@musictube369: ቢጠይቁኝ መልስ የለኝ🍁 ነፃነት መለሰን እንዴት እንደምወዳት💝😍 የማያረጅ ውበት ከባድ ሚዛን ድምፃዊት ! ዘመን ተሻጋሪ በርካታ ጣፋጭ ስራዎችን የሰጠችን ፣ በየሚዲያው ላይ ስትንጠባጠብ የማናያት እዩኝ እዩኝ የማትል ስነ - ሥርዓት ሞልቶ የተረፋት ጨዋ አርቲስት ! አንዳንድ ሰው ዕድሜው ሲጨምር ውበቱም እጥፍ እንደሚጨምር በነፃነት መለሰ ነው ያረጋገጥኩት😁 ፈጣሪ ከዚህ የበለጠ ውበቱን ፣ ዕድሜና ጤናውን ይስጥሽ።🙌🧡 በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ underrated አርቲስት፣ ግን ስራዎቿ ዘመን ተሻጋሪ: ደሞ ዘፈኖቿን በአዲስ መልኩ ስትሰራቸው ልቅም አድርጋ ስለሰራቻቸው እንደ መልኳ ቆንጆ ናቸው! ነፂ ኮከብ ዘፋኝ ናት❣️ ይሄን ዘፈን ነፂ በመድረክ ላይ ከafro sound ጋር ስትጫወተው አለ ፈልጌ ስላጣሁት ነው ካገኘሁት post አደርገዋለው🙌☺️ ገና afro sound መመስረቱ ነበረ🖤 ድምጻዊት ነጻነት መለሰ ወደ ዘፋኝነቱ ገና ስትመጣ በኢትዮጵያ ሬድዮ ቀርባ የዘፈነቻቸው የመጀመሪያ ዘፈኖች እና አጭር ቃለ መጠይቅ ተደርጎላት ነበረ ነጻነት ድምጿን ያሟሸችው በእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ዘማሪ በመሆን ነበር። ከዛ የኢትዮጵያ ሬድዮ የዕሁድ ጠዋት ፕሮግራም አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ታደሰ ሙሉነህ እንግዳ በመሆን ችሎታዋን ለህዝብ አስደመጠች። በወቅቱ ካዜመቻቸው ዜማዎች መካከል በአፍሪካ ቋንቋ ሰዋህሊኛ፣ የኩኩ ሰብስቤን፣ የእንግሊዘኛና የህንድ ዜማዎች ነበሩ። በዕለቱ ፕሮግራሙን ይከታተል የነበረው የዋሊያስ "የሙዚቃ ባንድ ሙዚቀኛ ዮሀንስ ተኮላ ነጻነትን ቀድሞ በማስፈረም የባንዱ ብቸኛዋ እንስት ድምፃዊት ለመሆን አስቻላት። ነፃነት መለሰ ለብቻዋ 8ት ከሌሎች ጋር በጋራ 3 በአጠቃላይ 11 የሙዚቃ አልበሞችን ሰርታለች። ቃለመጠይቁን ያደረገላት ተወዳጁ የኢትዮጵያ ሬድዮ ጋዜጠኛ የነበረው ጋሽ ታደሰ ሙሉነህ ከነፃነት መለሰ በተጨማሪ ለሌሎች የቀደሙ ብዙ የሀገራችን አርቲስቶች ከፍተኛ ክብር ይሰጥ የነበረና ለእውቅናቸው ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረገ ጋዜጠኛ ነበረ። ነፍስ ይማር ጋሽ ታዴ! ነፃነት መለሰ ከህዝብ ጋር ያስተዋወቀቻት ድምፃዊት ጃኪ ሙር (Jackie Moore ) ጃኪ ሙር (Jackie Moore )ትባላለች :: አሜሪካዊት ድምፃዊ ናት:: Jackie Moore የተወለደችው እ.ኤአ.በ1946 in Florida United States .she is best known for her gold single 1970 song "Precious, Precious," Jackie Moore እ.ኤአ. በ1970ዎቹ በአሜሪካን ገናና ስም ከነበራቸው ምርጥ ድምጻዊያን መካከል አንዷ ነበረች:: በርካታ አልበሞችንና ነጠላ ዘፈኖችን ሰርታለች:: ጃኪ ሙር (Jackie Moore ) በ 72 አመቷ November 8, 2019 አርፋለች :: R.I.p . የዚህችን እንስት ድምፃዊት ይህን “Precious, Precious," የተሰኝውን ዘፈንን አርብ አርብ listeners choice በሚል የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ደጋግማ ትሰማለች:: ከዚያም ይህንን ዘፈን አጥንታ በመዝፈን ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መስኮት ብቅ አለች:: በህዝብ ዘንድም እውቅናን አገኝች:: ለዛሬ ታዲያ የዚችን ዕንቁ ተወዳጅ ሙዚቃ "ቢጠየቁኝ መልስ የለኝ"ን ጋብዝኳቹ🥰 🗣ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🙌🙏 @musictube 🇪🇹 #fyp #ቢጠይቁኝመልስየለኝ #ነፃነትመለሰ #musictube369 #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
Region: ET
Tuesday 12 August 2025 21:24:25 GMT
Music
Download
Comments
Teddy :
Noo ያሬድ ተፈራ ነው ያቀናበርው Take 3 ነው
2025-08-15 18:37:36
2
sisኮ :
ይሄን ሙዚቃ ያቀናበረው ያሬድ ተፈራ ነው 🙏 በኃላ ዜማ ላስታስ ባንድ(እነ ኤልያስ መልካ) በኢቲቪ ስቱዲዬ ድጋሚ ሰርተውታል
2025-08-13 14:16:16
3
Almi Queen :
betam mirit music new
2025-08-15 10:30:52
1
deli :
siwedish
2025-08-14 18:48:10
1
ከ_ቢ_ር ✍️ :
ነፂኮ❤
2025-08-14 08:42:26
1
Davidovic :
እውነትም ነፃነት ✌️✌️✌️
2025-08-12 21:30:08
1
Muree shebo :
👌
2025-08-13 00:18:57
1
mesfin :
🥰🥰🥰🥰🥰
2025-08-14 13:55:28
1
ani :
😁
2025-08-13 20:54:43
1
it's me😎 :
🥰🥰
2025-08-13 16:38:37
1
𝗖𝗵𝗼𝗽𝗽𝗮 ᡣ𐭩 :
🥰🥰🥰
2025-08-13 08:28:34
1
ABESELOM :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2025-08-13 07:51:27
1
ሩት :
❤❤❤
2025-08-13 07:38:28
1
DEREJE DIRA 7 :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2025-08-13 06:51:26
1
Mimi coca :
👌🥰
2025-08-13 05:29:35
1
የብሌን እናት💕💞 :
🥰🥰🥰👌👌😍😍
2025-08-13 04:16:02
1
ᴇᴢᴇᴅɪɴ :
@Neni19jul ✌
2025-08-12 22:29:32
1
Ermiyas_t :
❤️❤️❤️👍👍🙏♥️🎶🎶👏👏🙌🙏
2025-08-12 21:36:04
1
አሰ ማኛዉ❤ :
😁😁😁
2025-08-21 20:18:46
0
አሰ ማኛዉ❤ :
😭😭😭
2025-08-21 20:18:43
0
To see more videos from user @musictube369, please go to the Tikwm
homepage.