@272127chris: #ፍልሰታ_ምን_ማለት_ነው? ➥ ሊቀ ማእምራን ደጉ ዓለም ለዚህ ጥያቄ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተዋል፤ "ፍልሰታ ማለት ፈለሰ /ተሰደደ/ ከሚለው ግስ የወጣ ነው።" ➥ ‹ፍልሰት› ማለት ደግሞ የተለያየ ትርጕም ቢሰጠውም ‹ፍልሰታ ለማርያም› ተብሎ ሲገለጽ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሚያልፈው ወደ ማያልፈው ዓለም ከመቃብር የወጣችበት (የተነሣችበት) ቀን ማለት ነው፡፡ ወይም ደግሞ ከሥጋዊው ዓለም ወደ መንፈሳዊው ዓለም የተሸጋገረችበት ማለት ነው፡፡›› ➥ ቀሲስ ስንታየሁ አባተም በተመሳሳይ መልኩ ስለ ፍልሰታ እንዲህ በማለት ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡ ➥ ‹ፍልሰታ ለማርያም› የሚለው የግእዝ ቃል ሲኾን ‹ፍልሰታ› ማለት ደግሞ ‹ፈለሰ› ከሚል ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ‹ፍልሰት› ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መሔድን (መፍለስን) ያመለክታል፡፡ እመቤታችን ካረፈች በኋላ የሥጋዋን መፍለስ አስመልክቶ ሐዋርያት የእመቤታችን ሥጋ የት እንደ ተቀበረ አላወቁም ነበርና እግዚአብሔር የእመቤታችንን ሥጋ እንዲገልጥላቸው የጾሙት ጾም ነው፡፡ ➥ ሐዋርያት ሁለት ሱባዔ ጾመው የእመቤታችንን ሥጋዋን ሰጥቷቸው ትንሣኤዋንና ዕርገቷን በማየት በረከት ያገኙበት ጾም ነው፡፡ ስለኾነም ምእመናን ፍልሰታ ለማርያምን ከልጅ እስከ አዋቂው በጾም በጸሎትና በመቍረብ በጋራ በፍቅር፣ በሰላም ያሳልፉታል፡፡›› ➥ ሊቀ ማእምራን ደጉ ዓለም ካሣ እንዳብራሩት ቅዱስ ዮሐንስ እመቤታችንን እንዲጠብቃት ከተደረገ በኋላ ሐዋርያት ‹‹የእመቤታችን ነገር እንዴት ነው?›› ብለው በጠየቁት ጊዜ ‹‹እመቤታችንማ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ናት›› ብሎ ነገራቸው፡፡ ➥ በዚህ ጊዜ ሐዋርያት እመቤታችን ከመቃብር መነሣቷንና ማረጓን ማየት አለብን፤ እንዴት ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ እንቀራለን ብለው በመንፈሳዊ ቅናት በመነሣሣት ነሐሴ አንድ ቀን በዕለተ ሰኞ ሁለት ሰባት ሱባዔ ያዙ፡፡ በዐሥራ አራተኛው ቀን ጌታችን የእመቤታችንን ሥጋ አንሥቶ ሰጣቸውና በጌቴሴማኒ ቀበሯት፡፡ እመቤታችን በ፷፬ ዓመቷ ጥር ፳፩ ቀን ዐርፋ ነሐሴ ፲፬ ቀን ተቀብራለች፡፡ ➥ ይኹንና ሐዋርያት ቢቀብሯትም ትንሣኤዋንና ዕርገቷን አላዩም ነበር፡፡ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያየው ሲቀብሯት ያላየው ሐዋርያው ቶማስ ነው፡፡ ቶማስ እንዲያስተምር ሕንድ አገር ዕጣ ደርሶት አስተምሮ በደመና ሲመለስ ነሐሴ ፲፮ ቀን እመቤታችን ስታርግ ሕዋ ላይ ተገናኙ በማለት ሊቀ ማእምራን ደጉ ያስረዳሉ፡፡ ➥ እንደ እርሳቸው አገላለጽ ምእመናን ጾመ ፍልሰታ የእመቤታችን ዕረፍት፣ ትንሣኤና ዕርገቷ የሚዘከርበት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ የኾነ ጾም ነው፡፡ በየዓመቱ ሕፃን አዋቂው ሳይቀር የእመቤታችን ፍቅር አድሮባቸው ጾሙን ይጾማሉ፣ ያስቀድሳሉ፤ ይቈርባሉ፡፡ ➥ የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው? ➥ የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ ሊቀ ማእምራን ደጉ ምላሽ ሲሰጡም "ኢትዮጵያ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የዐስራት ሀገር በመሆኗ እና ሕዝበ ክርስትያኑ ለእመቤታችን ልዩ ፍቅር ስላላቸው መሬት ላይ እየተኙ፣ ጥሬ እየበሉ በሰላም በፍቅር ይጾሙታል፡፡ ➥ ምእመናን ፍልሰታን ከሌሎች አጽዋማት በተለየ መልኩ መሬት ላይ እየተኙ ይጾሙታል፡፡ ይህ ደግሞ የእመቤታችን ፍቅር ስለሳባቸው ነው ፍቅር›› በማለት ያብራራሉ፡፡ ።።።።።።ወስብሐት ለእግዚአብሔር።።።።።።።።#ዘማርያም_ዘለቀ #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ፀንታ_ለዘለዓለም_ትኑር #ኢትዮጵያ_ለዘለዓለም_ትኑር🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #creatorsearchinsights

judit
judit
Open In TikTok:
Region: ET
Sunday 03 August 2025 07:10:26 GMT
133529
21997
121
2801

Music

Download

Comments

bubya64
1616 :
ቃለህይወት ያሰማልን
2025-08-04 05:33:13
24
user9119572696300
tsehy :
amen amen amen
2025-08-06 10:54:29
3
tegset.worket
tegset worket :
አሜን
2025-08-07 13:30:39
1
sitotaw.amaer
sitotaw Amaer :
አሜን አሜን አሜን አሜን
2025-08-06 08:59:45
3
user34198659313130
user34198659313130 :
አሜን
2025-08-06 10:50:20
4
abreham19670
kidist የመሬዋ :
እንኳን አደረሳችሁ🥰🥰🥰
2025-08-06 11:00:25
3
sone012_
ተዋህዶ@16 :
"ቃለ ህይወት ያሰማልን🙏
2025-08-05 19:29:15
3
enat.assefa4
Enat Assefa :
እንኳንአደርሳቹ እልልልልልልልልልልልልል
2025-08-05 19:41:28
3
user3727616687962
Teme :
ቃለ ህይወት ያሰማልን
2025-08-05 16:00:58
4
eliyastesema2
@yeshii20s2 :
ቃለ ህይወት ያሠማልን
2025-08-05 18:55:58
3
ye.mariyam212
𝑎𝑠𝑒 𝑦𝑒 𝑚𝑎𝑟𝑖𝑦𝑎𝑚 lji :
እናቴ🥰🙏🙏
2025-08-06 15:23:47
2
sigmajosi1
Yosef :
አሜን🥰
2025-08-06 17:20:31
2
endalkachew.gilgile
እንዳልካቸው :
አሜን አሜን አሜን🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2025-08-06 08:18:36
2
ermyas153
𝑒𝑟𝑚𝑦𝑎𝑠 :
አሜን
2025-08-06 06:18:33
2
melikamu.esayase
liji melki %1 :
ameni
2025-08-06 17:31:55
2
user54878031772050
ጆ🅽🅴 አ🆁🆂🅽🅰ል💪 :
አሜን
2025-08-06 07:25:58
2
ylkali.ylkali
ጎንደሬው ከበለሳ$23 :
አሜን
2025-08-05 19:09:49
2
nhomnhood
Nhom Nhood :
ድንቅ ነው
2025-08-03 19:13:28
5
hilinabayu349
hilinabayu349 :
እሜን ይማርን ይቅርም ይበለን🙏🙏🙏🙏
2025-08-04 21:38:21
5
hallelujha111
Raki🌑 :
Amen🙏🙏🙏
2025-08-05 15:15:56
2
kaleb.kasa1
Kaleb Kasa :
Amen Amen Amen
2025-08-05 15:27:34
2
bereketa70
Bereket :
ameni aneni ameni
2025-08-05 17:52:43
3
temesgtemesgenbetodelala
ተመሰጌን የቤቶች ደላላ :
እንኳንአደርሳቹ እልልልልልልልልልልልልል
2025-08-06 04:40:18
2
wariqu444
wariqu,444@❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤ :
አሜን አሜን አሜን🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2025-08-06 12:17:29
2
kalkidan122121
ቃልኪዳን መኳነንት :
አሜንንንንን
2025-08-07 18:27:28
1
To see more videos from user @272127chris, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About