@amharahq: ከአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት የተሰጠ የሐዘን መግለጫ የጦሩ ፊታውራሪ አርበኛ ከፍያለው ደሴ ስሙን በወርቅ የጻፈ የአማራ እና የኢትዮጵያ አይተኬ ልጅ ነው!! (ሚያዚያ 4/2017 ዓ.ም.) **** የአማራ ፋኖ የትግል ምልክት የሆነው የድርጅታችን ሥራ አስፈጻሚ አመራርና የአማራ ፋኖ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ተቀዳሚ ምክትል አዛዥ የጦሩ ፊታውራሪ አርበኛ ከፍያለው ደሴ፣ በዓላማ ቢስ ከሃዲያን ከጀርባው ተወግቶ በመሰዋዕቱ የአማራ ፋኖ ሕዝብዊ ድርጅት (አፋሕድ) መራር ሐዘን ተሰምቶታል፡፡  የጦሩ ፊት አውራሪ አርበኛ ከፍያለው ደሴ በአማራ ሕዝብ የኀልውና ትግል ውስጥ ከፊት መስመር የሚቀመጥ የአማራና የኢትዮጰያ አይተኬ ልጅ ነው፡፡ ቀደም ሲል አማራ ላይ በአደባባይ ዝተው ጦር ያዘመቱ የሕወሓት ታጣቂ ፅንፈኞች በጋሸና የቆፈሩትን "አይሰበሬ ምሽግ" ከደረመሱት ጀግኖች መካከል ከፊት የቆመው መሪችን አርበኛ ከፍያለው ደሴ ነበር፡፡ ብአዴን ከእነ ርዝራዡ ከጋይንት ምድር ተጠራርጎ ፈርጥጦ በነበረበት በዚያ ወቅት፣ አባት አርበኞችንና ወጣት ፋኖዎችን አስተባብሮ ሰፊውን ቀጠና ከፅንፈኞቹ የጦር ወረራ በጀግንነት የተከላከለ የቁርጥ ቀን መሪ ስለመሆኑ መላው ሕዝብ ህያው ምስክር ነው፡፡  የጦሩ ፊታውራሪ አርበኛ ከፍያለው ደሴ የአማራ ሕዝብ የኀልውና ትግል ወደሙሉ የትጥቅ ትግል በተቀየረበት ምዕራፍ፣ የመጀሪያውን ድል ሐምሌ 26/2015 ዓ.ም. በደብረታቦር ከተማ የለኮሰውም የትግሉ ምልክት ነው፡፡ በወቅቱ የመጀመሪያውን የፋኖ ትግል በአራት አቅጣጫ መርቶ የደብረ ታቦር ከተማን ሰብሮ በመግባት፣ ወደወሎ ጋሸናና ላሊበላ ሊጓዝ የነበረውን አንድ ሙሉ የብልጽግና ክፍለ ጦር ከጥቅም ውጭ በማድረግ  የትግሉን ችቦ በቀዳሚነት ለኩሶታል፡፡ የጦሩ ፊታውራሪ አርበኛ ከፍያለው ደሴ፣ በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ውስጥ ግዙፍ ክፍለጦሮችን ከሚመሩ ቀዳሚ መሪዎቻችን አንዱ ነበር፡፡ ለአማራነት ክብር፣ ለሰማዕታት የትግል አደራና ለድርጅታዊ ትግልና ወታደራዊ ሥርዓቶች ከፍተኛ ቦታ ይሰጥ የነበረው መሪያችን ላይ የተፈጸመው ክህደት በሕዝብና በታሪክ ፍርድ የሚያሰጥ ነው፡፡  ላለፉት ዘጠኝ ወራት አንድ አማራ አቀፍ ድርጅት ለመመስረት የተቸገሩ የተወሰኑ ግለሰብ አመራሮች፣ ከተመሰረተው አማራ አቀፍ ድርጅታችን ጋር በቅንነት አብሮ ከመስራት፣ ወይንም አማራጭ ሃሳብ የያዘ ድርጅት ከመመስረት ይልቅ፣ ለአማራ  ሕዝብ  አንድያ የሆነውን ድርጅት ለማፍረስ እንቁ መሪዎቻችንና ታጋዮቻችንን ለመምታት ቃታ ስበዋል፡፡  በሚያሳፍር መልኩ ደግሞ፣  "ወልቃይት እና ራያን በኃይል እናስመልሳለን" ከሚሉ የሕወሓት ፅንፈኞች ጋር እንደሚሰሩ በአደባባይ ከመናገራቸውም ባሻገር፣ ከፅንፈኞቹ ተልዕኮ እና የጦር ቁሳቁሶች እየተቀበሉ ጦር እስከማዝመት መድረሳቸውን በአደጋ ቀጠና ውስጥ የሚገኙት የወልቃይት እና ራያ ነዋሪዎች፣ እንዲሁም መላው የአማራ እና የኢትዮጰያ ሕዝብ ልብ ይበልልን። በአማራ አርበኞች አጥንትና ደም የጎመራውን የኀልውና ትግል ለአማራ ታሪካዊ ጠላቶች አሳልፈው ለመስጠት እየሰሩ ያሉ ጥቂት ከሃዲያን አመራሮች በከንቱ ይባዝናሉ እንጂ፣ የአማራ ሕዝብ በደሙ የጨበጣቸውን ድሎች በፍርፋሪ አይለውጥም። የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት የጦሩ ፊታውራሪ ከፍያለው ደሴ ለከፈለው ውድ የሕይወት ዋጋ መራር ሐዘኑን እየገለጠ፣ መላ ሠራዊታችን፣ ደጋፊዎቻችን እና ህዝባችን በተከታታይ ለምናስተላልፋቸው መመሪያዎች እና ትዕዛዝ በተጠንቀቅ እንዲጠብቀን እናሳስባለን። የአማራው የኀልውና ትግል ያጣው አይተኬ ጀግና አርበኛ ክፍያለው ደሴ፣ በታሪክ ማህደር ስሙን በወርቅ ቀለም የጻፈ በመሆኑ በትግል ፍሬዎቹ እና በሕዝቡ ህሊና ሕያው ሆኖ ይኖራል። አደራ ጥሎብን ስላለፈም፣ ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል፤ ታጋይ ይሞታል እንጂ ትግል አይሞትምና። ክብር ለሰማዕቶቻችን! ድል ለአማራ ፋኖ እና ድርጅቱ አፋሕድ! ድል ለአማራ ሕዝብ! ድል ለኢትዮጰያ ሕዝብ! የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት የፍይናንስ አሰተዳደር መምሪያ ኃላፊ፣ የአማራ ፋኖ በጎንደር የዘመቻ መምሪያ ሃላፊ እና የገብርዬ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ሜጀር ጄነራል ከፍያለው ደሴ። #AFPO #ስርነቀልለውጥ #AmharaGenocide #AmharaResistance መውጫችን ማሸነፍ ብቻ ነው። Amhara Fano people’s organization የዐማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ ) #ስርነቀልለውጥ #AFPO #አፋሕድ #AmharaResistance #AmharaGenocide

AmharaHQ
AmharaHQ
Open In TikTok:
Region: US
Sunday 13 April 2025 01:28:04 GMT
69956
3304
521
659

Music

Download

Comments

guzimizim
ወለላው :
ደረጄ አንችም ተመለሽ አለበለዚያ ትቀምሻለሽ
2025-04-13 09:01:44
31
cctt987654321
c_d 9876543210 :
እስክድራዊያን ፀረ አማራ ናችሁ።ደረጀ ሰለሞን መከታው እስክድርና ሀብታሙ አያሌው
2025-04-13 08:41:01
62
kemale098
Kemale :
ዘመነ ካሴ የእጅን ያገኛል
2025-04-13 10:06:27
16
atinaf424
atinaf :
አማራንማ በዶላር ቀይራችሁት የል
2025-04-13 08:27:18
34
user5214610495603
ልሳነ ጽጌ ዘተዋሕዶ.... ✍️✍️ :
ይሄ ሰውየ ክፋቱን ተመልከቱት። ደም መልሱ እያለ ነው።
2025-04-13 08:50:48
7
gara090000
Ybra gara ferdu :
ዘመነ ካሴ በገንዘብ የጎንደር ፋኖ ገዘው የውባንተ ልጅ 3ሚሊዮን ብር ገዛው ዘመነ የአማራ ጠላት ነው ከትግሉ መወገድ አለበት
2025-04-13 09:51:48
9
user6246900347825
እድለኛዉ :
ዉጣ እስከደር አይጠቅምም ትበላለህ ንቃ😂😂😂
2025-04-13 09:03:50
13
royalfamil9
አሞራው ውብነህ :
ye gojam Buda wendimachin belut😭😭
2025-04-13 05:33:40
4
nuranura0024
nuranura0024 :
ከአባቸዉ መኮነን እና ከአሳመነዉ ፅጌ ያልተማረ ፋኖ በቅርብ ዘመነን ይገሉታል ትግሉ እዚህ ላይ ያበቃል ያኔ ብልፅግና አማረለት 😌😌😌😌😌
2025-04-13 17:47:22
0
ymecheh
ሰላም ለሀገራቺን :
ባንዳው ደርጀ በላይ ታሪክ አይርሳቺሁም አማራን ከጠላት ጋላ ጋር በመተባበር የወጋቺሁ ናቺሁ
2025-04-13 08:57:11
25
erwgsg.ggsgsg
ይዘገያል እንጂ በደል አያረጂም :
አንተም ጠብቅ በቅርብ
2025-04-13 09:38:27
0
h13397
ጎጃም :
አትልፈሥፈሠ ከሥክድር ዉጣ
2025-04-13 08:48:39
2
kingon335
King 🤴 :
ዘመነን የምትሳደቡ ሰወች አታፍሩም ከእስክንድር ጎን የቆመ ሁሉ የአማራ ጠላትነው
2025-04-13 14:12:53
2
ibm_669
የቀን ሰው አትሁን ሲመሽ ትወድቃለህ :
ዶላሩን ላከውጂ እንበታትናቸዋለን ያለው ማን ነበር ብዬ😂😂😂😂
2025-04-13 08:54:04
8
gelawaye
አፄ ገላው-ዲዎስ ✝️💚💛❤️ :
አንተም በቅርቡ ጠብቅ አማራን ከድተሃል
2025-04-13 13:49:51
4
atfhnxonnqon
Rice :
ጀግናው ውባተን አታሣው የስክንድር ገረድ አተም በቅርብ ቀን አይቀርልህም ንቃ
2025-04-13 09:20:38
7
143only7
ስንቱ only በእመብርሃን🦅 :
ክንዴ አንተንምኮ ክደውሀል አይወይኔ ተቃጠልኩ💔💔
2025-04-13 09:17:59
4
user7399944215008
YONi 🇨🇬(ተዋጊዉ)🏋🏼‍♀️🗡✅ :
ዘመነ አማራን ነፃ አወጣለዉ እያለ የጎንደርን ጀግኖቺ በላቸዉ😭😭😭😭😭😭😭
2025-04-13 17:01:07
2
user5214610495603
ልሳነ ጽጌ ዘተዋሕዶ.... ✍️✍️ :
ለብልጽግና ነው እኮ ያደራጀኸው።
2025-04-13 08:52:25
5
getasew.molla
ስንቱን አየን ...... :
ዘላባጅ ሽማግሌ በስክ ያወራው ሌላ መግለጫው ሌላ የእስክንድር ደይፐር
2025-04-13 09:26:49
4
getachew9586
getachew :
ደረጀቨላይ ቢስነልጆቹ ደምና አጥት ሊሰማውና ሊቆረቁረው ይገባል ። የሡልጆች የሞቱት ለስልጣን አይመስለኝም ። ከዚህማር ያስፈልጋል ።
2025-04-13 12:58:08
3
abyu.ayew
ማለፉ አይቀርም ግን ? :
ምንዋጋለው በላችሁት
2025-04-13 08:49:37
4
jenberu394
jenberu :
ጀግንነት አንድ መሆን ነው የህዝብን እንባ ማበስ ነው እየተከፋፈልክ ታልቃለህ በዶላር እንደ ባሪያ እየተገዛህ አንተም ነገ አይቀርልህም ከእውነት ጎን ቆመህ ከወንድሞች ጋር ሁን
2025-04-13 09:08:36
4
nattytadesse1
natty :
ጭራሽ ቁራ ሂደሀል በስልክ እደዛትከው 😏😏😏
2025-04-13 11:01:39
0
user1067026927400
ሀብታሙ ደመላሽ :
ዶላር
2025-04-13 09:48:24
3
To see more videos from user @amharahq, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About