@musictube369: ፀጋዬ እሸቱ🎤🥰 ባለ ወርቅ ድምፁ ተወዳጁ ኢትዮጵያዊ 🙌 ጥቂት ሰለእሱ ላውጋቹ እስቲ …… !!! በመጀመሪያ ግን የግል አስተያይቴን ላስቀድም ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን ይሄ የኛ (musictube) መርህ ነው🙏🙏 ፀግሽ ከዚህ በላይ ክብር ይገባዋል ከምንም በላይ ሳልጠቅሰው ማለፍ የምፈልገው ፀጋዬን ከማንም አርቲስት በላይ ለሚሰጡት ግጥሞች አበጥርጥሮ በመምረጥ ይታወቃል ይሄ ማለት ለኔ እና ለእናንተ በሳል ስራን ይዞ ለመቅረብ ይጠነቃቃል ማለት ነው🙌 ታዲያ የሙያ ባልደረቦቹም ይሁኑ በቅርበት የሚያውቁት ሰዎች ስለ ሰው አክባሪነቱ ተናግረው አይጠግቡም መቼስ በኔ በኩል ለዚህ ማረጋገጫ አይስፈልገኝም የሱን ሙዚቃ ስሰማ የግጥሞቹን በሳልነት ሳደምጥ ለኛ ለማያውቀን አድማጮቹ ይሄን ያክል ተጨንቆ ጥዑም ሙዚቃዎችን ከሰጠን ለቀረቡትማ ምን ያክል ባከበራቸው🙏 እንኳንም እግርኳስ አልነጠቀችን እንኳንም ሙዚቀኛ ሆንክ ፀግሽ🙌 ፀጋዬ እሸቱ 🎼 በ1970ዎቹ ብቅ ብሎ በበርካቶች ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፏል፡፡ ከ4 በላይ አልበሞችን በግሉ ፤ በዛ ያሉ ስራዎቹን ደግሞ ከሌሎች ጋር በጋራ በአጠቃላይ ከ100 በላይ ሙዚቃዎችን ለአድናቂዎቹ አድርሷል፡፡ ከ1998ዓ.ም በኋላ ደግሞ በሰርግ ስራዎቹ ብቅ ብሎ በርካቶችን በሰርግ ሙዚቃዎቹ ድሯል፡፡ በልዩ ልዩ የበጎ አድራጎት ስራዎቹም ይታወቃል፡፡ ድምፃዊ ፀጋዬ እሸቱ፡፡ 🎼 ድምፃዊ ፀጋዬ እሸቱ ሙዚቃን በከፍተኛ 16 የሙዚቃ ኪነት ቡድን ጀምሮ ከአሞራው እና አክሱማዊት ባንዶች ጋር በመሆን ስራዎቹን አቅርቧል፡፡ በ1976ዓ.ም የህንፃ ኮንስትራክሽን የሙዚቃ ቡድንን ተቀላቅሎም ሰርቷል፡፡ በ1979ዓ.ም የተመሰረተውን አክሱማዊት ባንድንም በባለቤትንት ይዞ እየሰራ ይገኛል፡፡ የመጀመሪያ ካሴቱን በ1980ዓ.ም፣ ሁለተኛውን በ1983ዓ.ም ፣ ሶስተኛውን በ1987 ፣ አራተኛውን በ1995ዓ.ም እና በ1998/99ዓ.ም የሰርግ ስራዎችን የያዘ አለበሙን ለአድማጮች አድርሷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በርካታ ነጠላ ዜማዎችን ሰርቷል(አንድ እንሁን፣ ምን ሆነናል፣ በጉራጌ ደሳለኝ እና ሌሎችም) ፡፡ በ2005 ያወጣውን best of tsegaye ሳይረሳ🥰🙏 🎼 በልጅነቱ ለእግር ኳስ የተለየ ፍቅር የነበረው ሲሆን ከተከላካይ እስከ አጥቂነት ለቀበሌ እና ለት/ቤቶች ተጫውቷል፡፡ ለቀጣይም በአለምፀሀይ ወዳጆ የተዘጋጀ ዘፈን እየሰራ ነው፡፡ ለግጥም እና ዜማ የተለየ ቦታ የሚሰጠው ፀጋዬ በድምፃውያን ማህበር ውስጥም እየሰራ ይገኛል፡፡ ባለቤቱ ወ/ሮ ዘነበችም የዳንስ ባለሙያ ስትሆን በሀገር ፍቅር ትያትር ቤት የዘመናዊ ዳንስ አሰልጣኝ ናት፡፡ ተዝቆ ከማያልቀው የህይወት ልምዱና ተሞክሮዎቹ ይቺን ለቅምሻ ብለናል፡፡ 🎼 ቀሪ ዘመንህ የሰላም ፣የደስታ እና የስኬት እንዲሆንል እመኛለሁ፡፡🙏🙏 እኔም ለዛሬ በጣም ምወደውን ዘምናኒትን ጋብዤያቹ አበቃው🙌 @musictube 🇪🇹 #fyp #ፀጋዬእሸቱ #ዘምናንዬ #ሮሃባንድ #musictube369 #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱️🅴
🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱️🅴
Open In TikTok:
Region: ET
Saturday 19 July 2025 20:33:39 GMT
584572
22241
143
1534

Music

Download

Comments

aschalewtadele01
aschalewtadele977 :
የወንድ ልጅ ብሶት የዘፈነ ጀግና
2025-07-20 06:13:48
28
ermiyas_t
Ermiyas_t :
one of ❤️legend ethiopian music 🥰❤️
2025-07-19 20:49:09
10
behaila
behaila :
በማር እንካ ብላኝ ወለላ አሳይታኝ በጣም አስከንፋኝ በጣም አስረ.... ግጥሙን በትክክል ፃፉት በደንብ ስሙት እና የሰማችሁትን ፃፉልኝ plz
2025-07-21 17:58:58
5
borex22gizaw
borex gizaw :
ዘብናኒት 👌👌👌🥰🥰🥰
2025-07-20 12:31:42
8
mahi.mahi737
mahi.mahi :
:best ever ethiopian musician with best proformas quality song I love tiegeshe👑👍🙏🥰♥️best choice 👏🙏🙌
2025-09-19 16:08:16
1
butu4193
butu :
ዋው ድሮ ና ዘንድሮ፡፡
2025-07-20 11:27:33
5
user49176611152855
wagjiraHabte :
oneof 🌷iegendethiopianmusic
2025-09-15 11:35:07
1
user1239477921817
gezahegn :
ምርጥጥጥጥጥጥጥጥጥጥጥጥ
2025-07-21 12:41:31
2
binimanmahi
bini man mahi :
Ok
2025-07-23 18:34:47
0
dagnachew63
dacgachew :
ዘፈንን ፀጋየ እሸቱ ይዝፈናት
2025-10-10 15:08:47
0
asasas9491
አይ መኖር ደጉ :
ፅሁፉን ጎላ አድርጉ አይሠማም እንዴ
2025-07-22 18:07:45
0
mekonin.12
Mekonin Mengstie :
ድሬ
2025-08-02 12:36:35
0
teketofeteneteket
ተክቶ ፊጠነ :
የምር እውድሀለሁ🥰
2025-07-23 17:37:02
0
user7451873222386
@Habtoom :
ፀጋዬ ምርጥ ዘፈን ድሮ ዘፍኗል...አሁን አይችልም🙃🤗
2025-07-22 21:55:18
0
pristine117
🇪🇷pristine :
ግጥምና ዜማ የማነው
2025-07-22 18:14:37
0
hilinagezahgne
hilly🖤🤍❤️ :
🥰🥰🥰
2025-09-19 18:23:28
1
fevan14
fevan yeziid10758 :
🥰🥰🥰🥰
2025-07-20 12:52:51
3
yaredabate275
yaredabate :
🥰🥰🥰
2025-07-20 13:06:32
3
user7509278596537
user7509278596537 :
🥰 🎧🔥
2025-07-20 19:45:39
2
seble713
Seble :
🥰🥰🥰🥰
2025-07-20 19:46:09
2
whoknows1105
it's me😎 :
🥰♥️
2025-07-20 04:10:18
3
abi.nih
Abi Nih :
😁😁😁
2025-07-20 15:20:46
2
letu2097
letu :
🥰🥰🥰🥰
2025-07-20 09:05:16
3
sintayehukebede430
Santaa ye 16❤️🙏❤️ :
🥰🥰🥰
2025-07-20 08:17:55
2
ermiyas_t
Ermiyas_t :
👍👍👍
2025-07-19 20:47:55
2
To see more videos from user @musictube369, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About