@limitless_3principles: በድህነትና በውድቀት የታጠረውን ህይወቱን በስራ ፈጠራ ሰባብሮ ያለፈውና በዚህ ሰዓት ከ30 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት ሀብት እንዳለው የሚነገርለት ቻይናዊው ቢሊየነር “ጃክ ማ” እንዲህ ይላል፡- ‘’ገንዘብና ሙዝን ከዝንጀሮዎች ፊት ብታስቀምጥ ዝንጀሮዎች ሙዙን ይመርጣሉ። ምክንያቱም ገንዘብ ብዙ ሙዝ እንደሚገዛ አያውቁም! አብዛኛው ሰው ላይ ተመሳሳይ ሙከራ ብታደርጉና በአንድ የተወሰነ የግል ስራ (ቢዝነስ) እና በወር ደመወዝ መካከል ምርጫቸው ምን እንደሆነ ብትጠይቁ አብዛኛው ሰው ወርሃዊ ደመወዝ ያለው ስራን ይመርጣል። ምክንያቱም ትንሽም ቢሆን የግል ስራ (ቢዝነስ) ከወርሃዊ ደሞዝ የበለጠ ገቢ እንደሚያመጣ እና ህይወት የሚቀይረው ይህ እንደሆነ ስለማያውቁ ነው። ሰዎችን ለድህነት ከሚዳርጉት ነገሮች አንዱ ከግል ስራ (ቢዝነስ) የሚመጡትን እድሎች ማየት አለመቻላቸው ነው። ምክንያቱም በህይወት ዘመናቸው ሁሉ በትምህርት ቤቶች የሚማሩት ስራ ማለት ሁልጊዜ ለወርሃዊ ደመወዝ መስራት መሆኑን ነው። ለራሳቸው ከመስራት ይልቅ ለሌሎች መስራትን ብቸኛ አማራጭ እንደሆነ ተምረዋል! እውነት ነው የወር ደሞዝ ከድህነት ይጠብቅሃል። ነገር ግን ሀብትን እንዳታገኝ ያደርግሃል። በህይወቴ ከጠዋቱ 2 ሰአት እስከ 12 ሰአት የሚሰራ ተቀጣሪ ሰው ሀብታም ሆኖ አይቼ አላውቅም።’’ ------------------------------------------------------- አንተስ #ገደብ_የለሽ የሆነውን የአእምሮህን አቅም በመጠቀም ከዚህ ተመሳሳይ የሆነ የቅጥር ህይወት አዙሪት ለመውጣት ወይም ወደፊት ስራ ፈላጊ ሳይሆን ስራ ፈጣሪ መሆን ትሻለህ? እንግዲያውስ እነዚህን 👇👇 ሃሳቦች ምንጊዜም ደጋግመህ ለማስታወስ ሞክር :- 👉 መደበኛ ትምህርት ጥሩ የሚባል ተቀጣሪ ሰራተኛ ያደርግህ ይሆናል፤ ራስን ማስተማር ግን ከራስህ ባለፈ ለሌሎች የምትተርፍ ስራ ፈጣሪ ያደርግሃል!!! ስለዚህ የምንጊዜም ተማሪ (Lifelong learner) ሁን! 👉 የምትወደዉን ስራ ስራ ወይም ለመስራት ህልም ይኑርህ። አዳዲስ ክህሎቶችን ለመማር እራስህን አዘጋጅ፤ ሁሌም ለማሻሻል ጣር፤ ጎበዝ በሆንክበት ሙያ ከማንም የተሻልክ ሆነህ እንድትገኝ በየቀኑ አዳብረዉ። 👉 በህይወትህ ሊጠቅሙህ የሚችሉ ነገሮችን ብቻ አንብብ፡፡ ንባብን በቻልከዉ ቦታና ጊዜ ልማድ በማድረግ አእምሮህን መግበዉ፡፡ 👉 ለራስህ ህይወት ሃላፊነት ውሰድ! የምትነሳው በእራስህ ነው ፤ የምትወድቀው በእራስህ ነው ፤ የምታድገው በእራስህ ነው ፤ የኋሊት የምትጓዘው በእራስህ ነው። ለውድቀትህ የሚጠየቅ ሌላ አካል የለም። የትም ብትሆን ፣ ምንም ብትሰራ ያንተ ህይወት ሃላፊነት የእራስህ ብቻ ነው። ላለማደግህ፣ ላለመቀየርህ፣ ላለማወቅህ ...ካንተ ውጪ ሌላ ተጠያቂ አካል የለም። 👉 ካንተ ከተሻሉ ሰዎች ጋር አብረህ አሳልፍ። #አስታዉስ! የአእምሮህ_ብስለት የሚለካዉ አብረህ ብዙ ጊዜ ከምታሳልፋቸዉ አምስት ሰዎች የአስተሳሰብ ዉጤት ተደምሮ ነዉ። 👉 በእራስህ ታገል ፤ በእራስህ ተጣጣር ፤ ተፋለም ። በእራስህ ተማመን ፤ የሚመጣውን ተቀበል ፤ ያለፈው አልፏልና መጪውን ለማስተካከል ዛሬን በሚገባ ኑር። ቀጣዩን የህይወት ምዕራፍህን አስተካክለህ ፃፈው ፤ እርሱንም እመነው ፤ በነፃነት ፣ በልበሙሉነትም ተግብረው። 👉 በልዩነት አስብ! በተሻለ መንገድ አስብ ፤ የተሻለ ሃሳብ ሲኖርህ ብቻ ተመራጭ ትሆናለህ። በተለየ መንገድ አልም፣ በተለየ ሁኔታ ማለም ስትጀምር ብቻ የተለየ ነገር መፍጠር ትችላለህ። 👉 ትኩረትህን ሙሉ ለሙሉ መድረስ የምትፈልግበት፣ መገኘት የምትመኘው ቦታ ላይ አድርገው። 👉 ፉክክርህን ከሌሎች ጋር ሳይሆን ከትላንቱ ማንነትህ ጋር አድርግ! 👉 ሂደት በሚጠይቅ የረጅም ጊዜ ለውጥ ማመን አለብህ። እውነተኛ እርካታ እና ደስታ ያለው በመልፋትና በፅናት በሚገኝ ስኬት ውስጥ ነው። አቋራጭና ጥድፊያ የበዛበት ሰላም የሚነሳውን ህይወት ለሰነፎች ተውላቸው፤ የተሻለ ሰው የሚያደርግህ፣ የሚያስከብርህ የማይቆም ጥረትህ ነው! 👉 አስተውል! ዛሬህን ልክ እንደትላንትናህ ካሳለፈከው... የሚለወጡት አንተ ልትለውጣቸው የማትችላቸው ነገሮች ብቻ ናቸው! 👉 ክቡርና ድንቅ አድርጎ የፈጠረህ አምላክም የልብህን መሻት አይቶ ከጎንህ እንደሚቆም እመን። የምትፈልገውን ጠይቀው፣ ላደረገልህ ነገር ሁሉ አመስግነው! 👉 ማደግህን አታቁም! አጋጣሚዎችን መፍጠር ፣ የተለያዩ አማራጮችን መሞከር ፣ እራስን ማብቃት ፣ እራስን ማሳደግ ፣ ከፍ ማለት የየለት ተግባሩ የሆነ ሰው ሁሌም እድገቱ ይቀጥላል ፤ ነገዎቹ በሙሉ ከዛሬ የተሻሉ ይሆናሉ። 👉 ተደላድሎ የተቀመጠን ማንም አይረዳውም ፤ ተመቻችቶ የተኛውን ማንም አይቀሰቅሰውም ፤ እንዳልደላህ በመልፋት አሳይ ፤ እንዳልተመቸህም በመንቃት አሳይ የሚያግዝህ የሚረዳህም ፈጣሪ የእራሱን ድርሻ እንዲወጣ አግዘው!!! 👉 በአምላክህ እና #ገደብ_የለሽ አድርጎ በሰጠህ የአእምሮህ እምቅ አቅም እምነት ይኑርህ! ከፈጣሪህ ጋር የማትችለው፣ የማታሳካው፣ የማታገኘው፣ የማትኖረው ህልም የለም። የህይወትህን ህልም መኖር የምትችልበትን አስተሳሰብ፣ ተነሳሽነት እና መንገድ/ስልት ተምረህ እምቅ አቅምህን ለማውጣት ዝግጁ ነህ? ከሆነ ይህን #tiktok አካውንታችን #follow በማድረግ ቤተሰብ ሁን። መልእከእቱን አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ #like #repost #copylink #share ማድረግን አትርሱ 🙏 #ገደብ_የለሽ #Limitless #የእናንተገፅ #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #habeshatiktok🇪🇹 #ethiopian_tik_tok #fyp
Limitless/ገደብ የለሽ
Region: ET
Sunday 01 December 2024 17:14:00 GMT
Music
Download
Comments
kidan 🤗 :
ከቅጥር ስራ ለመውጣት እቅድ እያወጣው ነው ያገኘሁህ ወደ ኋላ እንዳል ብርታታ ስለሰጠኘኝ አመሰግናለው ሁላችንም መልካም ነገር ይግጠመን
2024-12-31 15:45:08
2
ekusingle❤ :
በሃሳቡ እስማማለው ግን መወጫ መንገዱን አለወቅም ፈጣሪ መንገዱን ያሳየኝ 🥺🥺
2024-12-04 09:45:41
15
yielayela zerawni :
ጥሩ እኔ ከሰው ቤት ሥራ የራሴ ይሻላል ብዪ እየለፍው ነው 5 አመት ሆነኝ ለውጡ ለኔ አልታይ ብሎኛል ክፍተት አለ
2024-12-15 15:25:23
1
Yetsion :
የመንግስት ስራ ለመልቀቅ ቋፍ ላይ ነኝ አስራ ስንት አመት ለውጥ የለም ግን የሆነ የሚጎትት ነገር አለው
2024-12-03 13:57:26
12
Zerihun Niguse የጫሊ በዳዳ ልጅ :
አመሰግናለው ይህ ሀሳብ በወሳኝ ሰአት አግኝቸዋለው። ከፍታ ከሌለው የደሞዝ ስራ ዛሬን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ አልፌ ነገየን ጥሩ ለማድረግ ወስኜ ጀምሪያለው። ተቀጥሮ መስራት በቃኝም ሰለቸኝም። በርታ ብላችሁ በጸሎታችሁ አስቡኝ(ሃ/ሚካኤል)
2024-12-08 11:21:01
1
@henok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 :
እውነት ነው ወንድሜ መንገዳችንን ምናረዝመው እኛው እራሳችን ነን
2024-12-02 14:28:36
12
@mula :
በጣም አመሰግናለሁ ትክክለኛ ድክመቴን አውቄበታለሁ
2024-12-03 04:50:31
5
#የተዋህዶ ልጅ❤ :
ጎበዝ ድንቅ ነው እንበል እና በራስህ ተነሳሽነት የራስህ ለመጀመር በመጀመሪያ እኮ ገንዘብ ያስፈልግሀል ከሌለህ እንዴት ትጀምረዋለህ እኔ አሁን ለምሳሌ የብዙ ሞያ ባለቤት ነኝ ግን ነገ ከነገ የራሴን እጀምራለሁ ስል ገንዘብ ሳላገኝ ቀርቶ ህልም ሆኖ ቀረብኝ ገባህ 🥰
2024-12-03 04:56:20
0
Aleme :
መስሪያ ቤቶችን ባዶ አድርጋቸው😂😂
2025-01-07 16:24:07
0
Ermiyas :
አሁን ባለሁበት ምን እንደሚሠመኝ ባላውቀውም ከቅጥር አዙሪት ለመውጣት ሳስብ ነው ይችን ምክር ያገኘዋት ቸሩ መዳኒያለም ይርዳን አሜን
2024-12-31 18:19:16
1
ኤርሚ :
በብልጽግና ዘመን ደሞዝተኛ መሆን በራሱ ድህነት ነው ያውም ቁምጥ ያለ።
2024-12-02 10:06:41
12
Lijalem Kastela :
እውነት ነው እኔም እሬሴ የሄድኩበትና ሰው የሆንኩበት ብሎም የከበርኩበት መንገድ ነው ሁሉም ሊከተለው ይገባል።
2024-12-03 15:46:45
2
bini :
ፈጣሪ ብልኽነት ከማስተዋል ጋር ላንተም ለኛም ይስጠን አሜን በሉ
2024-12-20 11:35:37
2
Aklilu tamiru :
በጣም አመሰግናለሁ ትክክለኛ ድክመቶች አውቄአለሁ
2024-12-03 17:53:47
3
hira bint eslam :
awo hulam yerasan lemsrat asbalew gn demo birr yasfelgal
2025-01-16 14:59:53
1
tema Ye Manchaw :
ያስማማኛል ቤተሰብ ከዚ በላይ ማብራሪያ አያስፈልግም
2024-12-26 16:14:17
1
ሐይለ ገብርኤል :
አሀሀሀ የኔን ህልም መርጬ ከሰራሁ ብዙ ሙዝ መግዛት እችላለሁ
2025-01-03 09:03:46
1
tesfamekonnen8 :
የሚገርም ሀሳብ ነዉ በተለይ ከፈጣሪህ ጋር ከሆነ ያለዉ
2024-12-02 08:55:15
6
Kalido :
አንደኛ እኔም 2 አመት ሆነኝ ታውቃለህ ለማኝ ፈላጊ ነው የሚያደርግህ ወላሂ የመንግስት ሰራተኛ በጣም ደባሪ ነገር ነው
2024-12-11 15:57:01
1
Bizuye Tefera :
በትክክል ፈቅ አይል እዛው መቀጠር
2024-12-10 08:11:56
1
አዲሱ ካሳዉ12 :
ፈጣሪ ዘመንህን ይባርከው።
ሚዲያ በዚህ ልክ ሲገኝ የህይወት ምግብ ይሆናል።
2024-12-11 17:01:07
1
tenaw :
የውነት ነው ወንድሜ ሁላችንም ያልተጻፈልን ህልም ነዉ እየኖርን ያለነው ልብ ያለው ልብ የበል????????
2024-12-03 19:38:18
2
Andebet Sisay :
በጣም እሚገርም ምክር, ትምህርት ነው አመሰግናለሁ
2024-12-02 18:09:25
5
𝔻𝕖𝕧𝕖.❤🌹 :
strong የሆኑ ሀሰቦች አሉት እኔ በበኩሉ ወድጀዋለሁ
2024-12-02 18:57:21
8
TgYemaryam :
አረ ለውጥም የለ ።ድህነትንም መላቀቅ የለ 4አመት ብድር ሠለቸኝ
2025-01-09 13:54:53
1
To see more videos from user @limitless_3principles, please go to the Tikwm
homepage.