@bahirdarbiketour1: #creatorsearchinsights #በዘመነ ሥጋዌ በናዝሬት ከተማ፤ ዮርዳኖስ ወንዝ የእስራኤል ሕዝብ በመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እጅ ለመጠመቅ ተራ ይዘው በሚጠብቁበት ጊዜ እርሱ እንዲህ እያለ ይሰብክ ነበር፤ ‹‹እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው መቅሠፍት ታመልጡ ዘንድ ማን ነገራችሁ? እንግዲህ ለንስሓ የሚያበቃችሁን ሥራ ሥሩ፤ አብርሃም አባታችን አለን በማለት የምታመልጡ አይምሰላችሁ፤ እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች የአብርሃም ልጆችን ማንሣት እንደሚችል እነግራችኋለሁ፡፡ እነሆ፥ ምሳር በዛፎች ላይ ተቃጥቶአል፤ መልካም ፍሬ የማያፈራውን ዛፍ ሁሉ ይቈርጡታል፤ ወደ እሳትም ይጥሉታል፡፡›› (ሉቃ.፫፥፯-፱) ሕዝቡም ምን ቢያደርጉ እንደሚሻል በተራ በተራ ይጠይቁት ጀመር፤ እርሱም ለእያንዳንዱ ሲመልስ፤ ሁለት ልብስ ያለው አንዱን ለሌለው እንዲሰጥ፣ ለተራበ እንዲያበላ፣ ቀራጮችን ደግሞ ከታዘዙት አትርፈው አንዳይውስዱ እንዲሁም ጭፍሮችን በማንም ላይ ግፍ እንዳይፈጽሙ እየመከረ አጠመቃቸው፡፡ እነርሱም በልባቸው እጅግ እያደነቁ ከጌታችን ኢየሱስ ጋር መሰሉት፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ግን እንዲህ አላቸው ‹‹እኔ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ግን የሚበልጠኝ የጫማውን ማሰሪያ እንኳን ልፈታለት የማይገባኝ ይመጣል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ፣ በእሳትም ያጠምቃችኋል፡፡›› (ሉቃ.፫፥፲፮-፲፯) ሕዝቡ ሁሉም ከተጠመቁ በኋላ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ ገብቶ ሊጠመቅ ወደ እርሱ ሲጠጋ ቅዱስ ዮሐንስ ግን ‹‹እኔ በአንተ ልጠመቅ እሻለሁ፤ አንተ ወደ እኔ ትመጣለህን?›› በማለት ከለከለው፡፡ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ አሁንስ ተው፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናልና›› አለው፡፡ እርሱም ተወው፤ ጌታችን ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያውኑ ከውኃ ወጣ፤ በዚይች ቅጽበትም ሰማይም ተከፈተ፤ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ ሲቀመጥ አየ፡፡ እነሆም በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይህ ነው የሚል ድምጽ ከሰማይ መጣ፡፡›› (ማቴ.፫፥፲፫-፲፯)
Bahir Dar Bike Tours
Region: ET
Friday 17 January 2025 15:06:00 GMT
Music
Download
Comments
There are no more comments for this video.
To see more videos from user @bahirdarbiketour1, please go to the Tikwm
homepage.