@gebrekidan07: ድንቅ ማህበረሰብ አቀፍ ጥብቅ ደን ማኅበረ ሥላሴ አንድነት ገዳም! የማኅበረ ሥላሴ አንድነት ገዳም ኢትዮጵያዊ ትውፊቱን ያልለቀቀ እና ጥብቅ ሥርዓትን የተከተለ ሕይዎት የሚኖርበት ሃይማኖታዊ ቦታም ነው፡፡ ገዳሙ ከጎንደር ከተማ 132 ኪሎ ሜትር፣ ከመተማ ወረዳ ገንዳ ውኃ ከተማ 35 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። ከደረቅ ዓባይ ቀበሌ በስተደቡብ የ3 ሰዓት የእግር ጉዞ ካደረጉ በኋላም ይገኛል፡፡ የማኅበረ ስላሴ አንድነት ገዳም በአራተኛው መቶ ከፍለ ዘመን በመጀመሪያው የኢትዮጵያ ጳጳስ አቡነ ሰላማ ዘመን እንደተመሠረተ ይነገራል። የአሁኑን ስያሜ ከማግኘቱ በፊት “ምቋመ ሥላሴ”ይባል ነበር፡፡ የሺዎች ማኅበር እየተባለም ይጠራል፡፡ ማኅበረ ሥላሴ የሚለው ስያሜ በአጼ ፋሲለደስ እንደተሰየመም ነው የሚነገረው። ማኅበረ ስላሴ አንድነት ገዳም ከአብርሃ ወአጽብሃ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ ከነበሩ ነገሥታት ጋር የተሳሰረ ታሪክ እንዳለውም ይነገራል። ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ፣ ከአጼ አምደ ጽዮን፣ ከአጼ ልብነ ድንግል፣ ከአጼ ሱስንዮስ እና ከአጼ ፋሲለደስ ጋርም የተያያዘ ሰፊ ታሪክ አለው፡፡ ከሱዳን ድንበር አካባቢ በመገኘቱ ምክንያት በተለያየ ጊዜ ጥቃት ሲደርስበትም ቆይቷል፡፡ ከዮዲት እስከ ሁለተኛው የጣሊያን ወረራ በተደረጉ ጦርነቶች የገዳሙ በርካታ ቅርሶች ወድመዋል፡፡ ገዳሙ የተለያዩ የእፅዋት ዝርያዎችንም ይዟል። የዲዛ፣ የእጣን ዛፍ፣ ሽመል፣ ዞቢ እና ቋራ የመሳሰሉት እፅዋት ዝርያዎች መገኛም ነው። እንደ ዝንጀሮ፣ ነብር፣ አጋዘን፣ ሜዳቋ የመሳሰሉ የዱር እንስሳት፣ እፅዋት፣ እዕዋፋት እና ተሳቢዎች ይኖሩበታል፡፡ ገንዳ ውኃ እና ሽንፋ በተባሉ ታላላቅ ወንዞች የተከበበም ነው። ገዳሙ የአካባቢውን ሥነ ምኅዳር ከመጠበቅ አኳያ ባለው ፋይዳ ተመሥርቶ በጥብቅ ሥፍራነት እንዲከለል ተደርጓል፡፡ Visit Amhara
ልጅ እሸት
Region: ET
Wednesday 12 March 2025 15:09:32 GMT
Music
Download
Comments
Habte :
አቤት አቤትትትትትትትትትት ኧረ ሙሉውን
2025-03-12 19:05:57
1
ማን ይሆን ታማኙ(ማራናታ) :
ሙሉውን ይለቀቅልን
2025-03-27 00:23:05
1
እስኩ የልዑሌ እናት💙🤌 :
🙏🙏🙏
2025-03-13 03:32:12
0
ጎንደሬዋ አይከላዊት የቴዎድሮስ የኖህ ልጅ :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2025-03-13 06:25:27
0
fisseha yacob :
ይህን የሰጠን ፈጣሪ ይመስገን
2025-03-13 12:04:50
0
śøʼný :
ወንድሜ እንዴት ነክ.....?!
2025-03-15 10:57:45
0
user44530444811 :
🙏
2025-03-15 17:44:00
0
sara :
በጣም የሜምረው
2025-03-15 19:58:16
0
Zeradawit Zewude :
yemigetim new
2025-03-22 07:11:21
0
meስfiን@24 :
ንሀሴ 19/2010 የተዎሰዱ ምስሎች ናቸው ተመቸኽኝ ጓደኛየ
2025-04-18 14:23:18
0
To see more videos from user @gebrekidan07, please go to the Tikwm
homepage.