@manismortal212: ለእግዜር የተላከ ደብዳቤ (አሌክስ አብርሃም) እንደምነህ እግዜር ፣ ሰማይ ቤት እንዴት ነው? "እመጣለሁ" ብለህ ፣ ቆየህሳ ምነው ? እኛማ ይኸውልህ... ለእልፍ አ'ላፍ አለቃ ፣ ማመልከቻ ፅፈን ለወፈ ሰማይ ህዝብ ፣ መድረክ ላይ ለፍፈን ፆለት ቤታችንን ፣ እኛው ላይ ቆልፈን የምድር አተካራ ፣ ህግጋቱን አልፈን ደብዳቤ ላክንልህ ! ................................................ አይንህን ካየነው ... ሁለት ሽህ ዘመን ፣ እንደቀልድ አለፈ የመምጣትህ ተስፋ እየኮሰመነ..... መቅረትህ ገዘፈ። እንደውም እንደውም..... ‹‹በ'መጣለሁ ተስፋ ሁለት ሽ ዘመን ፣ ቀጥሮን ከጠፋ በቀጠሮው ሰአት ፣ መምጣት ከተሳነው "እግዜር አበሻ ነው !" እያሉ ያሙሃል ፣ እኔ ምን አውቃለሁ!? .................................................. "አመስግነው" ሲሉኝ ፣ እልልታ የማቀልጥ "ቃሉን ስማ" ሲሉኝ .... ሰባኪው እግር ስር ፣ በደስታ 'ምቀመጥ "እግዚ...ኦ" በሉ ሲባል ፣ እንባየን የማፈስ "ሃሌ ሉያ" ሲሉኝ ፣ በሳቅ ልቤ እሚፈርስ ምናምኒት እውቀት ፣ ውስጤ ያልፀደቀ እንበረከክበት ፣ ጉልበቴ ያለቀ እኔ ምን አውቃለሁ?! ............................................ ግን አንተ ደህና ነህ .......? ከምር እንደሚያሙት ፣ ምፅአት ቀረ እንዴ ? የሰናፍጭ ቅንጣት ..... ታህል ጥርጣሬ ፣ አትከፋም አንዳንዴ ። ከሆነስ ሆነና ...... ሰማይ ቤት ፣ እንዴት ነው? አብረሃም ሰላም ነው? እዛስ ቤት ገነባ ፣ ዛሬም በድንኳን ነው ? እኛማ ይኸውልህ..... በቤት ኪራይ ችንካር ፣ እየተሰቀልን ‹‹ኤሎሄ›› እንላለን ፣ ጎጆ እንድትጥልልን ። ወደላይ ገነባን ፣ ወደጎን አሰፋን ወደላይም ከላይ፣ ወደጎንም ከጎን፣ እንደጉድ ተገፋን። "ቤት ለ'ንግዳ" ማለት ፣ ጭራሹኑ ጠፋን !! ..................................................... አባታችን ሙሴስ ፣ እነዴት ነው ለክብሩ ውቂያኖስ መክፈያው ፣ ደህና ናት ብትሩ? እኛማ ይሄውልህ .... እንጀራ ፍለጋ ፣ ባህር ስናቋርጥ የተስፋዋን ምድር ፣ አሸዋ ሳንረግጥ የትም ውሃ በላን ፣ የትም አሳ ላሰን ን ገ ር ል ን ና ፣ በትሩን ያውሰን ። እናልህ እግዜር ሆይ .... ከተስፋዋ ምድር ፣ ወደሌላ ተስፋ ፣ አለን እየኳተን መሄጃው ሲገርመን ...... መመለሻ መንገድ ፣ መቆሚያ ቦታ አጥተን። ላባታችን ሙሴ እንደምትልልን .... ‹‹የመሄድ ዘመን ነው ባህር የመሻገር ፣ " በትርህን ላክልን ›› ብሎሃል በልልኝ! ................................................ ሰማይ ቤት እንዴት ነው ? ዳዊትስ ደህና ነው ? ዛሬም ይዘምራል ፣ ዛሬም ይፎክራል ? ሰላም ነው ጠጠሩ? ፣ ሰላም ናት ወንጭፉ እዛስ አቅል ገዛ ..... ጎሊያድ ተራራው ፣ ጎሊያድ ግዙፉ ? እልፍ አላፍ ጎሊያድ ፣ ከቦን ሲደነፋ ወንጭፉን ጠቅልሎ ፣ ምነው ዳዊት ጠፋ ? ብሎሃል በልልኝ!! ለረከሰ ጠጠር ፣ ለሞላ ወርዋሪ ‹‹ወንጭፍህን ስጠው ፣ ለዚህ ታሪክ አውሪ›› ብለህ እዘዝልን ። ...................................... እንዴት ነህ ጌታ ሆይ? ሰማይ ቤት ፣ እንዴት ነው ? የሙሴ አልጋ ወራሽ ፣ እያሱ ሰላም ነው ? ያቆማትን ፀሃይ ፣ " ግቢ" ቢላት ምነው?! ያው እንደምታውቀው...... አስራ ሶስት ወራት ነው ፀሃይ የምንሞቀው ። ኧረ ፀሃይ በዛ ! ኧረ ፀሃይ በዛ ! ኧረ ፀሃይ በዛ !!! የመጣው ወር ሁሉ ፣ ፀሃይ እያዘለ የተሸመው ሁሉ ፣ ‹ ፀሃይ ነኝ › እያለ የአስራ ሶስት ወር ፣ የግዜር ፀሃይ የአስራ ሶስት ወር ፣ የሰው ጀንበር ባቃጠላት ምድጃ አገር ምን ታምር ሊኖር ይችላል ...... ፀሃይ ሁኖ ፣ እንደመፈጠር ?! .............................................. ኧረ እግዜር በናትህ ፣ በጭንቅ አማላጇ ባዘለህ ጀርባዋ ፣ ባቀፉህ እጆቿ ወይ ዝናብ ላክልን ፣ ወይ ዝናብ ሆነህ ና ሙቀት ገደለና !!! ........................................... እናል.....ህ እግዜር ሆይ..... ማጣፊያው አጥሮናል "ስም ያለው ሞኝ ነው "ሁሉም ይጠራናል። "ጳውሎስ" ሲሉን ...አቤት "ጴጥሮስ" ሲሉን ...ወዬ "ይሁዳ" ሲሉንም ፣ አቤት እንላለን ስማችንን ሸጠን ..... ሰላሳ ጭብጨባ ፣ እንቀበላለን። ................................................. ተወው የኛን ነገር ! ሰማይ ቤት እንዴት ነው ? ሄዋንስ ደህና ናት .....? ያው የልጅ ልጆቿ ፣ በ'ግሯ ተተክተው የፍሬው ሲገርምህ ፣ ግንዱንም አንክተው ለፍጥረተ አዳም... ባይኑ ያገምጡታል ሰይጣንም ደህና ነው ኑሮ ተስማምቶታል ሰውን ለማሳሳት ላይ "ታች" ማለት ትቷል ሳይጠራው የሚጎርፍ ፣ ህዝብ በዝቶለታል። ኧረ እግዜር በናትህ በጭንቅ አማላጇ ባዘለህ ጀርባዋ ባቀፉህ እጆቿ ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሁነህ ና ሙቀት ገደለና!!

ማን እንደ እናት
ማን እንደ እናት
Open In TikTok:
Region: ET
Sunday 29 June 2025 07:22:36 GMT
6551
187
6
116

Music

Download

Comments

bademaw.tadele
mekonnen bekalu :
😁
2026-03-21 18:22:10
0
s6801579
S ዬ // የአባቷ ብርቅዬ // :
😭😭😭😭
2025-07-02 11:59:28
0
user2471063376504
አምላክያዉቃል አልጨነቅም :
😂😂😂😂
2025-06-29 18:29:44
0
user125054428
daniel gg}gggg :
❤❤❤
2025-07-08 14:33:28
0
zimtegnaw8298
Minda :
abetu maren
2025-06-29 08:13:32
0
To see more videos from user @manismortal212, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About