@kibru_begena: «አለቃ ተሠማ ወልደ ዐማኑኤል (1875 - 1984)» (የበገና ቀደምቶቻችንን እንወቅ!) ``````````════◉❖◉═════ `````````` ▪︎ አለቃ ተሠማ፥ አቶ ደምሴ ደስታን፣ አቶ ታፈሰ ተስፋዬ እና መጋቤ ስብሐት ዓለሙ አጋን የመሰሉ ታላላቅ ሊቃውንትን ያፈሩ የበገና ባለውለታ ናቸው። ▪︎ ልጃቸው አባ ወርቅነህ ተሠማ ስመ ጥር በገና ደርዳሪ ነበሩ። ▪︎ በገናቸውን እየደረደሩ ታቦተ ጽዮንን ሲያጅቡ፥ በዓሉን ታድመው ከነበሩት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዓይን ውስጥ ይገባሉ። አዲስ አበባ መጥተው እንዲያስተምሩም ትእዛዝ ላኩባቸው። ▪︎ ይህ የምትሰሙት ዝማሬ (የዛሬ ዘመን/ዝናቡ መጣ) የአለቃ ተሠማ ሥራ ነው። ሙሉ ታሪካቸውን ከታች ያንብቡ። --- የበገናው ሊቅ አለቃ ተሰማ (አባ በገና) በቀድሞው የወሎ ክፍለ ሀገር እርቄ በምትባል አነስተኛ መንደር ውስጥ በ፲፰፻፸፭ ዓ.ም ነው የተወለዱት። አባታቸው ወልደ አማኑኤል ዘረፉ እናታቸው ደግሞ ወ/ሮ ሰገዱ ገብሬ ይባላሉ። አለቃ በዚህች በተወለዱባት አነስተኛ ከተማ ውስጥ ሆነው ከወላጆቻቸው ሳይርቁ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት የተማሩ ሲሆን እድሜያቸው ለአካለ መጠን ሲደርስም ሚስት አግብተው ቤት ንብረት አፍርተው ኖረውባታል። የመጀመሪያ ልጃቸውን ከወለዱ በኋላ ግን በበጌ ምድር ውስጥ ወደሚገኝ ደራገር ወደ ተባለ አካባቢ ሄደው ከዜማ መሳሪያዎች ሁሉ ቁንጮ የሆነውንና፣ ከኦሪት ዘመን ጀምሮ ስብሐተ እግዚአብሔር የሚደርስበትን፣ እርኩሳን መናፍስትን አባርሮ መረጋጋት የሚያድለውን የበገና ድርደራን ለመማር ተነሱ። አስበውም አልቀሩ ወደ በጌ ምድር ተጉዘው ከመንፈቅ ላለፈ ጊዜ ትምህርቱን አጥንተው ወደ ቀያቸው ተመለሱ። ነገር ግን ቤት ንብረት ወዳፈሩበት ቀያቸው ሲመለሱ ልቡናቸውን ፍቅረ እግዚአብሔር አሸፍቶት ስለነበር ጥቂት ጊዜ ቆይተው ፈጣሪያቸውን ብቻ በሙሉ ልብ የሚያገለግሉበትን የምንኩስና ሕይወት መርጠው በመመነን የቃል ኪዳኗ ታቦት ወዳለችበት ወደ ርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ሄዱ። በዚያም እግዚአብሔር አምላክንና እናቱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን እያመሰገኑ፤ ልክ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ያደርገው እንደነበረውም ታቦተ ጽዮንን በበገና ተግተው እያወደሱ ለሰባት ዓመታት ቆዩ። ከእነዚህ ዓመታት ቆይታ በኋላ ግን እርሳቸውን ከአክሱም ጽዮን የሚለይ አንድ አጋጣሚ ተፈጠረ። ዕለቱ የአክሱም ጽዮን ማርያም ዓመታዊ በዓለ ንግሥ የሚውልበት ኅዳር ፳፩ ቀን ነው። በዚህ ታላቅ በዓል ላይ ደግሞ ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በቦታው ተገኝተዋል። እናም በዚህች ዕለት አለቃ ተሰማ ከዚህ ቀደም እንደሚያደርጉት በገናቸውን እየደረደሩ ታቦተ ጽዮንን ሲያጅቡ በጃንሆይ ዓይን ውስጥ ይገባሉ። ጃንሆይም ታዲያ በቀለ ጢሞ የሚባል አገልጋያቸውን ልከው "ይህን በበገና የመዘመር ችሎታዎትን ወደ መሀል ሀገር አዲስ አበባ መጥተው እንዲያስተምሩ አዝዣለው በላቸው" ይሉታል። እርሱም ሄዶ ለአለቃ የተባለውን መልእክት ቢነግራቸው "እኔ ዓለምን ትቼ የመጣሁ መነኩሴ ነኝ እንደገና ወደ ዓለም መመለስ አይሆንልኝም" ብለው ይመልሱለታል። የንጉሡ አገልጋይ በቀለም ጠንከር ያለ መልሳቸውን በሰማ ጊዜ "አባታችን የንጉሥ ትዕዛዝ እምቢ አይባልም፤ ሲሆን ፈልገው በውድ አይ ካሉም በግድ ልንወስድዎ ታዘናልና እምቢ አይበሉ አላቸው።" አለቃ ተሰማም ከበዓሉ መጠናቀቅ በኋላ የንጉሡን ትዕዛዝ በማክበር ከመልእክተኞቹ ጋር አብረው ወደ አዲስ አበባ መጡ። በዚህም ማረፊያ ቤት ተሰጥቷቸው የእንግድነት ጊዜያቸውን ከጨረሱ በኋላ በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤትና በቀድሞው አምኃ ደስታ በአሁኑ የእንጦጦ መሰናዶ ትምህርት ቤት የበገና ድርደራን ማስተማር ጀመሩ። ይህን ጊዜ ነበር እርሳቸው ወደ ምናኔ ሲገቡ ድረውት የመጡት ልጃቸው ወርቅነህ ተሰማ "አባባ መኖሩን አለዚያም መሞቱን አውቄ እርሜን አውጥቼ ልመለስ" ብለው ከትውልድ ሀገራቸው ድረስ ለፍለጋ አዲስ አበባ የመጡት። በቅርቡ ያረፉት የአለቃ ልጅ አባ ወርቅነህ ተሰማ ስለዛች ከአባታቸው ጋር ስለተገናኙበት ቀን ሲያስታውሱ "አባባን ዳግም ሳገኘው ከሞት የተነሳ እንጂ ለዓመታት ተለያይተን የተገናኘን አልመስልህ ብሎኝ ነበር" ይላሉ። እናም ቁርጤን አውቄ እመጣለሁ ብለው ከሀገራቸው የወጡት አባ ወርቅነህ እንደገና ከአባታቸው መለየት ከብዷቸው ሚስታቸውንና ልጃቸውን ወደ አዲስ አበባ አምጥተው ከጎናቸው ሳይርቁ መኖር ጀመሩ። ይህን እንደገና የመወለድ ያህል ስሜት ያለው አዲስ ኑሮ መኖር ከጀመሩ ከዓመታት በኋላ ግን ዞሮ ዞሮ ከቤት ኖሮ ኖሮ ከሞት የሚቀር የለምና የእድሜ ባለፀጋው አባታቸው አለቃ ተሰማ ወልደ አማኑኤል በ፲፱፻፹፬ ዓ.ም በ፻፱ ዓመታቸው እነ መጋቤ ስብሐት አለሙ አጋን እና ደምሴ ደስታን የመሰሉ ታላላቅ ሊቃውንትን አፍርተው አረፉ። በዚህ ዘመን ከአለቃ ተሰማ ትምህርት የቀሰሙት ተማሪዎች መጋቤ ስብሐት ዓለሙ አጋ፣ አቶ ገብረ ኢየሱስ፣ አቶ አድማሱ ፍቅሬ፣ አቶ ታፈሰ ተስፋዬ፣ አቶ ደምሴ ደስታ፣ አቶ ሥዩም መንግሥቱና አቶ ተድላ ተበጀ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ˝መስተ-ሐምም˝ (ለተማርያም ዘውዱ ) ፳፻፲፫ዓ.ም ምንጭ፤ ቤተ እንዚራ ግራፊክስ እና አርትኦት፤ ክብሩ አየለ ════◉❖◉═════ ከአለቃ ተሠማ ዝማሬዎች መካከል፤ 1. ቀን የጣለ እንደሆን 2. እመቤታችን 3. የድሮ ዘመን 4. ሰላምታ 5. ከቶ አይቀርም ሞት 6. መኑ ተኅሥሡ 7. አንተ ነህ 8. ማን ይመራመር 9. ይበላሃላ 10. በእንተ ፍቅረ አብ 11. ቅዱስ 12. እግዚኦ 13. የዛሬ ዘመን (ዝናቡ መጣ) 14. ክርስቶስ ተንሥዓ እሙታን #ኅብር_በገና #creatorsearchinsights #foryou #begena #fyp

Kibru Begena - በገና
Kibru Begena - በገና
Open In TikTok:
Region: ET
Sunday 03 August 2025 16:27:44 GMT
72623
8490
150
995

Music

Download

Comments

thomasayele1
Thomas Ayele ቶ :
Thank you so much! እናቴ ስለ አባ በገና ሁሌ ትነግረኝ ነበር። አሳይቻት ደስ አላት። ታሪክ ተቀብሮ አይቀርም ለካ አለች።
2025-08-04 13:24:08
59
girumog
G :
እግዚአብሔር ይስጥህ እንደዚህ አይነት መዝሙር ስለጠቆምከን!
2025-08-14 22:09:11
0
kidanieselassie
አናንያ አዛርያ... :
ነፍስ ሔር!🙏
2025-08-13 16:24:51
0
getyemekuria
getye :
ሙሉ መዝሙሩን የት ማግኘት ይቻላል?
2025-08-04 06:02:34
4
dani12t21
dan_Begena :
በስመ አብ ቃል አጣዉለት! የመላእት ዝማሬ ያሰማልን🙏😇
2025-08-03 18:23:42
94
axumaxum4
Henok axum :
አረ በማርያም በምን ማግኘት ይቻላል ዝማሬውን
2025-08-05 08:20:48
2
besufkad710
Bešufķad Áďäņē :
ወይኔ እኔ በገና መደረደር ትምህርት ወሰጃለሁ ይህን አባት የዜማ በገና ድርድራ ግን ልችለው አልቻልኩም እናም ልቤን በጣም ነው እማሚያረስልሰው ወይኔ ጉዴ የአምላክ ድንቅ ስራ ግሩም ነው 🙏ለካስ ከላይ ሲታደሉት ነው🙏 በረከታቸው ጥበባቻው እውቀታቸው ይድረሰን🙏⛪️🙏
2025-08-03 18:22:40
14
hilawie13
WeldeHiwet :
ሙሉውን ልቀቅልን እንዲወርድ አድርገህ
2025-08-04 03:32:00
6
tictokk37
ፍቅር ብቻ። :
አማራ ፀጋ ያለው ህዝብ ነው ።
2025-08-07 11:19:34
0
dostyoski
ሎ'sif :
የዝማሬውን ሊንክ ይላኩልን ወንድማችን
2025-08-05 11:20:04
0
haileyosef15
ዮም ፯ :
አድርሱልኝ ለባለ ክራሮች
2025-08-07 14:53:20
2
_azi_g
zizi :
can I get the link please
2025-08-07 15:11:33
1
enkosenper21
Enqo Senper :
please Send to me ? 🙏🙏🙏
2025-08-05 08:33:19
1
bir.dddd
xyxy :
ግን ይህን የዘመረው ዲ/ን ስቡሕ ፈለገ መሠለኝ
2025-08-07 19:09:39
0
goldenx807
GoldenX :
I want full version 🥺🥺🥺
2025-08-05 00:14:29
0
sisbegena1221
sisaybegena :
እንደዚህ ያለ ፅሁፍ ይደገመን kibru🥰🥰🥰
2025-08-04 13:45:33
3
marsilas0716
marsila minilik :
እረ በማሪያም ሙሉውን ዝማሬ ለኔም ላክልኝ
2025-08-06 03:34:30
1
keradiyoo
ቅድስት🕊✝️🍀 :
እግዚአብሔር ይስጥልን ትልቅ ሰው ነው ያስተዋወቁን 🙏
2025-08-05 12:14:57
4
taddizyek
ታዲ ዘ ቅዱስ ሚካኤል J.A.K :
ይሄ መዝሙር የት እንደሆነ የማላውቀው ቦታ ይወስደኛል ያረጋጋኛል ይሰበስበኛል 🙏🙏
2025-08-08 19:43:58
1
shibi___aaaa
🦅coffee 🫧 :
link pls
2025-08-05 18:13:49
1
11.besu
mena :
ቃለ ህይወትን ያሰማልን
2025-08-11 07:20:28
1
hohite12
ኆኅተ :
አሁን ላለው የበገና ኅልውና ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረጉ አባት ናቸው! በገና ደርዳሪዎች አባቶቻችንን ለማወቅ መትጋት፣ ሥራዎቻቸውንም ማወቅ አለብን። ስንቶቻችን መዝሙሮቻቸውን እናውቃለን?
2025-08-03 16:37:07
14
kidanieselassie
አናንያ አዛርያ... :
ዝማሬ መላእክት ያሠማልን!🙏
2025-08-13 16:24:37
0
s_o_s_i0
SOSI :
mezmurn det lagegiew 🥺
2025-08-03 19:37:38
1
gizaw_get
G𝚒𝚣𝚊𝚠.G𝚎𝚝(🅗🅓🅒) :
እኔዝህን ቀለማት የፃፉ እጆች ይባረኩ።
2025-08-07 08:21:17
1
To see more videos from user @kibru_begena, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About