@afendi1978: ጸሐፊ: አፈንዲ ሙተቂ ---- ጥላሁን በሀገር ፍቅር ቴአትር የተቀጠረው በ1948 ነው። ሙሉ አልበለም መልቀቅ የጀመረው ግን በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ ነው። በኔ እይታ መሠረት የጥላሁን ምርጥ አልበሞች የሚከተሉት ናቸው፡፡ 1. የጠላሽ ይጠላ- 1972 2. እቱ ገላ- 1975 3. ምን ታረጊዋለሽ 1976 4. ይቺ ናት ጨዋታ-1979 በነዚህ አልበሞች ውስጥ የተካተቱት ስራዎች የሚጣልላቸው ነገር የላቸውም፡፡ ይህም የዘፈኖቹን ግጥምና ዜማ፣ የሙዚቃ ቅንብሩን እና የጥላሁን የድምጽ ቅላፄን ያካታትታል፡፡ በሌሎቹ አልበሞች ውስጥ ያሉትን ስራዎች ከነዚህኛዎቹ ጋር ማወዳደር ይከብደኛል፡፡ ለምሳሌ በ1960ዎቹ ውስጥ የተሰሩት እነ “ሰዎቹ ምን ይላሉ”፣ “ትዝ አለኝ የጥንቱ”፣ “አልቻልኩም”፣ “የፍቅርሽ ህመሙ በረታብኝ”፣ “ከመሞት አልድንም” በጣም ጥሩ ስራዎች ቢሆኑም እንዳሻው እየወጣ የሚወርደውን የጥላሁንን ድምጽ በነርሱ ውስጥ ለማየት አይቻልም፡፡ “ድማም ወድጄሻለሁ” የሚለው የ1977 አልበምም ጥሩ ሆኖ ሳለ በሙዚቃ ቅንብሩ እና በSound Mixing ረገድ ጉድለቶች አሉበት፡፡ በዚህ አልበም ውስጥ የጥላሁን ድምጽ እጅግ በጣም ጎልቶ ይሰማል፡፡ ሙዚቃው ግን ዝግ ያለ ነው፡፡ ከላይ የጠቀስኳቸው አልበሞች ግን ከነዚህ ጉድለቶች የጸዱ ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከላይ በጠቀስኳቸው የጥላሁን አልበሞች ውስጥ የተካተቱት ስራዎች በሙሉ “ኦሪጂናሌ” ናቸው፡፡ ስለዚህ በተለያዩ መድረኮች “የጥላሁን ኮከብ ስራዎች ናቸው” እየተባሉ እንደምሳሌ ከሚቀርቡት አንዳንድ ታዋቂ ዘፈኖች ላስቀድማቸው ይገደኛል፡፡ ለምሳሌ “እዩዋት ስትናፍቀኝ”፣ እና “የህይወቴ ህይወቴ” በጣም ውብ ስራዎች እንደሆኑ እንስማማለን፡፡ ነገር ግን ዜማዎቹ ከሱዳን ነው የተወሰዱት፡፡ በመሆኑም ከላይ ከጠቀስኳቸው ጋር ማወዳደሩ ይከብደኛል፡፡ በእነዚህ አልበሞች ላይ ከጥላሁን ልዩ ብቃት ችሎታ በተጨማሪ የዘመኑን ደራሲዎች የአዕምሮአቸውን ምጥቀት ለማየት ይቻላል፡፡ እነ ተስፋዬ ለሜሳ፣ አየለ ማሞ፣ ሲራክ ታደሰ፣ ያየህ ይራድ አላምረው፣ መቶአለቃ ገዛኽኝ ደስታ፣ ግርማ ሞገስ፣ ሱራፌል አበበ፣ ሸዋሉል መንግሥቱ እና ሌሎችም የጥበብ ፈርጦቻችን ምትሃታዊ ተሰጥኦአቸውን አፍሰውባቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ስራዎቹን ያጀቡት የዘመኑ የሙዚቃ ባንዶች ሚናቸውን በሚገባ ተወጥተዋል ለማለት ይቻላል፡፡ “የጠላሽ ይጠላ”ን ያጀበው አይቤክስ ባንድ በማሕሙድ አሕመድ “እንቺ ልቤን እኮ ነው፣ ስንቅሽ ይሁን ያዥው” እና በዓሊ ቢራ “ቱሩንቡሌ” ላይ ያሳየውን አስገራሚ ቅንብር በጥላሁን ገሰሰ አልበምም ላይ ደግሞታል (በነገራችን ላይ!! የጥላሁን "የጠላሽ ይጠላ" የታተመው በአስመራ ነው የሚል መረጃ ደርሶኛል፡፡ ነገሩን በትክክል የምታውቁ ወዳጆቻችን ታሪኩን ብታጫውቱን መልካም ነው)፡፡ “ይህቺ ናት ጨዋታ”ን ያጀበው ዝነኛው ዋሊስ ባንድ ነው፡፡ በ1980 የታተመውን “አውደ ዓመት/አወይ ገላ ሳሙና” የተሰኘ የጥላሁን አልበምን ያጀበው ሮሃ ባንድ ነው፡፡ “ምን ታረጊዋለሽ” እና “እቱ ገላ”ን ያጀበው ባንድ አይደለም፡፡ የዘመኑ ስመ-ገናና የሙዚቃ ፈርጥ የሆነው የማዕከላዊ እዝ ኦርኬስትራ ነው፡፡ ሙዚቃዎች በባንድ ሲታጀቡ እና በኦርኬስትራ ሲቀናበሩ የሚፈጠረውን ልዩነት በሁለቱ አልበሞች ውስጥ ማየት ይቻላል (የሱዳን ሙዚቃን ከነፍሴ የምወድበት አንዱ ምክንያት ሙዚቃዎቹ በኦርኬስትራ የሚታጀቡ መሆናቸው ነው)፡፡ በናንተ በኩል ምርጥ የምትሏቸው የጥላሁን ስራዎች የትኞቹ ናቸው?…. እስቲ ተወያዩበት፡፡ በኔ በኩል በ“የጠላሽ ይጠላ” አልበም ውስጥ ከተካተቱት የጥላሁን ተወዳጅ ስራዎች አንዱ የሆነውን “Akkam Nagumaan” በድጋሚ ልጋብዛችሁ፡፡ ----- Akkam Nagumaa ግጥምና ዜማ ፡ ሸዋሉል መንግሥቱ አጃቢ፡ አይቤክስ ባንድ አርቲስት፡ ጥላሁን ገሠሠ ----- አዝማቹ Akkam nagumaa fayyumaa (እንዴት? ነሽ አማን ነሽ? ደህና ነሽልኝ?) Hiriyaa hinqabuu kophumaa (ሌላ ጓደኛ የለኝም እኔ ብቻዬን ነኝ) Dhuftee na laaltus gaarumaa (እጅግ መልካም ነበር መጥተሸ ብታይኝ) Akkam nagumaa fayyumaa (እንዴት? ነሽ አማን ነሽ? ደህና ነሽልኝ?) ---------- Eessattin si arga garamin harkisaa (የት ነው የማገኝሽ ወዴትስ ልጓዘው?) Mee nama naaf dhaami bakkeen jirtu eessa (እስቲ ሰው ላኪብኝ ቦታሽን ልወቀው) Yaa damme yaa dammee yaa dammee bulbulaa (የኔ ማር የኔ ማር የኔ ወለላ ማር ) Ani hirriiba dhabe suman yaadaa bulaa (እንቅልፍ አጥቻለሁ ካንቺ ሓሳብ በቀር የለኝም አዳር) --------- Namni na ilaalee karaa na ceesisaa (ሰዎች ያዩኝና መንገድ ያሻግሩኛል) Gidiraan jaalalaa sihi na feesisaa (የፍቅር ውቃቢው አንቺን ያሰኘኛል) Garaan nurakinnaan sabbataan hidhannee (ሆድ ቢያስቸግር እንኳ በመቀነት ያስሩታል) Ijaa ammo akkam goona tan ilaaltee hin obsine (አይታ የማትታገሰውን ዐይን በምን ያባብሏታል?) -------- Bakka ati jirtu qalbiin koo na yaaddee (ያለሽበትን ቦታ በልቤ እያሰብኩት) Numan ciisa malee hirriibni na dide (ተጋደምኩት እንጂ ምኑን ነው የተኛሁት) Nagaatti, nagaatti nagaatti jiraadhu (በሰላም በአማን በደህና ኑሪልኝ) Guyyaa tokko dhufee hamman sidhungadhuu (አንድ ቀን መጥቼ ስሜሽ እስኪወጣልኝ) ------ ዘፈኑን ከነዜማው መስማት የሚፈልግ ሰው ይህንን የዩቲዩብ ሊንክ ይከተል፡፡ http://www.youtube.com/watch?v=QNfu_1TEQXk ------ አፈንዲ ሙተቂ ሚያዚያ 14/2008 ሀረር-ምሥራቅ ኢትዮጵያ --

Afendi Muteki
Afendi Muteki
Open In TikTok:
Region: ET
Sunday 02 February 2025 20:05:41 GMT
32095
886
20
276

Music

Download

Comments

long.man720
long man :
tnx alot
2025-02-05 18:47:36
0
abufewaz784gmail.com
ነግቶ ሰው ፍለጋ :
🥰🥰🥰
2025-03-28 22:53:57
0
amirjima1
user4846833837206 :
ሀይ
2025-02-17 01:22:21
0
bacha1771
bacha :
የዘፋኞች ንጉሥ ጥልዬ
2025-02-14 18:02:00
0
bacha1771
bacha :
❤❤
2025-02-14 18:01:27
0
user7698023036269ah
user7698023036269Ale :
ጥሌና ሙዚቃው ሁሌም ይደመጣሉ በፍቅርብ❤️❤️❤️👍👍👍
2025-02-12 12:48:11
0
user7698023036269ah
user7698023036269Ale :
❤️❤️❤️👍👍👍
2025-02-12 12:47:34
0
meysaw10
Meysaw :
🥰🥰🥰
2025-02-06 07:49:19
0
gemechu.bedru
GAMACHUU BADURU👑 :
guyyaa tokko dhufeen hamman sidhugadhuu,... wow tnxs my beloved
2025-02-03 06:46:09
0
tame34merga
ታሜ OLDIES :
👍👍👍❤❤❤❤🙏🙏🙏🙏
2025-02-05 06:11:48
0
ahmadt820
Ahmed :
❤️❤️❤️
2025-02-04 18:28:22
0
user7509278596537
user7509278596537 :
🥺🥺🥺👂🌺🙏
2025-02-04 16:55:19
0
y.ngatu
Y. Negatu :
😳😳😳😳
2025-02-04 11:24:23
0
jordanarodolfo
jordanna :
👑
2025-02-04 03:45:50
0
mahamad.gogam
Mahamad Gogam :
🥰🥰🥰
2025-02-03 22:21:58
0
ethpm2
Eth :
ስትለይኝ ካጠገቤ ሳጣሽ ከጎኔ ስትርቂኝ የ..ምታስጨንቂኝ! 🥰🥰🥰
2025-02-03 21:20:41
0
jallatagecho
jallata gecho :
🥰🥰😂😂😳😳😁😅😅
2025-02-03 20:54:56
0
zelalem.fikrezed
Zelalem Fikre :
yes
2025-02-03 20:06:56
0
To see more videos from user @afendi1978, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About