@genish_z_tana: ዋለልኝ መኮንን ማን ነው? ▪ ትውልድና እድገቱ በከፊል ዋለልኝ መኮንን የተወለደው መጋቢት 11 ቀን 1938 ዓ.ም ደቡብ ወሎ አማራ ሳይንት ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ሲሆን የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደሴ ከተማ በሚገኙት ስመ ጥሮቹ ንጉስ ሚካኤልና ወይዘሮ ስህን ትምህርት ቤት ተከታትሏል። የ12ኛ ክፍል ትምህርቱንም ያጠናቀቀው በ 1958 ዓ.ም በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ስር ይተዳደር በነበርው በልዑል በዕደማርያም ቅድመ ዝግጅት ትምህርት ቤት (Preparatory School) ውስጥ ነበር። በዚህ ትምህርት ቤት ቆይታው በሥነ ፅሁፍ ዝግጅት የላቀ ሚና ተጫውቷል። የክርክር ክበብ ምክትልና ዋና ፕሬዝዳንትም በመሆን አገልግሏል። በዚሁ ክበብ አማካኝነት በተለይም የሥነ አመክኗዊ ውይይት አካሄድን ልቅም አድርጐ እንደተማረ ይነገርለታል። ትምህርት ቤቱ ዋለልኝን ተከራካሪ ብቻ ሳይሆን ጥሩ ፀሃፊም እንዲሆን ረድቶታል። በሁለት ዓመት ቆይታው የትምህርት ቤቱ የጋዜጣ ረዳት አዘጋጅ በመሆንም አገልግሏል። ዋለልኝ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ በቀድሞ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ በ Political Science የትምህርት ክፍል ትምህርቱን ቀጥሏል። ከዚያም በኋላ በ ሕዳር 18፣ 1961 ዓመተ ምሕረት አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ በተደረገው የሥነ ጽሁፍ ውድድር ኢትዮጵያውያን ከጣሊያን ወታደር ጋር ያደረጉትን ተጋድሎ፣ መስዋዕትነት፣ ጀግንነት፣ ለአገር ታማኝነትና ፍቅርን የሚያሳይ ሰነ ጽሁፍ ጽፎ ከተወዳዳሪዎቹ ውስጥ የአንደኝነት ማዕረግ በመጐናጽፉ ሽልማት አግኝቷል። በየዓመቱ በሚከበረው የዩኒቨርሲቲው ቀን ላይም በመወዳደር ካሸነፉት ስመጥር ገጣሚዎችና ባለቅኔዎች አንዱ ነበር። ▪ የተማሪዎች ንቅናቄ ላይ የነበረው ተሳትፎ ዋለልኝ መኰንን በዩኒቨርስቲ ቆይታው የኢትዮጵያን አርሶ አደሮችና ላብ አደሮች ነፃ ለማውጣት በ1960ዎቹ ውስጥ በተደረገው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ትግል ውስጥ ዓብይ ሚና የተጫወተ ወጣት ነበር። ጥላሁን ግዛው የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ፕሬዝዳንት ሆኖ ከተመረጠ በኋላ ባደረገው ከፍተኛ የትግል ተሳትፎ ከባድ ክትትል ይደረግበት ነበር። አፍንጮ በር አካባቢ ታህሳስ 19፣ 1961 ዓ.ም ጥላሁን ግዛው በጥይት ይመታል። ይህ አሳዛኝ ሁኔታ ሲፈጠር ዋለልኝ መኰንን አምስት ኪሎ አካባቢ በሚገኘው ቤቱ ከጓደኞቹ ጋር ነበር። አንድ ወጣት ወደ ቤት ይመጣና ስለ ጥላሁን ግዛው በጥይት መመታት ይነግራቸዋል። እነሱም በድንጋጤ ተያይዘው ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል ይሄዳሉ። ሐኪሞቹ ሕይወቱን ለማትረፍ ሞክረው እንዳልተሳካላቸው ይነግሯቸዋል። በዚህ ወቅት ዋለልኝና ጓደኞቹ የጥላሁንን አስከሬን ከሆስፒታሉ በመውሰድ ዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ በስርዓት ያስቀምጡታል። ከዚያ በኋላ የተቃውሞ ትዕይንትና የቀብሩን ሥርዓት ዝግጅት ያደርጋሉ። ለኮሌጅና ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች መልዕክቶችን ያስተላልፋሉ። የጥላሁን ሞት ትግላቸውን እንደማይገታው፣ ጥላሁን ቢሞት ሽህ ጥላሁኖች እንደሚፈጥሩ በመግለጽ ጽሁፎችን በሕዝብ መሃል ያሰራጫሉ። በዩኒቨርስቲው ውስጥ ያለውን የጥላሁንን አስከሬን ለመውሰድ ወታደሮች በዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገባሉ። በዚህ አጋጣሚ ዋለልኝ ከፎቅ ላይ ሆኖ በድምፅ ማጉያ ጥላሁንን የሚቀብሩት የትግል ጓዶቹና ሕይወቱን የከፈለለት ሕዝብ እንጂ ገዳዮቹ መቅበር እንደማይችሉ ይናገራል። የክብር ዘበኛ ወታደሮች በተማሪዎቹ ላይ ተኩስ ከፍተው አበበ በርሔ፣ ስብሃቱ ውብነህ፣ ጀማል ያሲን የተባሉ ሶስት ተማሪዎችን ይገድላሉ። በዚያ ቀውጢ ጊዜ ዋለልኝ መኰንን ይተርፋል ያለ ሰው አልነበረም። ሆኖም ግን ዋለልኝና ጓደኞቹ በቁጥጥር ስር ውለው ኮልፌ በሚገኘው የፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ማሰልጠኛ ቅጥር ግቢ ውስጥ ታሰሩ። ዋለልኝ ከዚህ ቀደም በገደብ የተለቀቀ በመሆኑ ወደ ከርቸሌ እንዲወርድ ተደረገ። ዋለልኝ መኰንን ከእስር ቤት ከተለቀቀ በኋላ ወደ ትምህርቱ እንዳይመለስ ዕገዳ ተጣለበት። ▪ ዋለልኝ ስለ ብሔረሰቦች ጥያቄ የነበረው አመለካከት፤ ይቀጥላል... ዋቤ ድርሰት፦ አብርሃም ተፈሪ ከጀማል አብዱላዚዝ የምስል መግለጫ፡ በግራ በኩል ቀብረር ብሎ የሚራመደው ዋለልኝ መኮንን ሲሆን በቀኝ በኩል ከአጠገቡ የሚታየው ደግሞ ወንድምዬው ጌታቸው መኮንን ነው። ፎቶግራፉ መቼ እንደተነሳና ማን እንዳነሳው አይታወቅም።
Genish
Region: ET
Sunday 20 April 2025 14:29:40 GMT
Music
Download
Comments
kassahun demissie :
ጥራዝ ነጠቅ የነበረ ሌሎች ስለብሔራቸው ሲያቀነቅኑ እሱ ግን የተወለዱበትን ማህበረሰብ የወነጀለ የአማራ ህዝብ ቁጥር አንድ ጥላት ነበር።
2025-04-21 04:44:37
75
BlueNile :
የዋለልኝ ፍልስፍና በሕወሐቶች ዘንድ በእጅጉ የተወደደ ነበረ።
ምክንያቱ ደግሞ ስለብሔሮች መብት መከበር ይከራከር ስለነበረ ነው።
የዋለልኝ የብሔር አመለካከት ግን ከሕወሐቶች ይለያል።ዋለልኝ የግዛት አንድነቷ በተጠበቀላት ኢትዮጵያ ውስጥ የብሔሮች መብት ይከበር የሚል ሲሆን ሕወሀት ደግሞ በተበታተነች ኢትዮጵያ ነው
2025-04-22 10:30:32
5
Mr.X@12 :
የ አማራ የመጀመሪያው Collaborator አሁን ያየሰው ሽመልስን ተክቷል።
2025-04-21 16:07:40
11
MIGHTY MULUGETA :
በነገራችን ላይ የተወለደበት ልዩ መጠሪያው ቦረና መካነሰላም ይባላል።ልክ እንደ ባህል ሰዎቹም ጠማሞች ናቸው።ደሴ የስልጣን ቦታዎቹ በነሱ የተያዙ ሲሆን የመጨረሻ ደደቦች ናቸው።
2025-06-15 14:19:21
0
omerta(ኦሜርታ) :
ሺህ ጊዜ መሞት ያለበት :ኢትዮጵያ አሁን ላለችበት መከራ እና እልቂት ከዳረጓት ውስጥ ዋነኛው ሰው ነበር ::
2025-04-20 21:55:22
56
Dr. Tewodros A 👨⚕️🎙✍️ :
ማርታን አፍቅሮ የራሱ ህዝብ ላይ የዘመተና ያዘመተ መሆኑንም ብትጨምርበት 😂
2025-04-20 20:02:39
41
እዉነትን ተቀበል :
ዋለልኝ አሁን ቢኖር ብአዴንን እየመራ ህዝብ ላይ መከራ ያዘንብ ነበር የቀደመዉ የአማራ የእንግዴ ልጅ ነዉ
2025-04-21 20:02:16
13
jak :
ኢትዮጵያን ያለእውቀት ዳፋ ውስጥ ከከተቱ አንዱ ፣፣
2025-04-21 18:20:20
11
Yohanes Sahlu :
ዋለልኝ በኢትዮጵያ የአንድ ብሔር ጨቋኝነት ነበር ብሎ ያቀነቅን ነበር።ነገር ግን በአንድ ብሔር የበላይነት ስለተሠራች (ስለተመራች) ኢትዮጵያ ምንም ተጨባጭ መረጃ አላቀረበም።የገዢው መደብ አባላትን የብሔር ተዋጽኦ ማየት የቻለ አይመስልም።ለዛሬዎቹ ቅንጭብ ጩኸት(sound bites) አራጋቢዎች አንዱ ርዕሳቸው እርሱ ነው
2025-04-20 17:50:55
11
ፍቄ ...Fike :
ዋነኛው የአማራ ህዝብን ሞት እና ስቃይ ማንፌስቶ የፃፈ። በራሱ ህዝብ ላይ የመከራ ቀንበር የጫነ ሰው ነው።
2025-04-22 10:30:46
10
sewerhaile :
ዋለለኝና የዚያ ዘመን ወጣት አብዬተኞች ማስተዋል ያልፈጠሰረባቸው ግልብ ማርኪሲዝምና ሌኒንዝም በግልቡ ያነበቡ (ያልተረዱ)ይሕ በአግባቡ አለመረዳታቸውም ሀገራችን አሁን ላለችበት ችግር መሰረት የጣሉ "የዚያ ትውልድ" ደናቁራን ናቸው። ታዲያ ብዙ ምሳሌ የሚሆኑ ሰወች ታሪክ ብትጽፍ አይሻልም ነበር?
2025-04-21 08:21:58
9
Tik :
ትልቁ ካንሰር
2025-04-21 04:09:17
9
RasAddis :
የመከራችን ጠንሳሸ እሰከዛሪ አላረፍንም
2025-04-21 10:48:14
7
Abiy Abera249 :
የመጀመሪያዎቹ ወያኔ መጫወቻ የሆነ አመራ ግን የአማራ ጠላት
2025-04-21 05:39:17
7
Creator.search.Insights :
ታሪክ የሚፋረደው የተፋረደው ወንጀለኛ ‼️
2025-04-21 00:35:18
5
Mulualem Birhanu :
ኢትዮጵያ አሁን ላለችበት ቁጥር አንድ ተጠያቂ ይሄ ግለሰብ ነው።
2025-05-13 14:19:19
5
Face Jo :
ስሜታዊነ, አልመብሰል, የምናደር ጋቸውን ነገሮች በሂደት የሚያስከትሉትን መዘዝ አለማወቅ, አባቶች formal education ባይኖራቸውም በሕይወት ተሞክሮ ያገኙትን እዉቀት መናቅ, ከዉጭ ሀገር scholars ያገኘነዉን ሃሳብ ከገሃር ነባራዊ ሁኔታ ጋር ሳናግናዝብ እንደወረደ መውሰድ የዚ ሰዉና መሰሎቹ ድክመቶች ነበሩ.
2025-04-20 19:44:54
5
Faith and hope :
እማይረባ ተራ የአማራ ሕዝብ ጠላት ነው
2025-04-20 23:56:21
4
tewodrosworkneh6 :
አውሮፓ ላይ ከኢንዱስትሪ አብዮት በኃላ የተፈጠረ የሰራተኞች ማህበር እና ለነሱ የሚቆሙ ፖለቲካ ፓርቲዎች ነበሩ፤ የነሱ ርዕዮት ዓለም እንደ ወረደ ላብ አደር (የሠራተኞች) መብት ብለው ተነሱ፤ ፋብሪካዎች ሳይኖሩን፥ ኃላም ኢሐዴግ በአርሶ አደሮች ቀየረው እናም እስከ ዛሬ ምፍትሄ ያጣንለትን የደንቆሮ ፖለቲካ ተክሎ ሞተ።
2025-04-20 20:21:54
4
user5557266157635 :
መርዘኛ ፣
2025-04-21 07:14:48
5
getahuntilahun3 :
በምድር ላይ ትክክለኛ ፍትህ ያገኘ ሰው ነው። ሀገሩን ለአንድ ሴት ብሎ የከዳ የነጮች መጠቀሚያ የነበረ ነው።
2025-06-01 12:11:59
3
ፊሾም :
ኢብሣ ጉተማ &ዋለልኝ መኮንን የብሄር ፖለቲካ ጠንሣሾች ግን ሚደበቅላቸው ሠዎች ሥለ 1983 ነው ሚያወሩን
2025-04-20 15:28:00
2
biruk :
ሀገራችን ላይ መርዝ የዘራ እባቡ 1000 ጊዜ ደጋግሞ ይሙት
2025-04-21 20:05:07
3
abilake@1 :
his reincarnation is Yayesew Shimelis👍
2025-04-20 19:48:34
3
user2439929707693 :
በእናቱ ማህፀን ውሀ ሆኖ በቀረ ነበር🤔🤔🤔
2025-04-26 19:45:25
3
saidahmed5959 :
ዋለልኝ መኮንን ለኤርትራዊያን ተማሪዎች የተሰጠውን የቅጠረኝነት ተልዕኮ ያሰፈፀመ ተላላኪ እንጂ የብሔር ብሔረሰቦች ጠበቃ አልነበረም አሁን አገራችን ለተፈጠረው የብሔር ትርምስ እና ለኢትዮጵያ አንድነት አደጋ የነበሩ አስተሳሰቦችን የጠመቀ በላወቀው ፍልስፍና ራሱንም ትውልዱንም መሰዋዕት ያደረገ ከንቱ ነበር
2025-04-21 09:29:13
2
kanakana :
ጮማ ጮማ የሆኑ ስድቦችን እያየሁ ነው፡
2025-04-21 23:44:59
1
Seglelit :
እዚ ኮሜንት ሰዎች ሁላቹም ያንድሰፈር ልጆች መሆናችሁ አረጋግጫለሁ😂
2025-04-21 09:17:08
4
Jemal Kebede :
ዋለልኝ ከጀበሃ ተልኮ ተቀብሎ አማራን የወረደ ቁንፆል ሰው ነው ።
2025-04-21 07:25:00
2
Solomon :
የአማራ የእንግዴን ልጆች ናቸው! እውቀት የለሽ የሶቬት እና ግብፅ ፕሮፖጋንዳ ግጥም አድርገው የተጋቱ ኩታሮች! ከታላቁ ከተከበረው ማንነታቸው ተላቀው በተራ ብሄረሰባዊ ትርክት የናውዙ! አሁንላለንበት ውድቀት መሰረት የጣሉ! ካንሰሮች ነበሩ!
2025-04-21 05:18:03
3
RasAddis :
ነብሱ አትረፍ የአማራጠላት ነው ወገኖቹን ወደሞት የነዳ ባንዳነው
2025-04-21 10:54:52
1
@SERAWO :
ሺህ ግዜ ሳይሆን ትሪሊየን ግዜ ሞት የሚገባው ባንዳ ነው።
2025-05-07 16:06:47
1
ናሁ ሠናይ :
ዋለልኝ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በነበረበት ወቅት በኤርትራ ታጋዮች ተጠልፎ መጠቀሚያ ሁኖ ነበር እሱም አላወቀውም
2025-04-22 17:53:35
1
peace :
የሴጣን መልዕክተኛው። ሳይገባው ያመነ።
2025-04-21 17:53:47
1
Rational Voice :
የዛ ዘመን ባለ ምጡቅ አዕምሮ ወጣት። የብሔር ፣የሀይማኖት፣ የአርሶ አደርና የላብ አደር ጥያቄዎች እነሱ በተረዱበት መጠን መረዳት ባመቻላቺን ዋጋ እየከፈልን ነው።
2025-04-29 21:34:05
1
ሀዋ ቦረና ሳይንት :
ዋለልኝ መኮነን ጠላታችነው አማራማለት ክርስቲያን ህዝብ የሚበዛበት ነው ብሎ መስሊም አደለለን አድርጎ የተናገረ ባንዳ ነው🤨
2025-07-08 18:10:52
1
ፈይሳ ኤባ 🌎 ዳዳ :
ሞዴል ባንዳ !!
ብቃቱን ፣እውቀቱን፣ድንቁርናውን ፣ ጉልበቱን ሁሉ አማራን ለማጥቃት የተጠቀመ ።
ዘር ካለው ☺️☺️☺️☺️☺️☺️
2025-05-19 08:13:10
1
H/yesus :
አፈጻጸሙ ነዉ እንጂ ኢትዮጵያ የሁሉም ብሔር ብሔረሰቦችን ባህላቸዉን የሚታንፀባርቅ አይደለችም ነዉ ያለዉ ለዚህ ማሣያ ያስቀመጠዉ ደግሞ አብዘኛዉን ጊዜ በሁሉም ነገር የሚታንፀባርቀዉ ከአለባበስ ጀምሮ የአበሻ ልብስ የሰሜኖችንብቻ (የአማራና የትግራይ)ብቻ መሆን የለበትም ነዉ ያለዉ ::እንድያዉም እሱም እኮ ወደዚህ ሀሳብ የመጣዉ ከኢብሣ ጉተማ ጋር ከተከራከሩና ከተጋጩ በኋላ ነዉ የሚባለዉ::ነገሩ እንድህ ነዉ በዪኒቨርሲቲዉ የሥነ ፅሑፍ ዉድድር ላይ ኢብሣ ጉተማ
ኢትዮጵያ የማን ነዉ
የአማራ ወይንስ የትግሬ
የኦሮሞ ወይንስ የጉራጌ
..............የሚል ግጥም አቅርቦ 3ኛ ወጥቶ ሽልማቱን ከተቀበለ በኋላ ዋሌልኝ እንዴት እንደዚህ ዓይነት ግጥም ታቀርባለህ ብሎ እንደተጣሉ በኋላ ላይ ግን ሁለቱም ተስማምተዉ ዋሌልኝም የብሔሮች እኩልነትን ማቀንቀን እንደጀመረ ::ዋሌልኝ ኖረም አልኖረም ጥያቄዉ የማይቀር ነዉ የነበረዉ::አተገባበሩ ነዉ እንጂ ኢህአፓም በብሔረሰቦች እኩልነት ላይ የነበረዉ አቋም አንድ ነዉ የነበረዉ::
2025-05-19 10:51:56
1
teferiabebe04 :
ወቅተ የሰጠውን ዕውቀት ተጠቅሞ የሆነውን ሆኖ በስጋ ቢያልፍም በክፉም በደግም መነሳቱ ቀጥሏል:
ወደደንም ጠላንም ወደፊት ወደኃለወ ለሰው ልጆች የተሰጠ ነውና ይቀጥላል
2025-04-24 13:23:31
1
enkushu :
ወገኑን ለእምስ ሲል አሳልፎ የሰጠ ወራዳ ድሮስ ሴት የላከው
2025-04-21 15:43:30
1
ቢንያም አይተን ዘ አርሰናል :
በየቦታዉ እንደ በግ የሚታረደዉ እሱ የወጣበት ማህበረሰብ በሱ እና መሰሎቹ ጥራዝ ነጠቅ አስተሳሰብ ነዉ
2025-04-21 05:01:17
1
ዋሌ ሚዲያ- Walie Media :
ዋለልኝ የጀግና ጀግና ነው።ከብሄሩና ከመደቡ ከፍ ብሎ የበረረ።ለኢትዮጵያ ጭቁን ህዝቦች መብትና እኩልነት የታገለና ያታገለ።አሁንም የዋለልኝ ሃሳቦች እያከራከሩ የቀጠሉ።የዋለልኝ ሃሳቦች የበላይነቱን የያዘበት ዘመን ላይ ደርሰናል።
2025-06-04 13:18:31
1
የጁ በር ውርጌሳ :
በግሉ። ጎበዝ። ነው። አለም። ለብቻው። ቀድሞ። የገባው። ነው። እሱየገባውን። ለሌሎች ለማጋባት። ግን። የኢትዮጲያ። ህዝብ። የሚረዳበትን። ግዜ አላወቀም በግሌ ሀሳቡን። ያራመደበትን። ግዜ እና። ሰአት አልቀበለውም። ምክንያቱም። ጥቂት። በጣም። ጥቂት የተማሩ። ሰወች። ምንም። ንቃተ ህሊናው። ላልዳበረ። ህዝብ። እኔ የገባኝ። ለናተም። ይግባችሁ። ብሎ። የምእራቡን ሪኦት። አለም። እኛላይ። አምጥቶ ዘራው። ይሄው። እስካሁን። ሳይገባን። እያባላን ነው። የግሌ ምልከታ ነው። ይቅርታ። ስሙን። ስሰማ። ሁሉ። ያንቀጠቅጠኛል
2025-06-04 15:11:51
1
kator :
ለኤርትራዊቷ ማርታ መብራቱ በፍቅር ወድቆ ለአማራ መጠላት መነሻ የሆነ አጋሰስ ነው ።
2025-06-05 00:50:35
1
mihret sisay :
ሴኡል ይግባ
2025-06-01 16:40:00
0
user749980678747 :
true
2025-04-26 22:55:59
0
E and A :
እሱ ኮ ባመነበት መንገድ ትክክል ነው
ታድያ ምነው የሱን አካሔድ ሞግቶ ትክክለኛውን የምያመጣ ጠፉ ነው ሚሥጥሩ ።ለምን ሁለም አጨብጭበን መልሰን እንረግማሐን ??? ሣንረዳ ማጨብጨባችን እሔው ምሬቱን እያጨድን አይደል ??ታድያ ማን ማንን ልኮንን ።
መ
ሣይበስል አታጨብጭብ ተማር አንተስ አልተሣሣትክም !???????
2025-04-26 21:09:54
0
Zemenu Beyna :
ዋለልኝ እና ጥላሁን አሁን በሕይወት ቢኖሩ ኖሮ የአማራ ሕዝብ ለፍርድ ያቀርባቸው ነበር። ምክንያቱም የእነሱ ጦስ ነው አሁን ላለው መከራ ተጠያቂዎች
2025-04-26 12:00:33
0
Alex777 :
ለዚህ ሁሉ ጦስ የከተተን አማራን ለዚህ ደረጃ ያበቃ ባንዳ ነው ።ምንም ሳይጎልበት።
2025-04-25 20:06:28
0
Kebede Chany :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🥰🥰🥰🥰
2025-04-25 18:52:32
0
To see more videos from user @genish_z_tana, please go to the Tikwm
homepage.