@musictube369: ሀይማኖት ግርማ ☺️ ከሰንደል ማስታወቂያ እስከ ከዚራ የኮመኮምንላት በአይኗ ገርፋ ስንቱን ከታቪው ጋር የሰፍች የ90ዎቹ ንግስት የሀረሯ ፈርጥ 🥰 ፍልቅልቋን ለዛሬ ይዤላቹ መጥቻለሁ🙌😍 የሙዚቃ ጉዞዋ በልጅነት በቤት ውስጥ ሙዚቃን በማንጎራጎር ይጀምራል ቤተሰቦቿ እንደ ሌሎች ቤተሰቦች ሙዚቃን እንድትተው ጫና አያሳድሩባትም ነበር ኧረ እንደውም ሽልማት በመስጠት ያበረታቷት ነበር እንዲህ እንዲያ እያለ በትምህርት ቤት እና በተለያዩ ክበባት እንዲሁም በምሽት ክለቦች ችሎታዋን እያዳበረች ቆይታ በ1996 አ.ም የመጀመሪያ አልበሟን ለአድማጭ ያደረሰቺው ። ሰላም ውድ ቤተሰቦች ታዲያ ለዛሬ በ90ዎቹ በእጅጉ ገነው ከነበሩ አልበሞች መሀል አንዱ የሆነውን የሀይማኖት ግርማ "ኦማሂሬ" አልበም ላይ "ላባብልህ"ን በመጋበዝ ጥቂት ስለዚህ ድንቅ አልበም የማወጋቹ ይሆናል። ይህ በ1996 አ.ም በናሆም ሬከርድስ አሳታሚነት ለአድማጭ የደረሰው አልበም ከዚራ፣አስማሉ፣እሹሩሩ፣ላባብል እና ሌሎች 8 ተወዳጅ ሙዚቃዎችን ያካተተ ሲሆን የአልበሙ መጠሪያ ኦማሂሬ የተሰኘው ሙዚቃ ግጥም እና ዜማው በጌታሁን ምትኩ የተደረሰ ሲሆን ከግጥም እና ዜማ ባሸገርም በፊውቸሪንግ የተሳተፈበት እና "ጌቱ ኦማሂሬ" የሚል መጠሪያ ስምንም ያስገኘለት ነበር የሙዚቃው ሀሳብ እንዲህ ነው ። በልጅነት የወንድም ያህል ቅርብ ከነበረ በኋላም ወደፍቅር የተለወጠ አብሮ አደጓን በመናፈቅ እና እሱን በማሰብ ውስጥ ያለችን ሴት የሚያስደምጥ ነው...... "ከአይኔ አልጠፋም እንቢ ያለኝ እስከዛሬ በልጅነት ያሳለፍኩት በኩር ፍቅሬ በቃ እስካሁን እኔን አይልም ይረሳኛል ብዬ አቻዬን እንዳልፈልግ ቸግሮኛል ኦማሂሬ...........................ኦማሂሬ " "በልጅነት ያሳለፍኩት በኩር ፍቅሬ" እያለች ባማረ እና በተዋበ ድምጿ ትዝታዋን እያጋባች በዛን ዘመን ወጣትነቱን ልጅነቱን ላሳለፈ ሰው ትዝታን ሸክፋ በዚህኛው ዘመኑ የሚመነዝረው ሀብቱ አድርጋለታለች ተወዳጇ ድምፃዊት ሀይማኖት ግርማ ። እዚህ ተወዳጅ አልበም ላይ እራሷ ሃይማኖት ግርማን ጨምሮ ፍፁም ካሳሁን፣ጌታሁን ምትኩ፣ባሻ ብርሀኑ ፣ቢንአሚር አህመድ፣ ብስራት ጋረደው፣መሰለ ጌታሁን፣ አብነት አጎናፍር፣ሀብታሙ ቦጋለ፣ በግጥም የተሳተፉ ሲሆን ሀይማኖት ግርማ፣አብነት አጎናፍር፣ባሻ ብርሀኑ ፣ቢንአሚር አህመድ፣ ብስራት ጋረደው፣ጌታሁን ምትኩ፣ታመነ መኮንን እና ተስፋዬ የተባለ ሰው በዜማ ተሳትፈውበታል ። ይህንን ተወዳጅ አልበም የብዙዎች የትዝታ ማህደር እንዲሆን በማድረግ አስውቦ ያቀናበረው ታላቁ የሙዚቃ አቀናባሪ ዳግማዊ አሊ ነው ።🙌 በዚህ አልበም ላይ ለተሳተፉ ባለሙያዎች ሁሉ ልባዊ ምስጋናን እያቀረረብኩኝ 🙏🙏 ለዛሬ አበቃው !! ከአልበሙ ዉስጥ በይበልጥ የምቶዱትን ሙዚቃ በComment ንገሩኝ። "ኦማሂሬ"አልበም (1996 ዓ.ም) 1.እሽሩሩ 2.አሰማሉ 3.ኦማሂሬ 4.ከዚራ 5.በቃ በቃ 6.ጉራገኛ 7.ላባብልህ ⭐ ግጥም: ጌታሁን ምትኩ ዜማ: ጌታሁን ምትኩ 8.ሞክራታ....... 🎸ሙዚቃ ቅንብር; ዳግማዊ አሊ 🎹ሚክሲንግ እና ማስተሪንግ; ዳግማዊ አሊ ናሆም ሬከርድስ 🗣ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🙌🙏 @musictube 🇪🇹 #fyp #ሀይማኖትግርማ #የ90ዎቹ #ላባብልህ #musictube369 #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
Open In TikTok:
Region: ET
Thursday 24 July 2025 19:47:42 GMT
83768
3506
41
178

Music

Download

Comments

tizitanegash
Luuna🌙✨ :
ያን ጊዜን ደግመን መኖር ባንችልም 🥺.....ትዝታውን እንዲህ ደስ በሚል መልኩ ስለምታቀርብልን🙏🙏
2025-07-25 21:45:31
14
sosotesh1
soso teshome :
next Please አስማሉ🙏
2025-07-25 10:35:07
8
suranegro10
ራብች sura 🤙 :
1st yelhal
2025-07-24 19:54:53
4
semurad2
GUNNERS FOR LIFE :
እንደ ሌሎቹ ከነ ምናምኑ አቅርበው ሙሉ አልበሙን pls
2025-08-28 23:08:19
2
mehbubzayra
ZAYRA MEHBUB :
haymi my love🥰
2025-09-07 19:34:57
2
adonay6802
Christian :
ዝም ብላችሁ ስሜን አንብቡ!
2025-07-25 01:54:30
2
mubarek.seid774
የራስህን ሂወት ኑር :
ቴድሮስ ታደሰን አምጪልኝ እባክሺ🥺🥺🥺🥺🥺🥺🥺🥺🥺🥺🥺
2025-08-06 15:57:27
0
nati_mesfin19
ⓃⒶⓉⓘ ⓜⒺⓈⒻⓘⓃ :
New album Tewodros tadesse Coming soon!
2025-08-26 12:34:52
0
ermiyas_t
Ermiyas_t :
👍👍👍
2025-07-25 03:10:14
2
ermiyas_t
Ermiyas_t :
♥️♥️♥️
2025-07-25 03:10:16
2
112233teddy
😭😭😭 :
❤️❤️❤️
2025-07-25 06:01:58
2
birraclassics
BirraClassics :
🥰🥰
2025-07-25 16:13:52
2
aba.k7
abi :
❤❤❤
2025-07-25 20:16:57
2
bekam679
bekam :
🥰🥰
2025-07-25 07:29:44
1
richo.axum
Richo Axum :
🤒🤒🤒🤒🤒🤒🤒🤒🤒🤒🤒🤒🤒🤒🤒🤒🤒
2025-07-25 07:39:38
1
user632821451
@Anwar j.r :
😁
2025-07-26 19:42:01
1
makdagezahegn_
Makda✨ :
2025-10-17 06:25:25
0
gamo534
💓💓💓melkamu :
🥰🥰🥰🥰
2025-09-17 07:50:23
0
mezge51
mezge :
👍
2025-11-29 13:26:07
0
nasirumohammednur
Bor tolaa :
2025-12-03 08:40:00
0
jeti616
jeti :
❤️🥰
2025-09-13 08:00:27
0
daka5382
abi de :
🥰🥰🥰
2025-09-21 14:40:30
0
nasirumohammednur
Bor tolaa :
❤️
2025-12-03 08:41:50
0
sera2759
sera :
🥰
2025-09-27 16:53:12
0
yoooonas.g
yo :
😁
2025-07-28 15:23:42
0
To see more videos from user @musictube369, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About