@melakufekadu1: የመንግስት ሠራተኞች የጡረታ መመሪያ! ************** 1. ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ በተቀጠረው በ60 ቀናት ውስጥ ለጡረታ በማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ መመዝገብ አለበት፡፡ 2. የጡረታ አበል ለቀጣይ ተቀማጭ የሚሆነው ገንዘብ ከሠራተኛ 7% ሲሆን ከመንግስት ደግሞ 11% በድምሩ 18% ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ግን ከሠራተኛ 7% እና ከመንግስት 25% በድምሩ 32% ነው፡፡ 3. ጡረታ የሚያስወጡ ምክንያቶች:- 1=በእድሜ ምክንያት 60 ዓመት ሲሞላው 2=በራሱ ፈቃድ 3=በጤና ጉድለት 4=በስራ ለይ በደረሰ አካል ጉዳት 5=በሞት ናቸው፡፡ 4. የጡረታ አበል በውክልና የሚከፈለው:- 1= በእርጅና 2=በህመም 3= ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ 4= በትምህርት ወዳ ሌላ ቦታ በመሄድ 5=በእስራት ምክንያት ናቸው፡፡ 5ኛ. የጡሮታ አበል በይርጋ የሚዘጋው:- 1=የጡረታ አበል ጥያቄ ሳይቀርብ ወይም የተወሰነለትን ጡረታ ሳይወስድ ከ5 ዓመት በላይ ከቆየ አይከፈለውም፡፡ በቀጣይ ከአመለከተበት ቀን ጀምሮ ይከፈለዋል፡፡ 2=የዳራጎት ጡረታ ሳይጠየቅ ቀርቶ ወይም የተጠየቀውን 5 ዓመት ድረስ ሳይወስድ ከቆየ በይርጋ ይዘጋል (አይከፈልም):: 6. በእድሜ 60 ዓመት ሲሞላው ለሠራተኛው የሚሰጥ የጡረታ አበል ስሌት:- * ከተቀጠረበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ዓመት ድረስ ያለው አገልግሎት በ30% ሲባዛ ከ10 ዓመት በላይ ያለው እያንደንዱ አገልግሎት ግን 1.25 ይባዛል፡:ለምሳሌ 28 አመት አገልግሎት ያለው ስሌት 10ዓመት×30% + 18ዓመት ×1.25= 30+22.5= 52.5% ነው፡፡ በዚህም መሠረት ለጡረታ የሚያዘው ደመወዝ የመጨረሻው የ36ወራት (3ዓመት) ብቻ ስለሆነ በ3ዓመቱ ሲከፈል የነበረው ደመወዝ 5,000 ቢሆን ጡረታው 52.5% ×5,000ብር = 2,625 ብር ጡረታ ያገኛል ማለት ነው፡፡ 7. በጀማሪ ቅጥር ወቅት ቀንና ወር ሳይሞላ ዓ,ም ብቻ በህይወት ታሪክ ተሞልቶ ከተገኘ የጡረታ ቀንና ወር የሚያዘው በኢ/ያ አቆጣጠር ከሆነ ነሐሴ 30 ተብሎ ሲያዝ እ.ኤ.አ ከሆነ ታህሳስ 31 ቀን ተብሎ ይታሰባል፡፡ 8. በረሱ ፍላጎት ጡረታ የመውጣት መብት እድሜው 55 ዓመት ሲሆንና 25 ዓመት አገልግሎት ሲኖረው ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ሠራዊት ግን ከሚወጡበት ዓመት 5ዓመት ቀድሞ መውጣት ይችላሉ ፡፡ 9. የሟች ጡረታ የሚወርሱ ልጆች ከ18ዓመት በታች ወይም አካል ጉዳተኛ ልጅ ከሆነ 21ዓመት በታችና የሟች እናትና አባት ናቸው፡፡ 10. ለጡረታ አበል ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ ማስረጀዎች:- 1=በህይወት ታሪክ የተሞላው መረጃ (ጡ1እና 2) 2=የሙከራና የቋሚ ቅጥር ደብደቤ 3= የጡረታ መለያ ቁጥር 4= የ36 ወራት የደመወዝ መረጃ 5= የዝውውር፣ የደረጃ ዕድገትና የደመወዝ ለውጥ የተደረገበት ደብደቤ 6= የጋብቻ እና የልጆች ማስረጃ 7= የባለጡረታ ወይም የወራሽ ፎቶ ግራፍ ናቸው፡፡

መላኩ ፍቃዱ - Melaku Fekadu
መላኩ ፍቃዱ - Melaku Fekadu
Open In TikTok:
Region: ET
Thursday 24 July 2025 18:20:44 GMT
492665
5770
296
3281

Music

Download

Comments

aberham.ewnetu
ማን እንደናት :
አንድ የመንግስት ሰራተኛ 10አመት እንዳገለገለ ስራ ቢለቅ የሰራበት ይከፈለዋል ወይስ እንዴት ነው
2025-07-25 05:30:40
17
temesgen7428
Teme Boss28 :
እባክህን መልስልኝ 2አመት ከ7ወር ሰርቸ በራሴ ፊላጎት ተቋሙን ለቀቁ አሁን ከለቀኩኝ 2አመት ሞልቶኛል ጥቅማጥቅመን መጠየቅ ይችላለሁ????
2025-07-25 11:00:39
5
gtera4
senait :
10 አመት ያገለገለ ሰው ስራውን ትቶ ቢዋጣ እድሜው 60 ሲደርስ ጡረታ ይያዝለታል?
2025-07-25 10:42:04
8
demam.tseganeh
Demam Tseganeh :
መንግስት ሰራተኛ የሆነሰዉ በ53እድሜዉ እና አገልግሎት 26አመት ቢኖረዉ ጥሮታ ሊከፈለዉ ይችላልን
2025-07-25 12:07:09
1
mes05788
Mes :
አንድ ሰው አገልግሎቱ 25 ዓመት ቢሆንና ዕድሜው 45 ቢሆን በገዛ ፈቃዱ ጡረታ መወጣት ይችላል? አበሉን ማግኘት ይችላል?
2025-07-26 17:41:29
5
sol894880
sol :
አንድ ሰው አገልግሎቱ 25 ዓመት ቢሆንና ዕድሜው 57 ቢሆን በገዛ ፈቃዱ ጡረታ መወጣት ይችላል?
2025-07-25 05:51:13
4
yalewtuji
ያሊቲችኮቭ ቱጂቭስኪ :
ወታደር ሆኖ በጉዳት ምክንያት ጡረታ ቢወጣና እንደገና በመንግስት መስሪያ ቤት ተቀጥሮ ቢሰራ ከዚያም እድሜው ደርሶ ጡረታ ቢወጣ ሁለቱንም የጡረታ አበል ማግኘት ይችላል ወይ?
2025-07-25 04:12:22
1
user8282839e9e8e8e8
abeba :
በራስ ፍላጎት በ55 አመት ቢወጣ የጡረታ አበሉ 60 አመት እስኪሞላ ያስጠብቃል
2025-07-25 03:06:01
5
befikir.gizachew8
Befikir Gizachew Te :
የኮንትራት ቅጥር ስራተኞች የጡረታ አበል ይቆጣሉ ?
2025-07-25 14:12:53
2
user4144928376826
Jetua :
እኔ ስቀጠር የጡረታ ፎርም አልሞላሁም ነበር ደጋግሜ ጠየኩ ግን ማሽኑ ተበላሽቷል ሌላ ጊዜ እያሉ በስተመጨረሻ መስሪያ ቤቱ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ከስራ አሰናበተን ምን ተሻለኝ
2025-07-25 07:47:32
0
watbaw27
Wendesen Mya 21 27✝️ :
የወንድሜን ልጅ በማደጎ ባሳድገው ጡረታ ለእሱ ማድረግ አልችልም?
2025-07-25 18:50:00
1
amanchucha16gmail.com
Chorrie Sedoma :
28 ዓመት ያገለለ የመንግስት ሠራተኛ ጡረታ አሠራሩ ላይ 10x30%= 3 ነው፤ 18X1.25 = 22.5 ከሆነ 3+22.5= 25.5 ነው እንጂ 53.5 አይሆንም በዚህ ላይ ምን ትላለህ ?
2025-07-25 19:01:55
6
herrera1774
Haptsh K. :
ከ ጡረታ ግብር ይከፈላል?
2025-07-25 05:58:53
0
asefa.lemma7
Asefa Lemma :
ሶሻል ሚዲያን ተጠቅሞ መረጃዎችን ማጋራት ተደራሽነቱን ስለሚያሰፋው ቀጥሉበት!ኤጀንሲውን አመሠግናለሁ ።
2025-07-25 05:32:33
11
nebiyu.zerihun4
Nebiyu zerihun :
30%*10 is 3
2025-08-04 08:50:36
0
azezewassefa
azezewassefa :
ጥሩ መረጃ ነዉ በዉነት ማህበራዊ ዋስትና ተሻሽሏል ማለት ነው
2025-07-25 07:57:11
5
user2524799361746
ወንድም by Jesus :
ተቀጣሪ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ዚጋ ከሚሰራው የተወሰነ እየቆጠበ እድሜው ሲደርስ ጡረታ ቢያገኝ መልካም ነው
2025-07-26 17:05:03
3
user87338399006872
ሰው ለሰው-12 :
8ኛ ክፍል በስተት ዕድሜየን በጣም ቀንሽ ተመዝግቤ ግን አሁን ለጦረታ ሊረብሸኝ ነው .ማስተካከል ይቻላል?
2025-10-14 05:04:37
1
user7498745684877
መለኛው ደላላ ባህርዳር :
አንድ የመንግስት ሰራተኛ 10አመት ሰርቶ ጥሮታመውጣትይችላል?
2025-07-26 01:58:43
0
pushcash7
pushcash :
ሚስት ወይም ባል የጡረታ ውርስ አይመለከታቸውም ወይ ???
2025-07-26 04:51:28
1
gher197
So what? :
አንድ ሰው ከ 10አመት በታች ከሰራስ መጠየቅ ይቻላል🙏
2025-07-25 10:58:06
1
wediselke22
TITANIC💛❤️🔰💍 :
አንድ መከላከያ ዕድሜ 43 ማዕረጉ ሻምበል ያገለገለው ዓመት 26 ዓመት ቢሆን?
2025-08-03 19:50:05
1
kin.h417
Kin. :
10*30% =30 how?
2025-07-25 03:34:30
3
etheal1221
creater search insights etheal :
30%*10+1.25*18=?
2025-07-27 16:20:14
1
user68311382048221
user6831138204822 ibro jjagma :
አንድ ሰው የጡረታ ጊዜው ደርሶ ሲወጣ የደመወዙ ስንት ስንተኛ ነው ሚያገኘው
2025-07-25 15:40:10
1
To see more videos from user @melakufekadu1, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About