@saviolazeki: ስለተለየኝ ራሴን የጣልኩ ይመስላቸዋል። ስልኩን ስለማያነሳልኝ ዱካክ እየበላ የሚያሰቃየኝ ነው የሚመስላቸው ። አልፈልግሽም ማለቱ ብቻ የመቆም ድፍረቴን የናጠው ነው የሚመስላቸው። ግን አይደለም ! ሁሉን ነገር ተራ ማድረጉ አስደንግጦኝ ነው! አብረን ሳለን ያልወጣንበት የሃሳብ መስመር ፤ያልተንሸራሸርንበት ስፍራ ፤ያላሰስነው ቤርጎ ፤ ያልነገሩኩት ገመና አልነበረም ። ያልሆነው አለመሆን ብቻ ነበር !! በየደቂቃው ከጭንቅላቴ የሚፈልቀውን ዝባዝንኬ ሳላስቀር፤ ባጠገቤ ውል ያለውን ሳይቀር ነበር የምተነፍሰው። እንዳልቆም አድርጎ ያፍረከረከኝ ፤ ያሳለፍነውን ያገዘፍኩትን ነገር አንድ ሳይቀር ነው አሳንሷት የሄደው ። ትረካ የሌለው መለያየት ፤ ውጣ ውረድ የሌለው ፍቺ ፤ የማይተነፈስ ህመም ለማይታይ ጠባሳ ይዳርጋል ! እንዴት በዚህ መጠን ተራ ይሆናል ፤ እንዴት እየተፍለቀለቅኩ የምተርከውን ትዝታዬን እንደዚህ ያባክነዋል። እንዴት ጥሩ ምክንያት አይፈበርክም? አንዴት አካሄዱን ወዝ አያላብሰውም? በዚህ መጠን ተራ አድርጎኝ እንዴት ይሄዳል ? እችን ብቻ ነበር የምናክለው ? አብረን ስንሆን የኔ ነው ብዬ አይደል እርቃኔን የተንጎማለልኩት ? የነበረን ነገር ገብዶብኝ አይደለ ድክመት እና ስጋቴን መግለጤ? ያሳለፍነውን ውብ ጊዜያት ካለጥንቃቄ በአካሄዱ ተረማምዶበት ነው ያናወዘኝ። እንጂማ መለያየት ተፈጥሮም አይደል ነፍስ ከስጋስ ይለይ የለ ? መሄዱ አይደለም አካሄዱ ነው መላቅጡ የጠፋ ዱካክ ውስጥ የዶለኝ ። አወዳደቃችን ውስጥ የጣያችን ግዝፈት እና ተራነት አሻራ በጉልህ አለ ። ምን አለ አለሳልሶ ቢጥለኝ ፤ ምን አለ ሲተወኝ ይሉኝታ ቢስ ባይሆን ። አብረን በነበረን ጊዜ እንደምወደው እያንዳንዱ ዳናዬ ምስክር ነበር ። ሰው ለሚወደው አይደለም ላሸነፈው ጠላቱ እንኳ ይራራ የለ? ምን አልባት እኮ የእኔ ብቻዬን የመሆን ፍርሃት ሲያርደኝ መለማመጤን አይቶ ነው ለእኔ ያለው ስሜቱ የተከለለበት ። ምን አልባት ከእኔ የተሻለ ሰው አግኝቶ በእጁ እስኪያረጋት ወረት አውሮት ነው። ምን አልባት እንዲ መሙለጭለጭ ማንነቱ ይሆን ይሆናል። መሄዱ አይደለም ያጎሳቆለኝ ይሄ ማለቂያ የሌለው የምንአልባት ጉዞ ነው ከሰውነት ተራ ያወጣኝ ፤ ምንአልባት ቃል ገድፌ የማይወደውን ብዬ ፤ ወይ ምን አልባት ያልዋልኩበትን ነግረውት ይሆን? ወይ የሆንኩትን አገዛዝፈው አሻክረውት ይሆን? ይሄ እና ሌሎች የምን አልባት መላምቴ ነው ጭንቅላቴን ያጣበበው ። እንዲህ እንደባተልኩ አልቀርም እረሳሃለሁ ፤ ያኔ እዚህ የዘራሃውን እዛ ስታጭድ መሰስ እያልክ ትመጣለህ ፤ ያኔ የእኔን የምንአልባት የመላምት ችንካርን ትቀምሰዋለህ ። © Adhanom Mitiku ✍🏽 . . #onthisday #fyp #foryoupage #fy #foryou #habeshatiktok #ethiopian_tik_tok #cinematic #cinematography #ethiopianmusic #viral #viralvideos #streetphotography #cinema #zekisaviola #ኢትዮጵያ #aesthetic #addisababa #ethiopia
Zeki Saviola
Region: ET
Thursday 20 March 2025 11:58:20 GMT
Music
Download
Comments
keneni :
እሱን ያገዘፈው ያንቺ ፍቅር ነበር እንጂ በጣም ትንሽ ነበር
ሌላ ቦታም ቢሄድ በአዲሱ ፍቅር ደስተኛ የመሰለ መስሎሽ እንጂ ያ ባዶ መንፈሱን ፈሪ ልቡን ይዞ ነው
2025-03-20 19:22:15
131
Yale :
የደረሰበት ብቻ የሚያቀው ስቃይ ዛሬ አብሮ ዉሎ ነገ ያለምክንያት ጥፍትትትትት ኡፍፍፍፍ 😭😭😭
2025-03-21 09:26:26
14
ቀን ሳለ ፣ :
አይ ፍቅር ስንቱን በድን አደረከው ፍቅርን ረግጦ የሔደም ሌላው የሰበረውን በድን ገላ ያቅፋል የተገፋውም ሰባራ ልቡን ይዞ በሌላ ይታቀፋል የታመመ ህይወት 😥😡
2025-03-21 02:46:41
10
I vowed :
የኔ ህይወት 😭😭😭😭
2025-03-20 19:25:38
4
Lidu :
ትረካ የሌለው መለያየት.....ምክንያቱን በማላቀው ነገር ሳነበው ከፋኝ💔🙇
2025-03-20 15:23:50
21
ንፁህታዊት✝️ :
🥺🥺🥺እደፃፍከዉ ነዉ በቃ!
2025-03-20 16:48:29
7
helu@g :
የልቤን ነው ያወቅክልኝ 🥰🥰🥰🙏🙏🙏 ለመግለፀ ቃላት አጥቼ ነበር 🙏
2025-03-20 17:12:12
5
Hablø Afrø Cøffee :
አስቱካ ❤
2025-03-21 20:04:35
1
እሙሽ brooks :
please ye zefenun ሰም 🙏
2025-03-20 15:14:06
1
zcollugt535 :
aygermm i was thinking eko
2025-03-20 15:40:37
2
fifa m noah :
hmmmmmmm 😔😔😔 ❤
2025-03-20 15:32:42
2
Haile Zee :
Am With U Sis
2025-04-02 06:07:37
1
Kk :
This is me right now ene yetsafkut eskimeslgn deres bew dengche yanbebut Sigerm
2025-05-19 11:00:09
1
Engel :
እባካችሁ ተረዱኛ please በህመም ላይ ህመም አትጨምሩብኝ እባካችሁ ተውኝ......😭😭
2025-03-23 20:47:56
1
💝🧡🖤 :
lmn alasaznewm 🥺
2025-04-05 21:06:45
2
Kalkidan 🏋️♀️🏋️♀️ :
Deep 😞😞
2025-04-16 07:48:47
0
Mohammedamin Redwan :
የኔ እና የሀናንዬ ታሪክ
2025-03-22 20:13:31
0
🥀 :
ነገ የት ልሂድ🤔
2025-03-20 16:50:19
0
Abeni Bella :
የሱን ማን አየ?
2025-03-21 19:10:52
0
Ene :
yemenalbet guzo 😞👍
2025-03-22 06:20:29
0
W A S I H U N ¹² :
Indeed! 🙏❤️
2025-03-22 10:41:21
0
@Tizu24🔥 :
🙌 እደፃፍከዉ ነዉ በቃ!
2025-09-06 17:44:38
0
ማህደር🔴⚪️ :
ግን ለምንድነው🥹🥹
2025-03-23 11:16:45
0
RODANIM♱𖣂⁷⁷⁷🧿 :
silent reposte👀
2025-03-23 00:12:20
0
jo N :
so deep 😭😭
2025-03-20 18:00:10
0
To see more videos from user @saviolazeki, please go to the Tikwm
homepage.