@4stloo:

a4
a4
Open In TikTok:
Region: ID
Tuesday 19 August 2025 11:11:51 GMT
5512
431
3
44

Music

Download

Comments

nffeu_
nau :
alm pacarku 💔
2025-09-17 03:06:51
0
c_cocomelon0
cocomelon :
pasti sakit banget ya kak?
2025-08-19 14:35:30
0
vely.22
vel :
😔
2025-08-29 23:41:12
0
To see more videos from user @4stloo, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

#የርዕሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን
#የርዕሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን "መንበረ ፀሐይ" የሚል ስያሜ የተሰጠበት ምክንያት ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ በእቴጌ ጣይቱ አሳሳቢነትና በአጼ ምኒልክ መልካም ፍቃድ የእንጦጦ ማርያም ቤተክርስቲያን ግንባታ ሲከናወን ቆየ፤ግንባታውም ለሦስት ዘመናት ተከናውኗ በ1878 ዓ/ም ስለተጠናቀቀ እቴጌ ጣይቱ አዲሷን ቤተክርስቲያን መስከረም 21 ቀን 1879 ዓ/ም በልዩ ድምቀትና በታላቅ ድግስ ሊያስመርቁ ተነሱ አጼ ምኒልክ ግን "ተይ ጣይቱ ክረምቱ ጨርሶ አይወጣምና ድግሱን ዝናብ እንዳያበላሸው" አሉ እቴጌ ጣይቱ ግን "ምርቃቱ በዛው ቀን ይሁን" አሉ ምኒልክም የእቴጌን ሃሳብ መጋፋት አይሆንላቸውምና እሺ አሉ፡፡ ለድግሱም እስከ 40 ኩንታል የሚይዙ የሊጥ ማቡኪያዎች፤ ለመጠጥም እጅግ የበዛ ጠጅ ተዘጋጀ፤ 5395 ከብቶችም ለእርድ ቀረቡ፤ በጣም ትልቅ ዳስም ተጣለ፡፡ ይህ ሁሉ ነገር ከተዘጋጀ በኋላ ግን በዋናው የድግስ ዕለት ዋዜማ አርብ መስከረም 20 ቀን 1879 ዓ/ም ታላቅ ደመና ሆነ፡፡ የዝናብ ካፊያም ማንጠባጠብ ጀመረ፤ ቦታውም ተራራማ ነውና ዝናብ መጥቶ መመለሱ የማይታሰብ ነበር፡፡ በዚህም ጊዜ እቴጌ ጣይቱ፣ መኳንንቱና አገልጋዮቹም ተጨነቁ ይሄ ሁሉ ድግስ መበላሸቱ ነው አሉ፡፡ አጼ ምኒልክ ግን ጸሐፊ ትዕዛዝን ጠሩ እመቤታችን ዝናቡን ትመለሰው ዘንድ "ይድረስ ለቅድስት ድንግል ማርያም ....ከምኒልክ" ሲሉ ደብዳቤ አጻፉ፡፡ ካህንም አስጠርተው ደብዳቤውን በእመቤታችን ታቦት ላይ እንዲያስቀምጠው ነገሩት ፡፡ካህኑም ምኒልክ እንዳሉት ደብዳቤውን ታቦቱ ላይ ሲያረገው ዝናቡም ደመናውም ጠፋ፡፡ ድግሱም እስኪጠናቀቅ ቀናቱ ሁሉ ብሩህ ሆኖ በመልካም ሁኔታ አለፈ፡፡ በዚህም ምክንያት የቤተ ክርስቲኗ ስያሜ "መንበረ ፀሐይ" መባሉን ታሪክ ያወሳልናል፡፡

About