@eyob_12_: #ኢዮብ_ዘ_ሚካኤል ... የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በስፋት ወንጌልን የሰበከችውና ብዙ ተከታዮች ያገኘችው በአራተኛው ክፍለዘመን ጀምሮ ቢሆንም ክርስትና ግን ወደ ሀገራችን የገባው በኢትዮጵያዊው ጃንደረባው እንደሆነ ታስተምራለች። ይህ አስተምህሮ የቤተክርስቲያንን ታሪክ በሰፊው በጻፈው በአውሳብዮስ ዘቂሳርያም ተነግሮ እናገኘዋለን- "...የመድሃኒታችን ወንጌል ስብከትም በየቀኑ እየገፋ ሲሄድ የኢትዮጵያ ንግስት መኮንን የሆነ ሰው (ወደ ኢየሩሳሌም) መጣ።...እርሱም የእግዚአብሔርን ቃል ከፊልጶስ በመቀበል ከአህዛብ ውስጥ የመጀመሪያው ሆኗል።የመጀመሪያው አማኝ በመሆኑም ወደ ሀገሩ (ኢትዮጵያ) ሲመለስ የእግዚአብሔርን ቃል እንደሰበከና የአዳኛችንን ህይወት ሰጪ ትምህርት እንዳስፋፋ ይነገራል። ስለዚህም በእርሱ ምክንያት ይህ ትንቢት ፍጻሜውን አገኘ "ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።"...[1] የምስራቅ ስነመለኮት ፕሮፌሰር አንድሪው ሎዝ ይህ የአውሳብዮስ መጽሀፍ ከ 313AD አካባቢ ጀምሮ መጻፍ እንደጀመረና በ 324AD እንደተጠናቀቀ ያምናሉ።...[2] ይሄ ማለት አቡነ ፍሬምናጦስ ጵጵስናን ተቀብለው ከግብጽ ከመመለሳቸው (328AD) በፊት ነው መጽሀፉ የተጻፈው ማለት ነው። ከዚህ የተወሰኑ ነጥቦች እናገኛለን- 1) ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ወደ ሀገሩ ተመልሶ ክርስትናን አስፋፋ የሚለው አስተምህሮ ከአራተኛው ክፍለዘመን በኋላ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የተፈበረከ ሊሆን አይችልም።(አውሳብዮስ ሳይቀር በአራተኛው ክፍለዘመን ይሄንን ትውፊት ያውቀው ስለነበር) 2) አስተምህሮው ከአራተኛው ክፍለዘመን በፊትም ቢሆን በኢትዮጵያ ክርስቲያኖች የተፈበረከ ሊሆን አይችልም።(የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ትንሽ ቁጥር ትውፊቱን ያን ያህል ሀይል መስጠት የማይችል በመሆኑ እስከ አውሳብዮስ ሊደርስ አይችልም ነበርና) 3) ይህ አስተምህሮ በአውሳብዮስ ብቻ ሳይሆን በሄሬኔዎስና አርጌንስ በመሳሰሉ አባቶች ጭምር መጠቀሱ ትውፊቱ ከኢትዮጵያ ውጪ ባሉ ክርስቲያኖችም ተቀባይነት እንደነበረው ያሳያል።...[3] ...ከሁሉ በላይ በምትሆን ሃዋርያት በሰሯት በአንዲት ክብርት ቤተክርስቲያን እናምናለን... [1] Eusebius , Church history , Book 2 chapter 1. [2] Andrew Louth , The date Of Eusebius' Historia Eccelesiastica , page 41. [3] Ireaneus , Against heresies , Book 3 chapter 12 @eyobzmikael12 @eyobzmikael12 @eyobzmikael12
ኢዮብ-ዘ-ሚካኤል
Region: ET
Friday 20 December 2024 19:26:42 GMT
Music
Download
Comments
akli dekor :
amen amen amen 🙏🏿🙏🏾
2024-12-22 09:26:22
0
Tasfe :
AMEN❤❤❤
2024-12-24 14:05:28
0
ተሙ ዘተዋህዶ :
አህዛብ አልነበርንም ህዝብ እንጂ ምክነያቱም ህገ ኦሪትን የተቀበልን በመሆናችን።🙏🙏🙏
2024-12-21 09:25:11
18
Fasika@Dani :
ቃለ ህይወት ያሰማልን ኢዮባ🙏
2024-12-20 19:32:44
20
markeshaw_7 :
አህዛብ ነበርን የሚለውን ስሕተት ነው ። ምክንያቱም በሕገ ልቦና ፣ በሕገ ኦሪት እና በሕገ ወንጌል እግዚአብሔርን የምታመልክ ሀገር አህዛብ ነበረች ማለት ተቀባይነት የለውም ።
2024-12-20 22:28:39
8
meseret_27 :
ቃለ ህይወት ያሰማልን ኢዮባ🙏🙏🙏
2024-12-20 20:16:50
6
✝️ደቀ መዝሙርህ ነኝ✝️⛪️⛪️ :
እባካችሁ ሰው ከመሰረተው ድርጅት ውጡና የክርስቶስን ቤተክርስቲያን ፈልጉ🙏🥰
2024-12-20 20:19:31
4
Hibestish :
ቃለ ህይወትን ያሰማልን🥰
2024-12-21 06:59:20
3
serdinos internation :
ጃንደረባው ቅዱስ ባኮስ ይባላል🥰🥰🥰
2024-12-21 05:32:42
3
Addis (dagi) :
ቃለ ህይወት ያሰማልን
2024-12-20 21:43:38
3
mele :
ቃለህይወት ያሰማልን🙏🙏
2024-12-21 14:50:44
2
እርስቱ ፣ዘ-ተዋህዶ-፩፮ :
ቃለ ህይወት ያሰማልን 🥰🥰🥰🥰🥰
2024-12-21 12:28:15
2
dr.simry :
eyoba thanks🤩
2024-12-20 20:55:57
2
ネコ系 :
ቃልህይወት ያሰማልን እዮባ 💞
2024-12-20 20:20:53
2
Henok :
እዩ ቃለ ህይወት ያሰማልን 💙💙🥰🙏🙏🙏
2024-12-20 19:45:55
2
@mahlet mesfin :
የሕይወት ቃል ያሰማልን 🥰
2024-12-20 19:35:05
2
አቤት የሰው ልጅ🙏 :
አሜን 🥰🥰🥰🥰❤🤗
2024-12-22 05:16:24
1
Amele 19 :
አሜን ቃለህወት ያሰማልን🥰🥰🥰
2024-12-21 10:00:21
1
bubuye 1221 :
kalehiwot yasemalin 🥰🥰🥰🥰
2024-12-21 06:59:28
1
El_deah :
ቃለህይወት ያሰማልን🥰🥰🥰🥰
2024-12-21 04:30:07
1
Mahi ✝️ የክርስቶስ እስረኛ 🔐 :
ቃለ ሕይወት ያሰማልን 🥰🥰🥰
2024-12-20 23:04:11
1
ዳናት :
አንዲት ቤተክርስትያን 💖
ቃለሕይወት ያሰማልን ኢዮባዬ🥰
2024-12-20 20:36:02
1
helita 12 :
ይብቃት ለሊቱ ይውጣላት ፀሀይ
አሁን ይዘርጋ እጅህ ከ ሰማይ🙏🙏🙏
2024-12-20 19:54:08
1
@ጌርሳም ጌርሳም### :
አሜን ኢትዮጵያ ሳላምሽ ይብዛ🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️@
2025-03-06 22:16:28
0
ሳባ የጀግናው የናሆሜ እህትነኝአማራነቴ ውበቴነው :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰አሜን 3ማራት አገሬን ሰላምሽ ይመለስ አገሬ🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2025-03-06 13:46:53
0
To see more videos from user @eyob_12_, please go to the Tikwm
homepage.