@hanafantu21ffg: ይሄ መፅሐፍ ይለይብኛል ...ሰርክ እንደ አዲስ ያናግረኛል። መፅሐፉን ካነበብኩት ሦስት አመት አልፎኛል ነገር ግን ገፀባህሪያቱ ለብዙ ግዜ አብረውኝ ዘልቀዋል። በተለይ "እንጃኔ" እና "አንዴና ዘላለሜ" ላይ ያለችው "መሴ ቀዌ "...የመፅሐፉን ከግማሽ በላይ ገፆች የያዘው "የባስሊቆስ እንባ" ላይ ያሉት ገፀባህርያት ለ'ኔ መልክ አላቸው ፊቴ ላይ ድቅን የሚል ጋሽ ሙሌ መኪናውን ሽረረረረረረረ ሲያረግ ...እትሁኔ የሆነች እንስፍስፋ ያለች ነፍስ የመኖር ትርጉሟን የተነጠቀች ምስኪን ነፍስ😢 የልጅነት ያላለቀ ፍቅር ውሎ አድሮ ኑሮን ሲያናጋ "እንዴት በዚህ ልክ?" ያስብላል። የልጅነት የማይጠገቡ ትዝታዎችን፣ የወጣትነት እልህን፣ አትንኩኝ ባይነትንና ወኔ ምን እንደሚመስል በደንብ አሳይታናለች ከመንገር በላይ ጉልምስና አለፍ ሲልም እርጅናን ክትት አርጋልናለች። በታሪኩ ውስጥ ከግለሰብ ችግር አንስታ የቤተሰብ ከዛም ከፍ ሲል እንደማህበረሰብ እንደ ሀገር የገጠሙንን ህመሞች ከገፀባህሪዎቹ ጋር አብረን እንድንታመም እንድንቆዝም ባስ ሲልም እንድናለቅስ ታደርገናለች። በመፅሐፏ ጎንደር አካባቢ ካሉ ትንንሽ ከተሞች ተነስታ አዲስ አበባ እስካሉ ሰፈሮች ትወስደናለች። ከሌሎቹ መፅሐፎች ለእኔ ለየት የሚልበት ብዙ ግዜ ሴቶች በገፀባህሪ ሲሳሉ እንስፍስፋ የዋህና ደካማ ተደርገው ነው። እዚህኛው የትዕግስት መፅሐፍ ላይ ግን የነበረንን የተንሸዋረረ እይታ በሆነ ያህል መልኩ ቀይራልኛለች ብዬ አስባለሁ በእኔ ንባብ። ገፀባህሪ መሳልን ተክናበታለች አተራረኳ የሚማርክ ቋንቋዎቹ ውብና ቀላል ናቸው። የማላውቃቸው የተወሰኑ ቃላቶች ነበሩበት ግን ከገለፃው የቃላቶቹን ፍቺ ለመረዳት ብዙም ከባድ አይደለም። ሌላም ሌላም ይደገመን ብለናል ትዕግሥታችን። #📚 #bookish #BookTok #books #bookrecommendations #bookreview
Hana Fantu D
Region: ET
Sunday 01 December 2024 07:19:55 GMT
Music
Download
Comments
@tesfanam :
wow
2024-12-17 07:28:13
0
Sharew1 :
ሶፍት ኮፒውን ምንላይ ላገኘው እችላለሁ ቆንጅት ??
2024-12-01 08:48:33
1
yonab309 :
መጽሀፍ ላይ ባትጽፊ
2024-12-02 08:38:31
4
Biniyam Birhanu :
የመጽሐፉ እርስ
2024-12-08 04:18:35
1
Ezra Yohannes :
ቆንጆ መፅሐፍ 💛💛💛
2024-12-01 15:39:07
2
Sam :
ጃፋር የመፅሀፋ መደብር ይገኛል መፅሀፋ
2024-12-02 15:30:29
1
Wondesen Tesfaye :
በጣን የወደድኩት🥰
2024-12-16 10:54:52
0
ያልታደልሽ እንዴት አደርሽ :
የደራሲ ቃላት ልብ ውስጥ ሚቀረው እውነትም የተሰማው እና ያለፈበት መንገድ ሲሆን ነው ።
2024-12-03 15:27:09
0
iyuel :
እናነባለና እንግዲህ 🤷♂️
2024-12-01 18:37:01
0
khaludi :
አውሺኝ Please
2024-12-01 18:35:16
0
Hendaka Mersha :
አንዳንዴ የሚፈላስፋት ነገር የማይገባኝ እኔ ብቻ ነኝ
2024-12-01 16:02:44
0
Hebi Tsion :
🥰🥰🥰🥰
2024-12-01 08:13:26
1
birukgizachew81 :
😂😂😂
2024-12-29 04:36:25
0
ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ :
🥰🥰🥰
2024-12-27 15:15:34
0
ab :
😎😎😎
2024-12-25 20:30:19
0
unstoppable :
😁😁😁
2024-12-13 18:49:36
0
Lilly samuale💝 :
🙏❤
2024-12-13 05:56:24
0
Vintage🤎 :
🥰
2024-12-11 16:07:22
0
Tinsu :
😳😳😳
2024-12-10 09:36:10
0
ESROME :
👍👍👍
2024-12-04 11:07:01
0
アボカドトースト :
🕡
2024-12-01 07:59:51
0
Dr Adu :
Tigist Tafere Mmolla🥰
2024-12-01 16:55:57
1
henok21p :
10q hsnye Letkomashna yemtgelchbet menged des ylal
2024-12-01 20:32:04
0
selam :
lemn endanchi andaltesemagn
2024-12-01 16:39:42
0
To see more videos from user @hanafantu21ffg, please go to the Tikwm
homepage.