@mame7877: እመንገድ ላይ አየኋት ። ወፍራለች ፣ ጡቷ እንድድሮው አይደለም ። ቦርጫም ሆናለች፣ ትልቅዬ የጭቃ መከላከያ ጫማ ተጫምታለች ልጅ አቅፋለች ። ብዙ አመት አብረን ተንዘላዝለን ተጨቃጭቀን .. ተዋደን ... ተዳርተን... ተማምተን፣ ተሳስበን ሙሉ ቀን ተጠፋፍተን ምነው የት ጠፋህ የት ጠፋሽ ተባብለናል ። ተለያየን ብለን ታርቀናል ፣ተበዳድለን ይቅርታ ተባብለናል ትክዝ አልኩ ፦ ልጅነቷ ውስጥ ልጅነቴ ነበር። ጠረኗ ውስጥ ትዝታዬ ተወሽቋል ። እንድተለያየን ሁለት ወር ሳንቆይ ከኔ ጋ እያለች ከሚጀነጅናት ጋ መሰለኝ አብራው መኖር ጀመረች አራት ወር እንደቆዩ ተለያዩ ሲጣሉ አርግዛ ነበር መሰለኝ ብዙ ሳትቆይ ወለደች ልጁም የሱ ነው ተባለ ። ምን አለ ልጁ የኔ ቢሆን ...! አባትህ እንዲ መጥቶ፣ ሰርቶ ፣ሄዶ ፣በድሎኝ፣ ጠቅሞኝ፣ ገለመሌ እንዲ ሆነን ተጣብሰን ተዋደን ብዙ ግዜ ቆይተን ገለመሌ ትላለች እኔም የልጄ እናት እንዲ አድርጋ እንዲ ሄደን፣ ወጥተን ወርደን እንዲ አቶድም እሷ እንዲ ናት እያልኩ ለልጄ እነግረው ነበር ። ምን አለ እኔጋ እያለች ሙሉ እንድሆንላት ተመስጣ ባትደምር ባትቀንስ ፣ ምናለ እኔስ ባልፈለሳሰፍ ዝም ብዬ ገፋፍቼ አታልዬ አስርግዣት ቢሆን ። ህፃን ልጅ አቅፋ ጎስቁል ብላ ልጅነቷን በልጇ ተሸሽጋ እየሸኘችው ነው ። ውዱን ጊዜያችንን አብረን ነበርን ። ምን አለ ያቀፈችው ልጅ ከኔ ቢሆን፣ ምን አለ ያረገብኩት ጡቷ በኔ ልጅ ምክንያት ቢወድቅ ። ልጇ እሷን አይመስልም። ምን አለበት ሌላው ይቅር ልጆ እሷን ቢመስል ። ውድድ ...ሳምምም... እቅፍፍ ...ባደርገው ። አብሮነታችን ምንም ቋሚ የሚናገር ነገር ሳይገነባ አለፈ ። እሷ ግን ታድላ መኖርያ ምክንያት አገኘች ። በድርበቡ ሰላም ብያት ልጆን እጁን ስሜው አይን አይኖን እያየሁ ከላይ ከላይ ካወራን ቀጥሎ "ለኔም ውለጂልኝ" አልኳት ሳቀች ሳቋ ውስጥ ልጅነቷ ወጣ ፣ በማርያም.... እ....?🙏 ስለት አሳዘንኳት መሰለኝ ፊቷ ቅር አለው፣ "በዚህ ልጅ የበላውት ፍዳ ብታቅልኝ ኖሮ.... "አለች መንገዷ አባጣ ጎርባጣ እንደነበረው ብዙ ነገሯ ይናገራል ግዴለም ሁን ያለው ነው የሚሆንው ።እኔም ስንት መከራ ሳይገለኝ ምሮኛል ፣ሰንት ሞት አምልጫለሁ መጥፎ ነገር ብቻ የሚያልፈኝ በእውነቱ እኔ ማነኝ?! ባይልልን ነው ! #ኮፒ_ሊንኩን_እየተጫናቹሁ🙏 #ፍቅር➻ብቻ🖇ፍቅር➻ብቻ❤🥀🔐 #vairal #100k #tik_tok #follow @Master Tagel #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 @mame ደሴ 🏗 #1millionaudition @Seren❤️Tayfun
mame ደሴ 🏗
Region: KW
Monday 21 July 2025 08:37:30 GMT
Music
Download
Comments
eyerustekil :
የምር የኔ ሂወት እስከሚመስለኝ ጨርሼ አነበብኩት😢 ምን አለ እኔም ልጅ ወልጄለት ቢሆን የሚፈልገዉን ልጅ ሰጥቼዉ ቢሆን ልጅ እፈልጋለሁ ሲለኝ ልጅነት አይ ቤተሰቦቼ ይገሉኛል አልወልድልህም አልኩት 😢ይሄን ግዜ አብረን ነበርን ስንት ነገር አሳልፈን አሁን ግን እኔ ነኝ የማሳዝነዉ እሱ የሚፈልገዉን አንድም ሳይሆን መንታ ልጆች ወልዷል ደስ የሚል❤ሂወት እየኖረ ሳገኘዉ ግን በርቺ እራሽን ቀይሪ እያለ ይመክረኛል ምን አለ አግብቼዉ ቢሆን😢
2025-07-22 07:17:25
224
jemi amazing Gal :
ወላሂ ይሄ ሂወት ትክክለኛ የእኔ ሂወት ነው የመጀመሪዬን የልጅነቴ አብሮ አደጌ ጋር ባአጋጣሚ በተፈጠረ ቀላል ፀብ በመሀል ሌላ ሰው ገባ ቤተሰብም ይሄኛውን ወደዱት እንዳገባ ገፋፉኝ አገባሁት ስወልድ ግን ባህሪው ሁላ ተለዋወጠ ሂወት ተመሰቋቀለችብኝ አልፍታ ነገር የቤተሰቦቼ አፍ ፈራሁ ግን ሁሌም ሲከፍኝ የመጀመሪያ ጋር ነበር እየደወልኩ የማለቅሰው እሱው ነበር የሚፅናናኝ አልሃምዱሊላህ አሁን ግን ሁሉም ተስተካከለልኝ ትዳሬንም ፈታሁ ልጄም አደገችልኝ ስራዬን እየሰራሁ በሰላም እየኖርኩ ነው
2025-08-19 04:21:43
27
እርሽው ብሎፈራጅ🥺🤔 :
ሌላው ፅሁፍ ያልመጣው ለኔ ንቆኝ ነው ፈርቶኝ😏😁🤣🤣
2025-09-04 02:59:50
1
💝ቃል አለኚ ለናቴ❤ 🇪🇹🇰🇼🇮🇶 :
የገባቺሁ እዳታልፉኚ🙄🤔😌😌😌😌😌😌😌😌
2025-09-01 19:14:23
1
እግዚያብሄር ይመስገን :
ይገለፆልን ላልገባን🙄🙄🙄🙄
2025-09-03 13:23:05
2
𝐈𝐲𝐦𝐞𝐧 :
ማንኛውንም መፀሀፍ ማንበብ ምንችልበትን አፕልኬሽን እንፍጠር
ምን ይመስላችኸል ሀሳቤ የተመቸው ላይክ
አፑ ካለም አለ በሉኝ
2025-08-15 08:29:26
29
feti የረሱል ወዳጅ 💘🇪🇹💚🇹🇷✍️ :
ወላሂ እባየን መቋቋም አልቻልኩም 😭የታፈነ ጩህት😢😢😢
2025-08-31 16:46:17
13
ኮሜንት አፍቃሪዋ🤣🤣 :
እሂን ቪድዮ የፖሰትከው ልጅ የስራህን ይስጥህ ወደዝች ምድር ከመጣሁ 19 አመት ሆነኝ ግን እንደዛሬ አልቅሸ አላውቅም😭😭😭
2025-08-26 21:26:17
4
የመርሳዋ ❤👑 :
አህህህ አሰከ መጨረሻዉ ያነበበ
ጌታዬዬ ለልጀ ሰትል ጠንካራ አድርገኝ አቅም የለኝም ትዝታ ሲነሳ የመጀመሪያ ባሌ ብቻ ነዉ ትዝ የሚለኝ ንፁህ አፈቃሪ ሰለነበር
2025-08-15 17:50:15
4
S💚 ህልመኛዋ😍😘 :
ምድነዉ አስረዱኝ በማሬም
2025-07-22 10:07:55
6
user939311386353 :
ታልፈነዳንገሩኝኝኝኝኝ
2025-08-23 20:48:55
1
𝕖𝕞𝕒.𝕓𝕖𝕕𝕦𝕒𝕤𝕙𝕚🦋🦋 :
እመኑኝ አንድቀን ያልፍልኛል 🙄እስኪ ይለፍልሺ በሉኝ 😭😭
2025-07-23 10:44:43
51
Teddy z-Michael :
እኔስ ቁልጭ ብሎ ገብቶኛል እንባየም ፈሰሰ እናንኮ ትልቁን ጫማ ማን እንደለበሰው እየፈለጋቹ ይሆናል🤔
2025-07-22 04:51:14
36
Almaz Addisu :
በሰዎች ሂውት ውስጥ የሚሆን ነገር ነው
2025-09-04 11:55:09
1
🥀fatuma seid🥀 :
የኔ ታሪክ እደዚህ ነበር የሆነው ብቻ ከባድ ነው ሂወት እድህ ነች በአሁኑ ሠአት አልሀምዱሊላህ አላህ በጥሩ ነገር ክሦኛል አልሀምዱሊላህ የወደፊቱን የበለጠ አላህ ያሣምርልኝ ያረብ
2025-08-30 21:10:28
2
Fethya Ali :
አዎ እሱ ጋር ያመኛል ከሚለው መጸሀፍ ነው የተወሰደው ካገኛችሁት አንብቡት ወላሂ በጣም መሳጭ ነው☺️
2025-07-21 23:56:41
33
➳♥ :
ማነው እደኔ እሠከመጨረሻው ያነበበ
2025-08-19 17:09:38
7
Fruit🦅 :
ይሄን ያክል ካዘንክላት ህይወቷን እንደገና አስጀምራት ካሳት አግባት ልጇን አባት ሁንለት 🥺🥺
2025-07-22 05:13:04
67
ስሜ አንተ ነህ ✝️💒✝️💚💛❤️ :
ማናት ቆይ ያነበባችሁት ንገሩኝ
2025-07-22 18:02:21
4
ኣክስማዊት የማርያም ልጅ :
እፍፍፍ በጣም ያሳዝናል
2025-08-28 11:49:17
2
ከታገሱ ያልፋል :
አልሀምዱሊላህ በምንም አልፀፀት ፣በፊት ስንጣላ ይጨንቀኝ ነበር በጣም ስለምወደው መለያየታችን ሳይሆን የሚያሳስበኝ የነበረው ከሱ (1አንድ ልጅ) ሳልወልድለት ፍቅሬ በከንቱ እንዳይቀር በጣም እጨነቅ ነበር ፣አሁን ላይ በጣም ደስተኛ ነኝ 2 የፍቅር ፍሬወች እሱን የሚመሣስሉ ወለድኩለት አልሀምዱሊላህ ፣ቢሄድም ግርዱ ነው ምርቱን ይዣለሁ ምንም አይጨንቀኝ የሱን ፍቅር፣የሱን ጠረን፣የሱን ትዝታወች በልጆቸ አገኛቸዋለሁ ማሜነቴ በሂወት እስካለሁ ሁሌም አፈቅርሀለሁ የኔ 1ኛ
2025-07-23 00:24:33
25
EMOJI😎😜 :
🥺🥺🥺🥺🥺የኔ የባሰ ነው እድነግራቹሁ ከፈለጋቹሁ ንገሩኚ
2025-08-12 01:58:59
5
ነፂ የጁ ወልደያ🌹🌹🌹 :
ከታያለው አልነበብ አለኝ ባማርኛ አርጉልኝ ሆደን ቆረጠኝ😭😭😭
2025-07-22 00:43:26
9
aaaa :
ህዝቤ ሳይገባዉ ይኮምታል ከታች አንብቡ🤣🤣🤣ታሪኩ ግን😭😭😭
2025-07-22 11:46:51
7
𝙧𝙤𝙯𝙞𝙣𝙖 ለገሂዳ💔 :
በናንተ ዲርሰት እኛ እዉነት መስሎን ልባቺን የሚሰበረዉ ነገርሰ🥺
2025-07-21 23:58:09
174
To see more videos from user @mame7877, please go to the Tikwm
homepage.