@melakufekadu1: የድምፅ ብክለት (nuisance) ይርጋ ******** የክርክሩ ባህርይ የሚያሳየው የአመልካች ጥያቄ በይዞታቸው ላይ የተፈጠረው ሁከት እንዲወገድላቸው ሳይሆን የማሽኑ ድምጽ የፈጠረባቸው ረብሻ እንዲወገድላቸው ነው:: የማሽኑ ድምጽ ሥራው እስከተሰራ ድረስ የሚቀጥል መሆኑም ግልጽ ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ የብየዳው ሥራ ከተጀመረ በኋላ የጊዜ ማለፍ ሁኔታ መኖር በድምጽ ሁከት ተፈጥሮብኛል በማለት ክስ ለማቅረብ የሚገድብ አይደለም፡፡ ዋናው ቁልፍ ነገር ድምፁ ከመጠን በማለፍ ረብሻ መፍጠሩን ማረጋገጥ ነው፡፡ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1225 ስር የተመለከተው ድንጋጌ ዓይነተኛ ዓለማውም ባለሃብቱ በመብቱ በሚገለገልበት ጊዜ የጎረቤቱ ርስት ጥቅም የሚቀንስበትን ወይም የሚጎዳበትን ማናቸውንም ከመጠን ያልፈ ነገር ከመስራት መከልከል ነው፡፡ አንድ የተፈጠረ የድምጽ ብክለት እንዲቀጥል የሚደረገበት የሕግ አግባብ የለም፡፡ ተከራካሪ ወገኖች የጠቀሱትን ድንጋጌ ብቻ በመያዝ ለፍሬ ጉዳዩ አግባብነት የሌለውን ድንጋጌ በመያዝ ውሳኔ መስጠት የዳኝነት አካሄድ የሚፈቅደው አይደለም፡፡ ለጉዳዩ አግባብነት ያለውን ድንጋጌ በመለየት ዳኝነት መስጠት የፍርድ ቤት የእለት ተእለት የስራ ድርሻ እንጂ የተከራካሪ ወገኖች አይደለም፡፡ ስለሆነም የስር ፍ/ቤት 1ኛ ተጠሪን በተመለከተ የጉዳዩ ይዘት በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1225 እና 1226 ድንጋጌ ስርየተመለከተውን የሚመለከት ሆኖ እያለ በይዞታ ላይ ሁከት ሲፈጠር የይርጋ ጊዜን የሚመለከተውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ውሳኔ መስጠቱ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሆኖ አግኝተናል፡፡በማለት አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥተዋል ። ሰ/መ/ቁ.42824 ..ቅፅ 11
መላኩ ፍቃዱ - Melaku Fekadu
Region: ET
Monday 11 August 2025 16:38:55 GMT
Music
Download
Comments
There are no more comments for this video.
To see more videos from user @melakufekadu1, please go to the Tikwm
homepage.