@dj_mnlwal: እምዬ ኢትዮጵያ ይመርልሽ ሰብሉ፣ አውድማው ጎተራው ይሁንልሽ ሙሉ፣ በቸር ውሎ ይደር ጋራ ሸንተረርሽ ወንዛወንዝሽ ሁሉ። ይመስክር አካሌ ጉያሽ ያደረጀው፣ የእናትነት ጣምሽ ውለታሽ ያበጀው፣ በማጀትሽ ወተት በጤፍሽ እንጀራ፣ በማር በወለላ በጓሮ ሸንኮራ፣ ብድር አለብኝ ልክፈልና ልኩራ፣ ክብርሽ ከፍ ይበል ከሰላምሽ ጋራ! የወለደኝ ምጥሽ በቸር ይደር፣ ያሳደገኝ ቀዬሽ በቸር ይደር፣ ወንዝና ጅረትሽ በቸር ይደር፣ ጫካውና ደንሽ በቸር ይደር፣ አውድማና ማሳሽ በቸር ይደር፣ በቸር ውሎ ይደር፣ በቸር ይደር.... በቸር ይደር ዙሪያው በቸር ይደር፣ በቸር ይደር ያሳደገኝ መንደር። ....ያበቀለኝ ቀዬ የተወለድኩበት፣ ያበብኩበት ምድርሽ ባካል ያሸትኩበት፣ ሜዳውና መስኩ የፈነደኩበት፣ ያደኩበት ወንዝሽ የተራጨሁበት፣ ክፉም አልስማ ክፉም አልይበት! ሰላም ደምኖ ሰላም ይዝነብበት። የእናት ያባቴ አገር በቸር ይደር፣ የወገኔ ተገን በቸር ይደር፣ የትውልዴ መድን በቸር ይደር፣ አፈሩም ሰፈሩም በቸር ይደር፣ ዓየሩም ባሕሩም በቸር ይደር፣ በቸር ውሎ ይደር ... በቸር ይደር... በቸር ይደር ዙሪያው በቸር ይደር፣ በቸር ይደር ያሳደገኝ መንደር። በቸር ይደር ዙሪያው በቸር ይደር፣ ያደኩበት አገር፣ በቸር ይደር ዙሪያው በቸር ይደር፣ ያሳደገኝ መንደር Dj_Mnlwal
Mnlwal⚡
Region: ET
Saturday 01 March 2025 18:04:01 GMT
Music
Download
Comments
ወሎ ቤት አማራ :
🥰
2025-09-03 19:02:55
1
Âmãñ :
🥰🥰🥰
2025-09-13 17:40:15
1
To see more videos from user @dj_mnlwal, please go to the Tikwm
homepage.