@musab.tiktok2024: "ህጋዊ ካርታ ያለው መስጂድ በ5 ቀናት ውስጥ እንዲፈርስ ትዕዛዝ ተሰጥቶብናል!" - የለገጣፎ ለገዳዲ መጅሊስና የሱመያ መስጂድ ኮሚቴዎች በሸገር ከተማ በለገጣፎ ለገዳዲ ክፍለከተማ ህጋዊ ካርታ ያለው ሱመያ መስጂድ በፍርድ ቤት እንዲነሳ ያለአግባብ ውሳኔ መሰጠቱን አስመልክቶ ሀሩን ሚድያ ህዳር 19/2017 ዓ.ል በቦታው በመገኘት ዘገባ መስራታችን ይታወሳል። አሁንስ የመስጂዱ ጉዳይ ከምን ደረሰ ብለን የሱመያ መስጂድ ኮሚቴዎችን እና የለገጣፎ ለገዳዲ ክፍለከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጠይቀናል። ኮሚቴዎቹ በሰጡን ምላሽ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ በፍርድ ቤት በኩል ለለገጣፎ ለገዳዲ ክፍለከተማ አስተዳደር እንደተሰጠውና መስጂዱን እስከ ጥር 26/2017 እንዲያፈርስ ትዕዛዝ መሰጠቱን ተነግሯናል ብለዋል። የለገጣፎ ለገዳዲ መጅሊስ ከሸገር ከተማ መጅሊስ ጋር በመሆን ይህ ኢ-ፍትሀዊ የሆነ ውሳኔ መላውን የሙስሊም ማህበረሰብ ያስቆጣ ጉዳይ በመሆኑ የፀጥታ ችግር መንስኤ እንዳይሆን አስተዳደራዊ ውሳኔ እንዲሰጣቸው በተደጋጋሚ ቢጠይቁም የሸገር ከተማ አስተዳደር ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄ ምላሽ መስጠት አለመቻሉን በምሬት ገልፀዋል። በሸገር ከተማ በለገጠፎ ለገዳዲ በደንበል ጣፎ ከ2002 ዓ.ል ጀምሮ የአካባቢው ነዋሪዎች አካባቢው ላይ ምንም አይነት መስጂድ ባለመኖሩ ጥያቄያቸውን የጀመሩ መሆኑን በማንሳት ከዛም ነሀሴ 2014 ዓ.ል በዒድ ቀን በከተማ አስተዳደሩ 2077 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ የሱመያ መስጂድ ህጋዊ ካርታ እንደተሰጣቸው ገልፀዋል። የተሰጣቸው ቦታ ቆሻሻ መጣያ ስለነበር እሱን በማፅዳት መስጂድ በመገንባት ሲገለገሉበት ቆይተው አካባቢው ላይ ባሉ አንዳንድ አካላት መስጂዱ እንዲነሳ ጥያቄ ቢያቀርቡም የከተማ አስተዳደሩ እንዳልተቀብላቸው ተገልጿል። በ2001 ካሳ የወሰደ አርሶ አደር መስጂዱ በጉልበት 1,000 ካሬ ሜትር ወስዶብኛል በሚል ክስ መስርቷል። ፍርድ ቤት በነበረው ክርክርም የመስጂዱ ካርታ ህጋዊ መሆኑንና ለገበሬው ካሳ መከፈሉን በማስረጃ ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ መስጂዱ እንዲነሳ በሚል ያለአግባብ ውሳኔ መወሰኑን የመስጂዱ ኮሚቴዎች ተናግረዋል። የመስጂድ ጉዳይ የህዝብ በመሆኑ መስጂዱን በተመለከተ አሁንም የሚመለከተው የሸገር ከተማ መስተዳደር አስተዳደራዊ ውሳኔ ይሰጠን ሲሉ የለገጣፎ ለገዳዲ ክፍለከተማ መጅሊስና የመስጂዱ ኮሚቴዎች ጠይቀዋል። © ሀሩን ሚድያ
MUSAB~ዘ ብሔረ ወሎ😍
Region: ET
Wednesday 29 January 2025 14:25:37 GMT
Music
Download
Comments
ße Yourself :
እረ ሙስሊሞች የት አለን ምን እየጠበቅን ነዉ 🤨
2025-01-29 15:56:00
10
AAK@4400 :
subhan allah
2025-01-30 03:32:29
3
juhareendiresjema :
ማልቀስ አያስፈልግም ሊያፈርስ የመጣዉን ማፈረስ ነዉ
2025-01-30 08:37:54
2
mohammedahamed7600 :
ክክክ የትአሉ ኡስታዞቹ
2025-01-30 05:00:43
4
BBB :
ፋኖ ፀረ እስላም ነው ብለን ነበር። አልሰማ አላችሁ እንጂ
2025-01-30 04:32:37
2
userገንዘብ ኒቶርክነው ''''' zነኝ :
ሙስሊሞች አለንበሉ😭😭😭😭😭
2025-01-29 17:40:02
2
user4475433651668 :
ለድምፃችን ይሠማ ንገራቸው
2025-01-30 11:46:32
1
@jemuman9 :
yebelen gena mn ayten wehabiya ayyyyy🥺
2025-01-30 09:34:23
1
To see more videos from user @musab.tiktok2024, please go to the Tikwm
homepage.