@pazi1221: #መቅደሲቱ_ወደ_መቅደስ_ገባች "መቅደስ ዘይኬልልዋ ኪሩቤል እለ ስዑላን በስዕለ እግዚአብሔር" 👇ትርጉም "እግዚአብሔር የዓሳላቸው የሙሴ ኪሩቤል የጋረዷት ቤተ መቅደስ አንቺ ነሽ" እንዲል (ውዳሴ ማርያም ዘሰንበተ ክርስቲያን) " ኦ መቅደስ ዘኮነ ባቲ እግዚአብሔር ካህነ" 👇ትርጉም "እግዚአብሔር ያገለገለባት መቅደስ ወዮ እንደምን ያለች ናት?" እንዲል። (ሃይ.አበው ዘኤራቅሊስ ም ፵፰/48 ቁ ፲፯/17) 👉እንኳን እመቤታችን ወደ ቤተ መቅደስ ለገባችበት በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ!!! ✝️እነሆ መጻሕፍት እንደነገሩን ታሪክ እንደሚያስረዳን በታህሣሥ ሦስት ቀን አማናዊት መቅደስ ድንግል ማርያም ወደ ኦሪታዊት መቅደስ የገባችበት ቀን ነው። "መቅደሰ ኦሪት ዘቦዕኪ ማርያም እምነ ወእሙ ለእግዚእነ በሕፅነ ሐና ተማኅፀነ ፈንዊዮ ለፋኑኤል ይዕቀብ ኪያነ በረምኃ መስቀል ረጊዞ ሰይጣነ 👇ትርጉም፦ ወደ ኦሪት መቅደስ የገባሽ የጌታችን እናቱ እናታችን ማርያም ሆይ አንቺን በታቀፈ በሐና ጭን ተማፅነናል፤ ሰይጣንን በመስቀል ጦር ወግቶ እኛን ይጠብቀን ዘንድ ፋኑኤልን ላኪልን" እንዲል። (ነግሥ ዘማኅሌት) "ዘበሠለስቱ ዓም እንዘ ትጠቡ ሐሊበ እማ ቅድስት ሐና አብእዋ ዮም ቤተ መቅደስ ወበህየ ነበረት በቅድስና" 👇ትርጉም "በሦስት ዓመት የእናቷን የቅድስት ሐናን ጡት እየጠባች ዛሬ ወደ ቤተ መቅደስ አስገቧት በዚያም በቅድስና ኖረች" እንዲል። (ነግሥ ዘበአታ) ✅ ጥንተ ነገሩም እንዲህ ነው ከነገደ ይሁዳ የተወለደ ደግ ሰው ኢያቄም የሚባል እና ከነገደ ሌዊ የተወለደች ቅድስት ሴት ሐና የምትባል ባልና ሚስት ነበሩ። እኒህም ባልና ሚስት እግዚአብሔርን በፍጹም ልባቸው የሚወዱና የሚያመልኩ ሥርዓተ ኦሪትን በአግባቡ የሚፈጽሙ አስራቱን ፣ በኵራቱን እና ቀዳምያቱን የሚያወጡ ሕገ ኦሪትን ወደ እግራም ወደ ቀኝም ሳይሉ የሚጠብቁ ነበሩ። ነገር ግን መካኖች ስለሆኑ ልጅ አልነበራቸውም። በዚህም የተነሣ ሲያዝኑ ሲተክዙ ይኖሩ ነበር። እግዚአብሔርም ጸሎታቸውንና ስእለታቸውን ሰምቶ ከፍጡራን ሁሉ በላይ የከበረች "ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና - በድንግልና የጸናች ንጽሕት ናት ነውር ነቀፋ የለባትም" ተብሎ የተነገረላት ጥዕምተ ስም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በብሥራተ መልአክ ነሐሴ ፯ ቀን ተጸንሳ ግንቦት ፩ ቀን ወለዱ። ✔️ሦስት ዓመት በእናት በአባቷ ቤት ከቆየች በኋላ እናት አባቷ ደጋግ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ነበሩና በብዙ ልመና እና ስእለት የተወለደች ልጃቸውን ስእለታቸውን ለመፈጸም "ይቺ ብላቴና አፏ እህል ሳይለምድ ልቧ ዘመድ ሳይወድ ወስደን ለቤተ እግዚአብሔር እንስጥ ብለው ወስደው ወደ ቤተ መቅደስ አስገብተዋታል። ✔️ወደ ቤተ መቅደስ ባስገቧትም ጊዜ ካህናቱ የምግቧን ነገር እንዴት እናድርግ እያሉ ሲመካከሩ መልአኩ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ ይዞ መጥቶ ረቦ ታያቸው በዚህ ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ ሌሎችም ካህናት ለእነሱ የመጣ በረከት መስሏቸው ለመቀበል ቢነሡ ወደ ላይ እራቀባቸው ሐና እና ኢያቄምም ሊቀበሉ ቢነሱ ወደላይ እራቀባቸው። ያን ጊዜ ዘካርያስ ሐናን "ሐና! ምናልባት ለዚች ብላቴና የወረደ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ አናውቅምና ትተሻት ፈቀቅ በይ እስኪ" አላት። ትታት ፈቀቅ ብትል ድንኩል ድንኩል እያለች እናቷን ስትከተል መልአኩ ፋኑኤል ፈጥኖ ወርዶ እመቤቴ ሆይ መንገድ ባስመታሁሽ ይቅርታ አድርጊልኝ ብሎ "በቆመ ብእሲ" ይላል የሰው ቁመት ያህል ከፍ አድርጎ አንድ ክንፉን ጋርዶ አንድ ክንፉን አጎናጽፎ ሰማያዊ ኅብስትና ሰማያዊ ጽዋዕ መግቧት አረገ። " ኦ ድንግል አኮ ኅብስተ ምድራዌ ዘተሴሰይኪ አላ ኅብስተ ሰማያዌ እምሰማየ ሰማያት ዘበሰለ ኦ ድንግል አኮ ስቴ ምድራዌ ዘሰተይኪ አላ ስቴ ሰማያዌ እምሰማየ ሰማያት ዘተቅድሐ -ትርጉም" 👇ትርጉም " ድንግል ሆይ ከሰማየ ሰማያት የተገኘ ሰማያዊ ኅብስትን ተመገብሽ እንጂ ምድራዊ ኅብስትን አይደለም፤ ድንግል ሆይ ከሰማየ ሰማያት የተገኘ ሰማያዊ መጠጥን ጠጣሽ እንጂ ምድራዊ መጠጥን አይደለም " እንዲል። (ቅዳሴ ማርያም) የምግቧማ ነገር ከተያዘልን ብለው ካህናቱ ወደ ቤተ መቅደስ አስገብተዋታል። መላእክት፦ "ብጽዕት አንቲ ውድስት አንቲ = ብጽዕት ነሽ የተመሰገንሽ ነሽ" እያሉ ያመሰግኗት ነበር። " ከመዝ ነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ወመላእክት ያመጽኡ ወትረ ሲሳየኪ ከመዝ ነበርኪ አሠርተ ወክልኤተ ዓመተ እንዘ ትትናዘዚ እምኀበ መላእክት ስቴኪኒ ስቴ ሕይወት ውእቱ ወመብልዕኪኒ ኅብስት ሰማያዊ" 👇 ትርጉም በቤተ መቅደስ እንዲህ ኖርሽ መላእክትም ዘወትር ምግብሽን ያመጡልሽ ነበር፤ በመላእክት እየተመሰገንሽ አስራ ሁለት ዓመት እንዲህ ኖርሽ፤ መጠጥሽም የሕይወት መጠጥ ነበር ምግብሽም ሰማያዊ ኅብስት ነበር" እንዲል። (አንቀጸ ብርሃን) ✅እንዲህ በንጽሕና በቅድስና በድንግልና አጊጣ ብትገኝ ጌታችንን ለመውለድ በቃች። “ኦ ድንግል አኮ በተላህዮ ዘልሕቂ ከመ አዋልደ ዕብራውያን እለ ያገዝፋ ክሣዶን አላ በቅድስና ወበንጽሕ ውስተ ቤተ መቅደስ ነበር” 👇ትርጉም "ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ በፈዛዛ ያደግሽ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ" እንዲል። (ቅዳሴ ማርያም ) 🕎ከዚህ ቀጥሎ መጽሐፍ ቅዱስን መነሻ በማድረግ ሊቃውንት የተናገሩትን በአጭሩ እናያለን። ✝️ከቀድሞ ጀምሮ ንጽሕት ስለመሆኗ። ✔️"ማርያምሰ ተሐቱ እምትካት ውስተ ከርሱ ለአዳም ከመ ባሕርይ ፀዓዳ" 👇ትርጉም ማርያምስ ከቀድሞ ጀምሮ እንደ ነጭ ዕንቍ በአዳም ሆድ ታበራ ነበር" (ድጓ ዘማርያም) "ኵለንታኪ ሠናይት እንተ ኀቤየ አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ በላዕሌኪ" 👇ትርጉም ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው ምንም ምን ነውር የለብሽም"/መሐ ፬፥፯/። ✝️ዘለዓለማዊት ድንግል ስለመሆኗ። ✔️" ወትረ ድንግል ማርያም ወትረ ድንግል ማርያም ወትረ ድንግል ማርያም" 👇ትርጉም " እመቤታችን ለዘለዓለም ድንግል ናት እመቤታችን ለዘለዓለም ድንግል ናት እመቤታችን ለዘለዓለም ድንግል ናት" እኔዲል። (ቅዳሴ ዘባስልዮስ) "ወደ ምሥራቅም ወደሚመለከተው በስተውጭ ወደ አለው ወደ መቅደሱ በር መለሰኝ ተዘግቶም ነበር። እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ "ይህች በር ተዘግታ ትኖራለች እንጂ አትከፈትም ሰውም አይገባባትም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶባታልና ተዘግታ ትኖራለች" እንዲል/ሕዝ፵፬፥፩-፪/። ✝️መላእክት እንደሚያመሰግኗት። ✔️"መላእክት በልሳነ እሳት ይሴብሑኪ መላእክት በአክናፈ ብርሃን ይኬልሉኪ ማርያም እምነ ወእሙ ለእግዚእነ መላእክት በቀለመ ወርቅ ይጽሕፉ ውዳሴኪ #የኢትዮጵያ_💚💛❤ኦርቶዶክስ_💚💛❤ተዋህዶ_💚💛❤ቤተክርስቲያን #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ፀንታ_ለዘለዓለም_ትኑር✝️ #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ፀንታ_ለዘለዓለም_ትኑር✝️

ጳዝዮን ዝክረ ቅዱሳን☦️🦅
ጳዝዮን ዝክረ ቅዱሳን☦️🦅
Open In TikTok:
Region: LB
Wednesday 11 December 2024 15:06:39 GMT
46331
7822
92
591

Music

Download

Comments

max259774
max :
Amen amen amen marry marry marry marry marry marry marry marry marry marry marry marry marry marry
2024-12-14 10:19:54
10
marakiye17
Maraki👑💌✍️ :
🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️Amene Amen Amen🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2025-01-08 23:46:09
4
abiadi50
abiadi50 :
Ameeeeeennnnnnnn❤❤❤❤❤
2024-12-18 01:51:03
1
user482584538378
b :
Amin ❤️❤️❤️❤️❤️❤️
2024-12-20 13:17:32
0
user7516094416086
በክርስቶስ ክርስቲያን :
ዜማው መልክአ ምንድነው በማርያም ?🥺
2024-12-11 16:56:19
8
raraman49
raraman :
ይህ መዝሙር የት ላገኘው እችላለሁኝ እባካቹሁኝ ኣትለፉኝ ንገሩኝ
2024-12-20 21:47:18
2
guaztote
nigisttessema :
አሜን። አሜን አሜን
2024-12-19 12:41:47
3
user8778759596353
Abebech :
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር
2025-01-08 19:00:06
1
To see more videos from user @pazi1221, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About