@yonas.belay74: ...መቼስ አይሆንም ካልሽ ቅሪ ግድ የለም አትገደሪ ልቦናሽ በመተረልሽ ባሳደረብሽ እደሪ ተስፋ መቀነን ነው መቼም የሰው ልብ አይችለው የለም ብቻ ዳግመኛ ሞት ሳንሞት አዲስ ቀን ሳይጨልምብን ድፍን ደመና ሳይቋጥር ክረምት ውጅት ሳይወርድብን ኮከባችንን ሳንጠራ ሳንቆጥርባት ሳትቆጥርብን ሞራችንን ሳናስነብብ ሳናሳያት ሳታይብን ጨረቃን መስክሪ ሳንል ሳናውቅባት ሳታውቅብን አዋሽ ማዶ ቆቃ በረን እባክሽ ጀንበር ትጥለቅብን ውሃ እንደ ዱታ ሲተምም በድን ሸለቆ ሲናገር በሰማይ ፈረስ ተጭኖ ከአጥናፍ አጥናፍ ሲንደረደር ሲያስጉተመትም ሲያስገመግም በአይነ ህሊና ለመመስከር ሳንጨነቅ ሳንገደብ ለማንም ምንም ሳናዋይ ሳንናገር ሳንጋገር ካይንሽ ከልብሽ ከልቤ አዋሽ ማዶ አብረን እንብረር ከሰው ኳኳታ እንነጠል ላንድ አፍታ እንኳ እንገለል በእፎይታ ጥላ እንጠለል ዝም ብለን አብረን ዝም እንበል 1961,ቆቃ ክቡር የአለም ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን . . . . "ዝም ብለን አብረን ዝም እንበል"#ፀጋዬ_ገብረመድህን #ግጥም #foryoupage #video #creatersearchinsights #ግጥምለምትወዱ #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Yonas Belay
Yonas Belay
Open In TikTok:
Region: ET
Tuesday 08 July 2025 17:56:29 GMT
371789
21132
189
2634

Music

Download

Comments

amanchucha16gmail.com
Wonber Wonber :
ለሚከተሉት ቃላት ትክክለኛ ፍቻቸውን በምንባቡ መሰረት ተናገሩ፤ ለእያንዳንዱ ቃላት የ 100 ብር ካርድ ተዘጋጅቷል! 1) አትገደሪ 2) መቀነን 3) ውጅት
2025-07-11 17:14:41
18
robel.12212
robel @1221 :
እንካንም ይህን ዘመን አላዩ ሎሬት
2025-07-09 12:16:37
130
zennyh1
JevJev 💙 :
አማርኛን ያገዘፏት የኦሮሞ ሊህቃን ናቸዉ 👌
2025-07-14 19:05:36
25
merry54444
ሜሮን☦️ :
አዋሽ ማዶ እያለፍኩ ነው የሰማሁት🥰
2025-07-10 06:07:39
54
sifbeka6257
beki Ahadu :
@beki Ahadu:@beki Ahadu:ጉድ እኮ ነው😞 01,02,03,04,05,06,07,08,09,10,11,12,13,14,15,16,17,18,19,20,21,22,23,24,25,26,27,28,29,30,31,32,33,34,35,36,37,38,39,40,41,42,43,44,45,46,47,48,49,50,51,52,53,54,55,56,57,58,59,60,61,62,63,64,65,66,67,68,69,70,71,72,73,74,75,76,77,78,79,80,81,82,83,84,85,86,87,88,89,90,91,92,93,94,95,96,97,98,99,100,101,102,103,104,105,106,107,108,109,110,111,112,113,114,115,116,117,118,119,120,121,122,123,124,125,126,127,128,129,130,131,132,133,134,135,136,137,138,139,140,141,142,143,144,145,146,147,148,149,150,151,152,153,154,155,156,157,158,159,160,161,162,163,164,165,166,167,168,169,170,171,172,173,174,175,176,177,178,179,180,181,182,183,184,185,186,187,188,189,190,191,192,193,194,195,196,197,198,199,200,201,202,203,204,205,206,207,208,209,210,211,212,213,214,215,216,217,218,219,220,221,222,223,224,225,226,227,228,229,230,231,232,233,234,235,236,237,238,239,240,241,242,243,244,245,246,247,248,249,250,251,252,253,254,255,256,257,258,259,260,261,262,263,264,265,266,267,268,269,270,271,272,273,274,275,276,277,278,279,280,281,282,283,284,285,286,287,288,289,290,291,292,293,294,295,296,297,298,299,300,301,302,303,304,305,306,307,308,309,310,311,312,313,134,315,316,317,318,319,320,321,322,323,324,325,326,327,328,329,330,331,332,333,334,335,336,337,338,339,340,341,342,343,344,345,346,347,348,349,350,351,352,353,354,355,356,357,358,359,360,361,362,363,364,365,366,367,368,369,370,371,372,373,374,375,376,377,378,379,380,381,382,383,384,385,386,387,388,389,390,391,392,393,394,395,396,397,398,399,400,401,402,403,404,405,406,407,408,409,410,411,412,413,415,416,417,418,419,420,421,422,423,424,425,426,427,428,429,430,431,432,433,434,435,436,437,438,439,440,441,442,443,444,445,446,447,448,439,450,451,452,453,454,455,456,457,458,459,460,461,462,463,464,465,466,467,468,469,470,471,472,473,474,575,476,477,478,479,480,481,482,483,484,485,486,487,488,489,490,491,492,493,494,495,496,497,498,499,500,501,502,503,504,505,506,507,508😜ሴሌም ኖ😂 እዚ ድርስ መታቹ የለ ፎሎ አርጉና እለፏ
2025-07-11 11:46:01
5
dev7612
dev :
ሎሬት ጸጋዬ ወድሃለሁ
2025-07-11 21:10:46
18
user8529371238407mesh1
Emarina menor :
ኧረ በአማርኛ አርጉልን!!
2025-07-10 09:32:29
19
mamea06
mamusha :
የዘር ሀረጉ ይጣራልን
2025-07-30 09:18:38
0
teshal.woreku
Teshal Woreku :
ምንም አልገባኝም
2025-07-09 23:55:40
4
abelll1919
dagmaros :
ግጥም እንዲህ ነው የሚነበበው....... ገጣሚው ሳይሆን ግጥሙ ነው መጮህ ያለበት
2025-07-11 11:02:14
7
seblewongell
Maya🦅 :
ሞታችሁ እንዴት ያለ ሆኖ ይሆን የእናንተ? እናንተ ድንቅ ፍጥረቶች🥰🥰🥰🙏
2025-07-09 19:03:39
18
delila_ah
Delilah :
አባትአለም❤️
2025-07-10 10:48:27
7
user4126709731670
#ሸገር ሼልፍ :
ንዝረት
2025-07-10 14:22:31
6
tiktok.marketcenter
Market place :
እንደ ሎሬት ፀጋዬ ያሉ ስንት ሙሁራንን በሞት አጣን ይሁን እንጅ ዘመን ተሻጋሪ ሥራቸው ከኛ ጋር ነው ። ነፍስ ይማር የኔ ምሁር
2025-07-11 09:22:12
10
berhanu354
Berhanu :
ታላቁ የጥበብ ሰው ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን እግዚአብሔር ነፍስዎን በደጋጎቹ በአብርሃምና ያዕቆብ አጠገብ ያድርግልን !!!
2025-07-09 15:59:06
8
lealem872
Lealem :
አትገደሪ ጎጃም አካባቢ የሚነገር ቃል ሲሆን ትርጉሙ ጉድ አታርጊኝ፣ አትቀልጅብኝ እና የመሳሰሉትን ማለት ነው
2025-07-14 22:05:18
3
wes08126
wesi lawyer :
ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድን🥰❤🥰
2025-07-09 11:59:34
9
keepmesilent5252
keep me silent :
ግጥም ብቻ ሳይሆን ፍልስፍናም ጭምር ነው በይ ነኝ በኔ መረዳት
2025-07-10 17:04:02
4
adbar.tilahun
Adbar Tilahun :
ህያው ሎረት
2025-07-18 21:28:58
2
woynadega
የወይና ደጋ ሰው :
አማርኛ አንችልም ለካ😭
2025-07-11 13:07:24
4
amanchucha16gmail.com
Wonber Wonber :
ከዚህ በታች ያሉትን ቃላት በምንባቡ መሰረት ፍቻቸውን ተናገሩ፤ ለእያንዳንዱ ቃል የ 100 ብር ካርድ ተዘጋጅቷል! 1) አትገደሪ 2) መቀነን 3) ውጅት
2025-07-11 17:10:28
3
martha.kassahun
Martha Kassahun :
የኔ ጀግና 🥰🥰🥰👏
2025-07-09 10:06:41
9
gashaw.sinkeneh
Gashaw Sinkeneh :
one love loret
2025-07-10 16:30:15
4
aziz955
wanofey2 :
አማርኝን አማርኝ ያደረጉ የኦሮሞ ገጣሚዎች ክብር ይገባቹሃል🥰🥰🥰🥰
2025-07-13 21:21:28
4
abuye266
7ኛው ልጅ 4k Driver🏍🤨🇪🇹 :
እንዴት አባቱ የሚጣፍጥ ጣዕም ያለው ግጥም ነው አባት አለም
2025-07-15 11:35:16
2
To see more videos from user @yonas.belay74, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About