@reformed_faith: በዚህ ቪዲዮዬ የ16ኛው ክፍለ ዘመን በአውሮጳ የተነሳው ሪፎርሜሽን ከጥንቷ ቤተክርስቲያን ያፈነገጠ እንቅስቃሴ ሳይሆን የሃዋሪያቱን አስተምህሮ በጥንቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ የነበረውን ዶክትሪን ያስቀጠለ እንቅስቃሴ እንደሆነ ለማሳየት በጥቂቱ ጥረት አደርጋለሁ። ብዙ ጊዜ የ16ኛው ክፍለ ዘመን ሪፎርሜሽን ከሚተችባቸው የሃሰት ትርክቶች መሃል አንዱ ከሃዋሪያትና ከጥንቷ ቤተክርስቲያን እጅጉን የራቀ ነው በሚል ነው። ይህን ሰንካላ ትርክት በትክክል ለመረዳት ሁለት ነገር ማወቅ ወሳኝ ይሆናል። የመጀመሪያው የጥንቷ ቤተክርስቲያን የቆመችበት መሰረታዊ የሆኑ ዶክትሪኖችን ማወቅ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሪፎርሜሽኑ የቆመባቸው መሰረታዊ የሆኑ አስተምህሮችን በማስተያየት ከጥንቷ ክርስትና መራቁና አለመራቁን መመርመር ይቻላል። በነዚህ ሁለቱ ላይ የተንሸዋረረ መረዳት የሌለው ግለሰብ በትክክል ሪፎርሜሽኑ የሃዋሪያትና የጥንቷን ቤተክርስቲያን አስተምህሮ በሙላት መያዙን በቀላሉ ይረዳል። ይህን አሳቤን በበለጠ ትረዱ ዘንድ በጥቂቱ ላብራራ. የጥንቷ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ በዋነኝነት የተመሰረተባቸው ንጣፎች 1 በሃዋሪያት ትውፊት (rule of faith/apostolic tradditions)፣ 2 በአለማቀፍ ጉባኤያት (ecumenical council)፣ 3 የሃይማኖት ድንጋጌዎች (creeds) እና 4 ከኑፋቄዎች (heresies) መለየት ናቸው። እንግዲህ እነዚህ የጥንቷ ቤተክርስቲያን መሰረት የሆኑ የአስተምህሮ ምንጮች ላይ ተመስርተን የ16ኛውን ክፍለ ዘመን የፕሮቴስታንት ተሃድሶን እንቅስቃሴ ለመበየን ሙከራ እናድርግ። 1 ሃዋሪያዊ ትውፊትን በተመለከተ…. በሃዋሪያት በቃልና በጽሁፍ የተሰበከ፣ ለሌሎችም በእውነት እንዲያስተምሩ አደራ የተሰጡ ትምህርቶች በጥንቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ በስፋት እናገኛቸዋለን። አባቶችም ይህን ትውፊት ከሃዋሪያት መቀበላቸውንና ሌሎችን አስተምህሮ በዚህ መለኪያ እየመዘኑ እንደሚቀበሉ ማረጋገጫ ነው። ይህን አሳቤን እንድትረዱና በቃል ሲተላለፍ የነበረው ሃዋሪያዊው ትውፊት ምን አይነት ትምህርቶችን እንደያዘ ታውቁ ዘንድ በቅዱስ ኢራኒየስ የተነገረውን ሃዋሪያዊውን ትውፊት ላሳያችሁ። “For, as to the Church, dispersed as she is through the whole world unto the ends of the earth, yet having received from the Apostles and their disciples the Faith in One God the Father Almighty, Who made the Heaven and the earth and the seas and all that is therein; and in one Christ Jesus, the Son of God, Who was made flesh for our salvation; and in the Holy Ghost, Who by the Prophets declared the Œconomies, and the Advents, and the Birth of a Virgin, and the Passion, and the Rising from the dead, and the bodily Ascension into Heaven of the Beloved, Christ Jesus our Lord, and His Coming from the Heavens in the glory of the Father, to sum up all things and to raise up all flesh of all human nature; that to Christ Jesus, our Lord and God, and Saviour and King, according to the good pleasure of the Invisible Father, every knee may bow, of things in Heaven and in Earth and under the Earth, and that every tongue may confess to Him, and He may administer just judgment to them all; that is, may both send into the everlasting fire the spiritual things of wickedness, as well angels that have transgressed and passed into revolt, as the ungodly and unjust and lawless and blasphemous among men; and also to the righteous and holy, and to such as have kept His commandments and persevered in His love, whether from the first or after penitency, may freely give life, grant incorruption, and compass for them eternal glory:”Against heresy , bk. 1. Chap. X. § 1. እንዳያችሁ ከዚህ ሃዋሪያዊው ትውፊት ሪፎርሜሽኑ በአንዲትም ነጥብ አይለይም። ይልቁን የሚያጸናቸውና በትውፊቱ ላይ የተደላደለ አስተምህሮ እንደሚከተል በቀላሉ ትረዳላችሁ። 2 ኢኩሚኒካል ካውንስሎችን በተመለከተ….. ሌለኛው በጥንቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ የዶግማ ትምህርቶች የሚቀዱባቸው ከ ኢኩሚኒካል ጉባኤያት እንደሆኑ በትክክል ይታመናል። ሪፎርሜሽኑ ሙሉ በሙሉ በጥንቷ ቤተክርስቲያን የሚታመኑ አለማቀፍ ጉባኤያትን ማለትም የኒቂያ ጉባኤ፣ የቁስጠንጥኒያ ጉባኤ፣ የኤፌሶን ጉባኤና የኬልቄዶን ጉባኤን ያለምንም የአስተምህሮ ልዩነት ይቀበላል። የተሃድሶ ፍሬ የሆኑ የፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶችም መሰረታዊ የሆኑ ኮንፌሽኖቻቸውን በነዚህ ጉባኤያት ላይ የመሰረቱ ናቸው። ከነዚህም ዶግማ በሆኑ አስተምህሮ የሚቃረን አንድም ትምህርት ሪፎርሜሽኑ አልተቀበለም። 3 የጥንቷን ቤተክርስቲያን የእምነት ድንጋጌዎችን በተመለከተ…… ሪፎርሜሽኑ በጥንቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተደነገጉ መሰረታዊ የሆኑ የሃይማኖት ድንጋጌዎችን በሙላት ይቀበላል። እነዚህ የሃይማኖት ድንጋጌዎች የጥንቷ ቤተክርስቲያን ዶግማ የሆኑ አስተምህሮዎችን የያዙ፣ የማይሻሩ፣ ከሃዋሪያት የተቀበሉ፣ በቅዱሳት መጸሃፍት የተመሰከረላቸው ጽኑ የዶግማ ትምህርቶችን የያዙ ናቸው። እነዚህ የእምነት ድንጋጌዎች የኒቂያና የቁስጠንጥኒያ እምነት ድንጋጌ፣ የሃዋሪያት እምነት ድንጋጌና የአትናቴዎስ እምነት ድንጋጌ ተብሎ የሚጠሩ ናቸው። የታሪካዊው የፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶች ሙሉ በሙሉ በነዚህ የእምነት መግለጫዎች ላይ የተመሰረቱ ናቸው። 4 የኑፋቄ ትምህርቶችን በተመለከተ ……. በጥንቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንደ ኑፋቄ የተቆጠሩ የስህተት ትምህርቶችን ሪፎርሜሽኑ ሙሉ በሙሉ ከጥንቷ ቤተክርስቲያን ጋር በመሆን የሚያወግዘው እንጂ ተቀብሎ የሚያስተምረው አንድም ኑፋቄ የለውም። ወዳጆቻችን የሚያቀርቡት ክስ እውነት ቢሆን ኖሮ ፕሮቴስታንቲዝም በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ኑፋቄ ተብሎ በተወገዙ የስህተት ትምህርቶች ውስጥ መውደቅ በቻለ ነበር። በተቃራኒው ግን የ16ኛው ክፍለ ዘመን የሪፎርሜሽን እንቅስቃሴ የጥንቷን ቤተክርስቲያን አስተምህሮ የሚያጸናና ከኑፋቄ ትምህርት እጅጉን የራቀ መሆኑን በቀላሉ መረዳት ይቻላል። ስለዚህ የ16ኛው ክፍለ ዘመን ሪፎርሜሽን የወለዳቸው የፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶች የሃዋሪያት ትምህርትን በሙላት የያዙና የመጀመሪያይቷ ቤተክርስቲያን አስተምህሮዎችን ያለ ምንም
Christian dogmatics
Region: ET
Thursday 30 January 2025 15:08:30 GMT
Music
Download
Comments
Raph :
ጥያቄ
በ ንቅያ ጉባኤ ጥምቀት ለ ሀጥያት ማስተሰርያ ይላል አብዛኛው ፕሮቴስታንት ግን ይሄን አይቀበልም
እና አራቅነም ነው ምትለኝ
2025-01-30 19:56:16
19
መጽሐፍ ቅዱሳዊ - Biblical :
ሸልፌክስ 😇
2025-01-30 16:14:08
89
ዲ/ን ምስክር :
ወንድሜ አባባልህን በጣም ወድጄዋለሁ። 100% ከጥንቷ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ጋር አንድ ነው አልክ ጥሩ እስኪ እነዚህን ጥያቄዎቼን መልስ
1) የኒቂያ-ቁስጠንጢኒያ ክሪድ "ሀጢአት በሚሰረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን" ትቀበላለህ ትምቀት ለድህነት ነው ብለህ ትወስዳለህ???? ....ይቀጥላል
2025-01-30 22:34:33
15
Tesfa :
በጃንደረባው ወደ ኢትዮጵያ የገባው ትክክለኛው ክርስትና ፤ በዃላ በግብጾች የቅኝ አገዛዝ የተቀየረው እስከአሁን ያለው ኦርቶዶክስ ትክክለኛ ነው ትላለህ ? ይልቁን እጅግ ርቃችሁ ያላችሁት እናንተው ናችሁና ራሳችሁን ምርምሩ !
2025-01-31 08:29:17
14
መልህቅ :
ትመቸኛለህኮ ሸልፌክስ 😁👊
2025-01-31 08:40:59
31
Dr Yihune L. (MD) :
ከ451 በፊት ያለችው ቤ/ክ ምስጢራት ለድህነት ያላቸውን አስፈላጊነት የካደች፣ድህነት በእምነት ብቻ የሚል fantasy የምታምን፣ጌታ ኢየሱስ አብን ይለምናል ብላ ይምታስተምር፣የሕጻናትን ጥምቀት የምትቃወም፣ሥርዓት የሌለው በጳጳሳት የማይመራ
2025-01-31 16:33:02
1
megersa goiytom anberbir :
የ2ሺ አመት ጉዞ በአንድ ደቂቃ ግልፅ ሆነልኝ ተባረክ
2025-01-31 04:34:57
12
Lidya MK🕊️ :
Nice 👍🏽 ቲክቶዶክስ የሀሰት ትርክታቸው is blame shifting ራሳቸው ከጥንታዊ ክርስትና መራቃቸውን ላለማመን ያለ ትግል ይመስላል::
2025-01-31 11:06:24
0
Amex :
ለማን ብለህ እንደዚህ የምትዋሸው ግን? እነዚህ የዘረዘርካቸው ራስህ አትቀበልም።
2025-01-31 06:52:02
4
የንጉስ ካህን :
ፕሮቴስታንቶች ወደ ሙታን ስለሚፀልዩ ከወንጌል እውነት ርቀዋል ¡
😂😂😂😂
2025-03-11 03:17:25
1
ተስኒም :
ምንኩስና
የማርያም አማላጅነት
መስቀል
የሙታን አማላጅነት ነበረ። ይህንን ትቀበላላችሁ?
2025-01-31 23:24:24
1
𝑫𝒆𝒔𝒂𝒍𝒆𝒈𝒏 :
ኧይ አኬ ፕሮቴስታንት ብቻ ምትተቸው ነገርስ🥺 ጆቫ አለ ኦጄ አለ ካቶሊክ አለ… እውነተኛ የሐዋርያት አስተምህሮ ተቀብላ ስላሴን የምታስተምረውን እሷን ብቻ😏 ለነገሩ ውሸት እውነትን እንጂ ውሸትን አይቃወምም😥
2025-01-30 23:18:25
0
Ze_micheal1 :
በደፈናው እንቀበላለን ብለህ አለፍከው😁 ..የኒቂያው ጉባኤ ጥምቀት ለሀጥያት ስርየት ይላል ፣ የኤፌሶን ጉባኤ emphasizes that Christ’s real presence in the Eucharist is tied to salvation ፣ The early Church and fathers እምነት ብቻ የሚለውን አላስተ
2025-02-05 02:55:32
3
EP.Christian.✠ :
ና ግባው ሸልፉ ዘፕሮማክስ👊
2025-01-31 14:10:46
10
መኮንን ምርከና :
አኬ አየዋሸ የተወደደ መስሎት ሀዲዱን እየሳተ ነው
2025-01-31 08:57:19
13
Nibret Addisu :
protestant ድካም የለባቸዉም ባይባልም ነገር ግን አሁን ካሉት ሃይማኖቶች መፅሃፍ ቅዱስ ላይ ወደተጠቀሰች ጥንቷ ቤተክርስትያን የቱ ሃይማኖት ይቀርባል ቢባል ፕሮትስታንት ነዉ የማይል ሰዉ ይኖራል? ልብህ የምያቀዉን እዉነት ብትናገርስ!
2025-03-23 07:28:11
1
sami Fam :
ደግመህ ሥራልን 🙏🙏🙏🥰
2025-02-17 19:37:24
1
ዲ/ን ምስክር :
2) የጠቀስካቸው አባቶችም ይሁኑ ሉተርም ጭምር ቁርባን የጌታ እውነተኛ ስጋና ደም ነው ለሐጢአት ስርየትም የግድ አስፈላጊ ነው ይላሉ ትቀበላለህ???
3) ለመዳን ከማመን በኋላ መልካም ሥራ የግድ እንደሆነ ይህም ብቻ ሳይሆን ሰው አምኖ ሀጢአት ቢሰራ ድህነቱን እንደሚያጣ አባቶች በግልፅ ፅፈዋል ትቀበላለህ?? ......
2025-01-30 22:39:10
1
Agape⭕🛐-ἀγάπη :
ሽልፌክስ 👏👏👏👏👏
2025-01-30 15:58:17
2
theophorus :
የመጀመርያው rule of faith ውስጥ ሁሉም አባቶች የሚስማሙበት ትምህርት ይህ ብቻ አይደለም ቀንሰሀል
2025-02-01 21:04:55
1
Israel :
ይህ ትንታኔ ፕሮቴስታንት ክርስቲያን ይባላል ለማለት የቀረበ ነው፤ ክርስቶስ ራስ የሆነላት ቤ/ክ አለች ኤፌ4:4-6፤ ባጭሩ ሉተር ከካቶሊክ ወጥቶ በ1517 አምስት ብቻዎች ብሎ አዲስ እምነት መሠረተ አሁን 45,000 ደርሷል፣ ወንድሜ አትሰቃይ፣ ወደአንዲቱ ጌታ ወደመሠረታት ቤ/ክ ተመልሰህ በህይወት ኑር።✝️✝️✝️
2025-01-31 08:30:48
1
tsihon የኢየሱስ✝️🛐 :
ሰልፌክስ ቃሌ... ወደ ቲክታክ አርፍደው የመጡ በረከቶቻችን ምናለ ከ2አመት ፊት ብትመጡ ብዙ ነገር ይለወጥ ነበር።😌😁ተባረክ ሸልፌክስ❤️❤️❤️❤️❤️❤️
2025-04-09 18:13:44
0
Mayko_black :
keep it up🥰
2025-04-25 15:47:06
0
Mesfin Teklu :
ይሄ የጥንቷን ቤተክርስቲያን አይወክልም ኒቂያ ጉባኤ 325 ዓ.ም ከጥንቷ ቤተክርስቲያን ውጪ ስላሴን ት/ት ለመጀመሪያ ጊዜ ያፀደቁበት ክሕደት የተፈፀመበት ጊዜ ነው።
2025-03-30 10:55:10
0
ⒾⓈⒶⒶⒸ ⓈⒺⒾⒻⓊ :
shelf🥰🥰🥰
2025-01-30 19:10:10
0
To see more videos from user @reformed_faith, please go to the Tikwm
homepage.