅና ፋተሀዊ ቢሆኑልን
2024-11-28 01:23:22
1
dannyky11111
Titan k :
😆 immigration is always the no 1 curropt office in the country. the minister left the country to escape accountability.
2024-11-27 15:36:03
2
ayimenayamn14
ayimenayamen :
ኦዲት ሲባል ይደነግጣሉ ሌቦች ናቸዋ ባሏም ባለስልጣን ስለሆነም ጭምር ነው ። ሁሉም በስራው መጠየቅ አለበት አንች ግን ጎበዝ ጀግና ነሽ ሀላፊነትን መወጣት እንደዚህ ነው።ሌሎችም ካንች ሊማሩ ይገባል።
2024-11-28 06:15:13
0
To see more videos from user @ebc_tiktok, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About