@yas_seid: 💔መጅኑኑ ለይላ 💔 ====================               ለይላ እና ቀይስ              ------------           እዉነተኛ የፍቅር ታሪክ ❤️                 ክፍል #3 የልጅነት ፍቅራቸዉ ለይላ ላይ ተዳፍኖ እሱ ላይ ብቻ እንደተጋጋለ ተሰማዉ በለይላ አለመወደድ በለይላ አለመፈለግ አይነት ስሜት ተሰማዉ ሰርክ አይኑ እንባ አቀረረ ፣ ልቡ ተሰብሮ ቀዘቀዘ ገፁ ፈዞ ደበዘዘ ፣ ሙሉ አለሙ ተቃወሰ በዚህ ምክንያት መጅኑን ተሰኘ። ነገር ግን ያኔ ለይላም ከመጅኑን ያላነሰ የፍቅር እሳት እየበላት ማንም እንዳያዉቅና እንዳይሰማት በዉስጧ ቀብራዋለች የማትተነፍሰዉ የሚያቃጥል ረመጥ ሆኖባት ሁሉንም ስሜቷን በሽሽግ እንደተፀነሰ ልጅ በሆዷ አርግዛ ሚስጥራቸዉን ደግሞም ከልቧ ማጀት ደብቃዋለች ለይላ ምንም እንኳን ለመጅኑን ግድ እንደሌላት ብትገፋዉም ስለሱ የሚሰማት ውስጣዊ ፍቅር ናፍቆቷን ፤ መሻቷን ፣ መዉደዷን አፍ አዉጥቶ ይናገራል። ወጣትነቷ ከመጅኑኑ ደረት ላይ ሊጥል ይገፋፋታል ከዉስጧ የሚልጣት የግጥም ዘር ቀይስ ቀይስ እያስባለ ሊያስለፈልፋት ይዳዳዋል ግን አትፈቅድለትም ግን ደግሞ በሌላ በኩል በሷ እጦት ወደ እብደት ጎዳና ዳዴ የሚል የነፍሷ ሰዉ አለ ታድያ ለምን ደበቀችዉ ? ከምድር እንብርቷ መካ በስተ ደቡብ አቅጣጫ የምትዋሰን የነጅድ ገጠራማ ከተማእንደወትሮዉ ደንገዝገዝ ብላ ቀኗን እየገፋች ነዉ። ጊዜዉ ገና ልጅ ቢሆንም ፀሀይዋ ግን ጠንክራለች ። የነጅድ ሻኢሮች ከፀሀዩ ለመከላከል በየበረንዳዉ እና በየተምሩ ዛፍ ተጠልለዉ የተለመደዉን የግጥም እንካሰላንቲያቸዉን ማዶ ማዶ ሁነዉ ይወራወራሉ። ክፍት ጀለቢያ ሰፋ ካለ ነጭ ሱሪ ጋር ለብሶ ጥቁር ጫማ የተጫማ ሸጋ ወጣት "ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን እናንተ የዕብር ጌቶች" እያለ በመሀላቸዉ አልፎ ከአደባባዩ ሚንበር ላይ ቆመ ከላይ የቆመውን ገጣሚ ለማዳመጥ በአንድ ጊዜ ጠባቧ የነጅድ አደባባይ በሰዉ ጎርፍ ተዋጠች... ይቀጥላል... #mejnun #mejnunleyla

Someone
Someone
Open In TikTok:
Region: ET
Tuesday 14 January 2025 05:02:43 GMT
6413
195
5
67

Music

Download

Comments

abdure_ak22
Abdure🐐 :
🥰ደጋግሜ እኮ ነው ማነበው ቀይስ ከርታታው😥
2025-01-14 05:07:09
5
kalid.werebabo
💞💝👉Kነኝ ተስፈኛው👈💞 :
መጅኑኑ ለይላ የት ነው እማገኘው
2026-06-08 06:45:07
1
mita172017
Haniza :
❤️
2025-11-27 12:32:16
0
usersebri1
sebri✌️ :
👌
2025-12-20 11:36:20
0
To see more videos from user @yas_seid, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About