@abrhammengesha19: 🌹#አባ ጉባ ማለት⁉📌 📌#ወር በገባ በ2 ፃድቁ አባ ጉባ ከዘጠኙ ቅዱሳን አንድ ናቸው#አባ ጉባ🌹••• ጻድቁ የተወለዱት ታሕሳስ 29 ቀን በ336 ዓ/ም በመንፈቀ ሌሊት ነው:: አባታቸው ጌርሎስ : እናታቸው ቴዎዶክስያ ደጐች ነበሩ::አባ ጉባ ("ባ" ጠብቆ ይነበብ) በተወለዱ ቀን ጌታችን ከመላእክቱ ጋር በመውረዱ ቤታቸው ለ7 ቀናት በብርሃን ተሞልቶ ነበር:: ሕጻኑ ጉባም ፈጣሪያቸውን "ሃሌ ሉያ" ብለው አመስግነዋል:: በልጅነታቸው መጻሕፍትን አጥንተው : ወደ ገዳመ አስቄጥስ ገብተው መንነዋል:: ለበርካታ ዓመታት ከተጋደሉ በኋላ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል "ወደ ቅድስት ሃገር ኢትዮዽያ ሒድ" ብሏቸው ከ8ቱ ቅዱሳን ጋር ወደ ሃገራችን መጥተዋል:: በወቅቱ ዕድሜአቸው ከ140 በላይ ነበር:: ጻድቁ አባ ጉባ እንደመሰሎቻቸው በስብከተ ወንጌል : መጻሕፍትን በመተርጐም : ገዳማትን በማስፋፋትና አብያተ ክርስቲያናትን በማነጽ ቆይተዋል:: በተለይ ራማ ኪዳነ ምሕረት የእርሳቸው ናት ይባላል:: ጻድቁ ቅዳሴ ሲቀድሱ ከመሬት ከፍ ብለው ነበር:: ብዙ ጠበሎችን አፍልቀው ድውያንን ፈውሰዋል:: ሙታንንም አንስተዋል:: እመቤታችንም የብርሃን መስቀል ሰጥታቸዋለች:: ጻድቁ ከበርካታ የቅድስና ዘመናት በኋላ በዚህች ቀን ዐርፈው በገዳማቸው ተቀብረዋል:: በዘመኑ ትኩረት ካጡ ታላላቅ ገዳማት አንዱ ይሔው ትግራይ ውስጥ የሚገኘው የአባ ጉባ ገዳም ነው:: (በነገራችን ላይ "ጉባ" ማለት "አፈ-መዐር : ጥዑመ-ልሳን" ማለት ነው) ††† ቸሩ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ የጻድቃኑን በረከት ያድለን:: በጸሎታቸውም በደላችንን ይቅር ይበለን:: #አሜን_አሜን_አሜን🙏❤💒🤲❤🤲 #አሜን_አሜን_አሜን🙏❤💒🤲❤🤲 #foryoupage #videoviral #fppppppppppppppppppp #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #habeshatiktok #Haile

Haile21
Haile21
Open In TikTok:
Region: ET
Saturday 10 May 2025 01:56:56 GMT
3655
188
3
18

Music

Download

Comments

tekdeme
tekdeme16 :
በረከታቸው ይድረሰን
2025-05-10 06:45:53
0
matebemekonen0
ዘጎንደር አስናቀ :
አሜን
2025-06-08 15:26:56
0
To see more videos from user @abrhammengesha19, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About