@gebruma2017: #CapCut #ጸጋ ቅባት እና ተዋሕዶ ጸጋ እና ቅባት የእምነት አስተሳሰቦች ሲሆኑ በአጼ ሱስንዮስ ዘመን ካቶሊክ በተዋሕዶ በተረታ ጊዜ አፈ ጉባኤ የነበረው አልፎንሱ ሜንዴዝ በጎጃም እና በሸዋ ለነበሩ ሐይማኖት መሪዎች ያስተማረው ትምሕርት ሲሆን "ኢትዮጵያ ሁለት እሾህ ተክየባት ሔድኩ" እንዳለ እስካሁን የሕዝቡን የአንድነት ስሜት ሲቀንስ ለዘመናት የኖረ ነው:: በክርስቶስ ያለን እምነት የሞት የሕይወት ጉዳይ ስለሆነ በዚህ አጭር ጽሐፉ የጸጋ እና ቅባት ትምሕርት መጽሐፍ ቅዱስ ይመዘናል:: ጸጎች : - ኢየሱስ ክርስቶስ በ እናቱ ማሕጸን ሳለ በመንፈስ ቅዱስ ተቀብቶ በጸጋ አምላክነትን አገኘ ብለው ያምናሉ:: ቅባቶች:-ኢየሱስ ክርስቶስ በ እናቱ ማሕጸን ሳለ በመንፈስ ቅዱስ ተቀብቶ የባሕሪይ አምላክነትን አገኘ ብለው ያምናሉ:: ___የጸጎች ትምሕርት በመጽሐፍ ቅዱስ ሲመዘን 1. አብ ቀቢ ወልድ ተቀቢ ከሆነ ጌታችን የጸጋ አምላክ ነውና በስልጣን እኩል ናቸው አያስብልም:: ቅዱሳን መጻሕፍት ደግሞ ወልድ ከአብ በምንም በምን እንደማያንስ ያስረዳሉ:: ዩሐ 17:10 'የእኔም የሆነ ሁሉ የአንተ ነው የአንተውም የእኔ ነው፤...." ዩሐ 10:30 "እኔና አብ አንድ ነን" ዩሐ 1:1 "በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።" ወልድ እግዚያብሔር ከሆነ እንዴት አብ ወልድን ሊያከብረው ይችላል? ከ እግዚያብሔርነት በላይ አምላክነት አለና እርሱ ይከብር ዘንድ ሻ? በጸጋስ አምላክ ከሆነ ጸንቶ አምላክ መሆን ይችላል? ጸጋ እንዲሰጥ ይነሣልና:: 2. መንፈስ ቅዱስ ቅብ በመሆን ወልድን ተቀባው ካልን በምስጢረ ስላሴ የምናምነውን የሦስት አካል ትምሕርት ያፈርስብናል:: ምክኒያቱም መንፈስ ቅዱስ ወልድን ተቀላቅሏል:: ቅዱሳን መጻሕፍት ግን መንፈስ ቅዱስ እንዳልተቀባና በራሱ አካል ጸንቶ የሚኖር መሆኑን ይመሰክራሉ:: ዩሐ 1:32..መንፈስ ከሰማይ እንደ ርግብ ሆኖ ሲወርድ አየሁ፤.../ማቴ 3:16/ ዪሐ 14:26 አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል። ...በማለት ጌታችን የመንፈስ ቅዱስ አካላዊነቱን አረጋግጧል:: ሙሴም በጸጋ አምላክ ነበር:: ዘጸ 7:1 ለሎችም አምላክነት በጸጋ እንደተሰጣቸው ይታወቃል: መዝ 81:1 የቅባቶች ትምሕርት በመጽሐፍ ቅዱስ ሲመዘን በዘመናት የተለያዩ መምህሮቻቸው የሚናገሩት ይለያያል ለማሳያ ያህል ግን :- 1. የነ ዘኢየሱስ ትምሕርት "ቃል በተዋሕዶ ተገዥ ሆነ: ከስጋ ሲዋሐድ የባሕርይ ክብሩን አጣ ለቀቀ በተቀባ ግዜ ግን ወደ ጥንተ ክብሩ ተመልሶ በሰውነቱም በአምላክነቱም በቅባት የባሕርይ ልጅ ሆነ::" የሚል ነው:: ይህ ትምሕርት ፍጹም ስሕተት ነው:: መጀመሪያ ቃል ሲዋሐድ የሥጋ ባሕርይ አሸንፎት ተገዢ ሆነ ማለት መጀመርያውኑ የሚሳነው አለ ያሰኛል አምላክ ነው ማለት አይቻልም::እግዚያብሔር ከገዢነት ወደ ተገዢነት እንደገናም ወደ ገዢነት የሚለዋወጥ አምላክ አደለም:: " እኔ እግዚያብሔር አልለዋወጥም ሚል 3:6 "ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ዘላለሙ ያው ነው" ዕብ 13:8 "እነርሱ ይጠፋሉ፥ አንተ ግን ትኖራለህ፤ ሁላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ፥ እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፥ ይለወጡማል፤" መዝ 102:26 2. የ እነ አካለ ክርስቶስ ትምሕርት " በተዋሕዶ ሁለትነት ጠፍቶ አንድነት ቢገኝም ሥጋን ያከበረው የለም: የአምላክነት ክብርም አላገኘምና አብ መንፈስ ቅዱስን ቅብዕት አድርጎ ቃል የተዋሐደውን ሥጋ ቀብቶ አከበረለት:: ሥጋም በተቀባ ግዜ ክብር ተላለፈለት: ተፈጥሮ ተገብሮ ጠፋለትና በቅባት የባሕርይ ልጅ የባሕርይ አምላክ ሆነ::" ይላሉ:: የፍጡር ሥጋ ተለውጦ አምላክ መሆን አይቻለውም:: ፍጡር ሥጋ ተለውጦ በቅባት አምላክ ቢሆን ኑሮ ቀድሞ የተቀቡት እነ ዳዊት እነ ሰሎሞን አምላክ በሆኑ ነበር:: ቀድሞውኑ አዳምና ሔዋንን ሞት ያስቀጣቸው ፍጹም ጠብ ከሰማያውያን ጋርም ያጣላቸው "ፍጡር ወደ ፈጣሪነት ሊለወጥ ይችላል" ብለው ማመናቸው ነው:: ስለዚህ ይህ ጥንተ ጠላት ለሔዋን ያስተማራት ኑፋቄ ነው ማለት ይቻላል:: ቃል በቅብዓት ተለውጦ አምላክ መሆን የሚቻለው ከሆነ ቃል ወደ ማሕጸነ ማርያም መጥቶ እንዲያድር ለምን አስፈለገው:: ቃል የአብ ቀዳማዊ የባሕርይ ልጅ ነው:: አሁን ደግሞ ሥጋ በቅብአት የባሕርይ ልጅ ከሆነ አብ ሁለት ልጆች አሉት አያሰኝምን? እንዲህስ ከሆነ የፈሰሰው ደም የተቆረሰው ሥጋ የማን ነው? እንዲህ እና የመሳሰሉትን መልስ የማይሰጥ ሲሆን በድቡሽት ላይ እንደተሰራ ቤት በፈራሽ ነገር ላይ ተመስርተዋል:: ማጠቃለያ አንባቢን ለዘርዝር ንባብ ወደ "ሁለቱ ኪዳናት" ወደሚለው የመሪጌታ ኃየሎም በርሔ መጽሐፍት እየመራሁ ለማጠቃለያ ያህል ግን: - መንፈስ ቅዱስ ቅብእ ነው ካልን ቅድስት ስላሴን ክደናል:: በስልጣን እኩል ያይደለ አብን የሐብት ማሳደርያ ምልክት አድረገነዋል::አብን እንደ ሳሙኤል መንፈስ ቅዱስን እንደዘይቱ ወልድንም እንደ ሳኦል አድርገው በማሰባቸው ፍጹም ስሕተት ነው:: የጸጋ የማደጎ ልጅ የወደቀ አዳምን ወደ ቀደመ ክብሩ ሊመልሰው አይችልም:: አዳምን በጥንተ ተፈጥሮ የፈጠረው እግዚያብሔር ነው:: ሕጉን ሲተላለፍም የፈረደበት እግዚያብሔር ነው:: ወደ ቀደመ ክብሩም ሊመልሰው የሚቻለው እግዚያብሔር ነው:: "የዲያብሎስን ሥራ ያፈርስ ዘንድ የ እግዚያብሔር ልጅ ተገለጠ" መባሉም ሰው የሆነው እርሱ አምላክ ወልደ አምላክ መሆኑን ያረጋግጣል:: በቅባት የባሕርይ አምላክ መሆን አይቻልም:: የባሕርይ ማለት ጥንት መገኛ የራሱ የሆነ ከማንም የማይቀበሉት ነውና። ተቀብቶ ከበረ ካልን ቀድሞ የራሱ ያልሆነ ገንዘብ ተቀብሏልና የባሕርይ አምላክ ሆነ ማለት አይቻለንም:: ራስን በራስ ማክበር ለ እግዚያብሔር የተለመደ ነገር ነው:: ፍጡርን ከመፍጠሩ በፊት ባሕርይው ባሕርይውን እንዳመሰገነችው ባሕርይውን ባሕርይው እንዳከበረችው ፍጡርን ከፈጠረ በኋላ ሰው በሆነ ግዜ ባሕርይው/አምላክነቱ/ የተዋሐደውን ሥጋ አከበረች እንጂ በሌላ አክባሪ የከበረ የተቀባ አደለም:: ምንጭ እና ተጨማሪ ንባብ " ሁለቱ ኪዳናት " መሪጌታ ኃየሎም በርሔ መጽሐፍ ቅዱስ /1840 / የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ በአባ ጎርጎርዮስ ( M.A ) ፲፱፻፸፬ እና ፲፱፻፹፮ ዓም

𝖌𝖊𝖇𝖗𝖚➮ ?
𝖌𝖊𝖇𝖗𝖚➮ ?
Open In TikTok:
Region: ET
Sunday 02 March 2025 04:35:51 GMT
27997
874
234
389

Music

Download

Comments

abrhame2129
D̤e̤r̤e̤j̤e̤@A̤. G̤o̤n̤c̤h̤a̤ :
ፍሬ ሆዳሙ መጀመሪያ መንፈስ ቅዱስ አካሉን አና ህብቱን በሎ ነገር የለም ከትባለም የባህረ ነው የፀጋ ነው የሚባለው
2025-05-28 12:32:57
0
amexgojje1221
አማረ የጎንቻው :
አይ ፍሬ ለሆድሽ ብለሽ ሁለት ግዜ ዘፈቁሽ ያስለፈልፍህ ጀመር አይደል
2025-03-03 07:50:53
2
user8153600610740
yilkal :
እስኪ የ ፀጋ እምነት እና የቅባት መፅሐፍ ወይም መምህራችን የሚሉትን ያስተማሩትን ነገር ማንበብ እፈልጋለሁ። ጠቁሙኝ በእናታችሁ።
2025-03-07 16:52:50
1
bebe59816
ቤERUት ቤERUት 🎀📑 :
መምህራችን ቃለ ህይወት ያሰማልን🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2025-03-02 07:39:50
3
user9199295506138
ቀንጦራሂው የግዮን ስደተኛ ከገነት መገኛ🙏❤️ :
አይ ፍሬ ሕይወት ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ መጥቶ አፉን አሲዘን እንዳልሰደደድነው ሁሉ እዚህ ሚዲያ ላይ ይቀደዳል እከካም የጠመጠመ ሁሉ አዋቂ አይደለም
2025-03-03 14:46:38
3
getch7744
Getch :
እስኪ ከኦርቶዶክሶች ጋር ስትከራከር እንይህ
2025-03-03 17:01:52
1
gojjamew.1
Never give up!! :
እሱስ ይሁን ታዲያ ለምንድነው ልደትንስ አንዴ28 ጳጉሜ 6 ሲሆን ነው ትላላችሁ በ29 ጳጉሜ 5ሲሆንው ትላላችሁ ጳጉሜ ከ600አመት አንድ ጊዜ 7 ስለምትሆን ያኔስ በ27 ትበላ??እላየህም መፅሀፈ ሚስጥርን ሀይማኖት አበውን እ
2025-03-03 16:52:32
0
ab.ab7818
Ab.Ab :
መጀመሪያ ሃይማኖትህን ለይተህ እወቅ መድሃኒያለም ልብ ይስጥህ
2025-05-03 18:01:19
0
habtamu3299
Habtamu የጎንቻው :
አይ የሮም ተኩላዋች ሁለቴ ተጠምቀህ ለከርስህ ትለፈልፋለህ
2025-03-07 14:41:23
0
brukaberaraw
Bruk Aberaraw :
አንተ ብቻህን ትፎገላለህሳ እስኪ አንድ ጥያቄ መልስ ከናቱ በፊት የተወለደ ከናቱ በፊት ወተት የጠባ ማነው
2025-03-06 08:56:54
0
www.namrud
G T M.ናምሩድ :
ኖኖኖኖ የንታ ልክ አይደሉም
2025-03-03 15:10:30
0
frie277
frie :
ዝም በል ቢቀርብህ ይሻላል
2025-03-03 14:32:02
1
zelizalawu.edmeye
zelizalawu edmeye :
የእንቶ ፈንቶ ተረት ተረት አላበቃም እንዴ?? ለመሆኑ ይህ አብሾ የበላ ደኬ መጽሐፍ ቅዱስ አንብቧል?? ዝም ብሎ በማሕበራዊ ሚድያ መቀባጠር እውቀትን አይመዝንም ለመሆኑየሐዋርያት ስራን ምዕራፍ 10:38ን አንብቧል
2025-03-02 18:53:09
1
user3668861752636
የ ደራ ው ጎንደሬ :
አይገባኝም ቅባት ፀጋ ምናምን የሚባል ነገር ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለዘላለም ፀንታ ትኖራለች
2025-03-03 11:12:38
1
user2652741026113
user2652741026113 :
በእግዚአብሔር
2025-03-30 10:27:23
0
user240663261103
Habtamu , 27 :
አሪወስ ተዋርሰህ ነው
2025-03-03 13:05:08
0
getch7744
Getch :
ኧረ ካራዎች ተረጋጉ
2025-03-03 16:58:26
1
abrhame2129
D̤e̤r̤e̤j̤e̤@A̤. G̤o̤n̤c̤h̤a̤ :
ፍሬ አምስት ግዜ ነው የትዘፈቅ
2025-03-12 10:33:51
0
gebruma2017
𝖌𝖊𝖇𝖗𝖚➮ ? :
ቄርሎስ ደግሞ በተዋሕዶ ከበረ እንጅ በመንፈስ ቅዱስ ከበረ የሚል የለም ብሮ
2025-03-05 05:19:16
0
ayneku
Ayine :
ድንቁርና ደፋር ያረጋል
2025-03-05 17:31:01
0
gebruma2017
𝖌𝖊𝖇𝖗𝖚➮ ? :
ማነው ያከበረው ማነው የሾመው ግልፅ የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ አምጣ?
2025-03-05 05:11:45
0
yesakbat
ደረሰ :
😳
2025-10-04 05:33:55
1
nati23150
Nati :
🌹
2026-03-18 16:24:16
1
xxxxxxxxxxxx1221xx
ሰዉ መሆን ይሻላል :
Bereketachihu yiderbin
2025-03-03 19:32:35
1
coder64
Amour :
comment yetesadebishiw denqoro ekekami memihierie truthfulness alachew
2025-04-20 16:41:32
0
To see more videos from user @gebruma2017, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About