@todaynews200: Preschool labeled sleepy sticker’s by teachers Parents:it’s a crime #foryou #news #fyp

user5912501784962
user5912501784962
Open In TikTok:
Region: US
Friday 12 September 2025 16:50:50 GMT
2235
61
0
3

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @todaynews200, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

'አይበጅም ወይ'👌☺️ ✨አበበ መለሰ እና ይልማ ገብረአብ በኢትዮጲያ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ መተኪያም መለኪያም በቀላሉ የማይገኝላቸው እንደወይን እየቆዩ በሄዱ ቁጥር ጣእሙ የሚጨምር ተወዳጅ ስራ የሰሩ መልካም የጥበብ ገበሬዎች ናቸው። በተለይ ላለፉት 35 ዓመታት የኢትዮጲያን ሙዚቃ ተሸክመው ዘመን እንዲሻገር ትልቅ ዋጋ ከከፈሉት የጥበብ ሰዎች መካከል አበበና ይልማ ቅድሚያውን ይይዛሉ።ከሰባዎቹ መጀመሪያ እስከ ሰማኒያዎቹ አጋማሽ ድረስ ለወጡ ስኬታማ ድምጻዊያን የሞያው ውሃ ልክ ሆነው ያቆሟቸው እነዚህ ጥንድ የጥበብ ገበሬዎች ናቸው።🙌🥰 ✨ውድ ቤተሰቦቼ  የኢትዮጲያ ሙዚቃ እንደዛሬው ዘፋኙ በ 4 ጋርድ ሙዚቃው በአንድ ኦርጋን የመታጀብ ደረጃ ከመድረሱ በፊት አበበ መለሰ፣ ይልማ ገብረአብ እና ሮሃ ባንድ በጋራ የከፈሉት ዋጋ ጥሩ ስራ በዘመን የማይገደብ ለመሆኑ ምስክር ነው።  ዛሬ እንደተለመደው ስለ ታላቁ ይልማ ገብረዓብ የገጣሚነት ብቃትና ችሎታ የተወሰነ ነገር ለማንሳት እሞክራለሁ። 🙏 ይህም ውስን ዳሰሳዬ በኔ የግዜና የአቅም እጥረት የተገደበ እንጂ የይልማ የብቃት መለኪያ ተደርጎ እንዳይቆጠርብኝ አደራዬ ጥብቅ ነው። ታላቁ ገጣሚ ይልማ ከጻፈውም ከሚጽፈውም በላይ ብዙ ነው። ትልቅ ነው።  ከተወዳጁ ገጣሚ ይልማ ገብረአብ ጥልቅ የንፅፅር ስንኞች ውስጥ በኤፍሬም ታምሩ የ1978 ስራዎች ውስጥ የተካተቱትን በጥቂቱ ልግለፅ። በዚህ የኤፍሬም አልበም ውስጥ ወለባ በተሰኘ ዘፈን ውስጥ ከተካተቱት ስንኞች መካከል አንዱ የንጽጽር ግጥም እንዲህ ይላል። “የአጋም እሾህ በቅሎ እግሬን ቢወጋው አንቺ ብትለይኝ እቴ በነጋው ለእግሬም ሀኪም አልል ላንቺም አማላጅ እሾህን በእሾህ ነው ሴትን በሴት ልጅ ይላል። በህክምና ከበሽታው መድሃኒት እንደሚሰራ ሁሉ በዚህ ስንኝ ውስጥም ንጽጽሩ በግልጽ ተቀምጧል። በዚሁ ስራ ውስጥ ስለፍቅሩ ፅናት የጠቀሳቸውን እማኞች በመጥራት እንዲህ ይላል። “ስላንቺ እያሰብኩኝ ቆሜ ለማደሬ ኮከብ ጨረቃ ነው እማኝ ምስክሬ ይላል። ለማንም በማያዳሉና ያዩትን እውነት ብቻ በሚመሰክሩ ከእኛ ጋር ማን ወቶ ነበር ብለው ማየት በሚችሉት አስመሰክራለሁ በሚል ነው የፍቅሩን ፅናት የገለፀው።  የታላቁ ገጣሚ ይልማ ገብረአብ ጥልቅ ስንኝ ወደ ሚዳሰሱበት ወደ ፀጋዬ እሸቱ ስራዎች ላምራ። መረዳዳት ቢኖር በተሰኘው ፀጋዬ፣ አረጋኸኝ፣ ነዋይ በጋራ ባወጡት አልበም ከተካተቱት የፀጋዬ እሸቱ ስራዎች ውስጥ “ጥንትም ላይሆንልሽ” የተሰኘ የዚህ ታላቅ ደራሲ ስራ ይገኛል። በዚህ ስራ ውስጥ ትልቅ መልእክት አለ። በተለይም ስለቅንነት ፣ልዩነትን በፍቅር ስለመፍታት፣ ልዩነታችን ሌላውን በማጥፋት ወይም በማስወገድ ሳይሆን የተሻለ ፍቅርና መተሳሰብን በማሳየት የተሻለ ፍቅርን ያ ሳለፍንበትን ጊዜ አስበን መልካም መመኘት ይገባል የሚል ስንኝ ተካቷል። “አንዱ ብሩን ሲቸር ሌላው ጌጥ ያመጣል የኔ ልብ ሃብታም ነው እምነቱን ይሰጣል ዛሬም አለኝ ፍቅር የያዝኩት ሰስቼ መቸም በዚህ በኩል አላውቅም ደኽይቼ። ፍቅር ፈጣሪ ነው ከፈጣሪ በላይ ምን ትልቅ ሃብት አለ የሚል ትርጉም ይሰጠኛል ለኔ! ፍቅር ና አፍቃሪነት የፈለጉትን በማግኘት ብቻ ሳይሆን በማጣትም መገለፁን በዚሁ ስራ ውስጥ እናገኛለን። “ዛሬ እኔን ዘንግቶ ገላሽ ሰው ቢለምድም ትላንት ወደሽኛል ክፉሽን አልፈቅድም
'አይበጅም ወይ'👌☺️ ✨አበበ መለሰ እና ይልማ ገብረአብ በኢትዮጲያ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ መተኪያም መለኪያም በቀላሉ የማይገኝላቸው እንደወይን እየቆዩ በሄዱ ቁጥር ጣእሙ የሚጨምር ተወዳጅ ስራ የሰሩ መልካም የጥበብ ገበሬዎች ናቸው። በተለይ ላለፉት 35 ዓመታት የኢትዮጲያን ሙዚቃ ተሸክመው ዘመን እንዲሻገር ትልቅ ዋጋ ከከፈሉት የጥበብ ሰዎች መካከል አበበና ይልማ ቅድሚያውን ይይዛሉ።ከሰባዎቹ መጀመሪያ እስከ ሰማኒያዎቹ አጋማሽ ድረስ ለወጡ ስኬታማ ድምጻዊያን የሞያው ውሃ ልክ ሆነው ያቆሟቸው እነዚህ ጥንድ የጥበብ ገበሬዎች ናቸው።🙌🥰 ✨ውድ ቤተሰቦቼ የኢትዮጲያ ሙዚቃ እንደዛሬው ዘፋኙ በ 4 ጋርድ ሙዚቃው በአንድ ኦርጋን የመታጀብ ደረጃ ከመድረሱ በፊት አበበ መለሰ፣ ይልማ ገብረአብ እና ሮሃ ባንድ በጋራ የከፈሉት ዋጋ ጥሩ ስራ በዘመን የማይገደብ ለመሆኑ ምስክር ነው። ዛሬ እንደተለመደው ስለ ታላቁ ይልማ ገብረዓብ የገጣሚነት ብቃትና ችሎታ የተወሰነ ነገር ለማንሳት እሞክራለሁ። 🙏 ይህም ውስን ዳሰሳዬ በኔ የግዜና የአቅም እጥረት የተገደበ እንጂ የይልማ የብቃት መለኪያ ተደርጎ እንዳይቆጠርብኝ አደራዬ ጥብቅ ነው። ታላቁ ገጣሚ ይልማ ከጻፈውም ከሚጽፈውም በላይ ብዙ ነው። ትልቅ ነው። ከተወዳጁ ገጣሚ ይልማ ገብረአብ ጥልቅ የንፅፅር ስንኞች ውስጥ በኤፍሬም ታምሩ የ1978 ስራዎች ውስጥ የተካተቱትን በጥቂቱ ልግለፅ። በዚህ የኤፍሬም አልበም ውስጥ ወለባ በተሰኘ ዘፈን ውስጥ ከተካተቱት ስንኞች መካከል አንዱ የንጽጽር ግጥም እንዲህ ይላል። “የአጋም እሾህ በቅሎ እግሬን ቢወጋው አንቺ ብትለይኝ እቴ በነጋው ለእግሬም ሀኪም አልል ላንቺም አማላጅ እሾህን በእሾህ ነው ሴትን በሴት ልጅ ይላል። በህክምና ከበሽታው መድሃኒት እንደሚሰራ ሁሉ በዚህ ስንኝ ውስጥም ንጽጽሩ በግልጽ ተቀምጧል። በዚሁ ስራ ውስጥ ስለፍቅሩ ፅናት የጠቀሳቸውን እማኞች በመጥራት እንዲህ ይላል። “ስላንቺ እያሰብኩኝ ቆሜ ለማደሬ ኮከብ ጨረቃ ነው እማኝ ምስክሬ ይላል። ለማንም በማያዳሉና ያዩትን እውነት ብቻ በሚመሰክሩ ከእኛ ጋር ማን ወቶ ነበር ብለው ማየት በሚችሉት አስመሰክራለሁ በሚል ነው የፍቅሩን ፅናት የገለፀው። የታላቁ ገጣሚ ይልማ ገብረአብ ጥልቅ ስንኝ ወደ ሚዳሰሱበት ወደ ፀጋዬ እሸቱ ስራዎች ላምራ። መረዳዳት ቢኖር በተሰኘው ፀጋዬ፣ አረጋኸኝ፣ ነዋይ በጋራ ባወጡት አልበም ከተካተቱት የፀጋዬ እሸቱ ስራዎች ውስጥ “ጥንትም ላይሆንልሽ” የተሰኘ የዚህ ታላቅ ደራሲ ስራ ይገኛል። በዚህ ስራ ውስጥ ትልቅ መልእክት አለ። በተለይም ስለቅንነት ፣ልዩነትን በፍቅር ስለመፍታት፣ ልዩነታችን ሌላውን በማጥፋት ወይም በማስወገድ ሳይሆን የተሻለ ፍቅርና መተሳሰብን በማሳየት የተሻለ ፍቅርን ያ ሳለፍንበትን ጊዜ አስበን መልካም መመኘት ይገባል የሚል ስንኝ ተካቷል። “አንዱ ብሩን ሲቸር ሌላው ጌጥ ያመጣል የኔ ልብ ሃብታም ነው እምነቱን ይሰጣል ዛሬም አለኝ ፍቅር የያዝኩት ሰስቼ መቸም በዚህ በኩል አላውቅም ደኽይቼ። ፍቅር ፈጣሪ ነው ከፈጣሪ በላይ ምን ትልቅ ሃብት አለ የሚል ትርጉም ይሰጠኛል ለኔ! ፍቅር ና አፍቃሪነት የፈለጉትን በማግኘት ብቻ ሳይሆን በማጣትም መገለፁን በዚሁ ስራ ውስጥ እናገኛለን። “ዛሬ እኔን ዘንግቶ ገላሽ ሰው ቢለምድም ትላንት ወደሽኛል ክፉሽን አልፈቅድም" ያለፈን ጥሩ እያሰቡ ለነገ ክፉ አለመሆን ከዚህ በላይበምን ይገለፃል? ወደ ቴዎድሮስ ታደሰ የይልማ ገብረአብ ተወዳጅ ስንኞች ስናልፍ፦ ዛሬ የጋበዝኳችሁን 'አይበጅም ወይ' ለኔ እጅግ በጣም በግጥሙ ልህቀት ከፊት የማስቀምጠው ሆኖ በተጨማረሪም ቴዎድሮስ ታደሰ 1978 ባሳተመው አልበም ውስጥ በተካተተው “መዋደዳችንን ”በተሰኘው ስራ ውስጥ ያለው ስንኝ የውበትን አላፊነት የገላን ረጋፊነት እና ጊዜያዊነት የፍቅርን ሃያልነትና ዘላቂነት የሚገልፀው ስንኝ እንዲህ ይላል። “ውሎ እያደር አካል ሰረገላው መሰስ ይላል በቁንጅና በራስ ገላ ማመኑ እንደ ሰባራ ምርኩዝ ይጥላል ስለ መውደድ ደፋም ቀናም ያለ ይጠቀማል መቼም ቢሆን የእኩል ፍቅር የእኩል ነው ደገፍገፍ እንዳረገ ይከርማል ሌላው የቴዎድሮስ ታደሰና አሰፉ ደባልቄ በጋራ ባሳተሙት አልበም ውስጥ ከተካተቱት የቴድሮስ ታደሰ ስራዎች አንዱ “አጉል ተቆራኝቶኝ” ውስጥ የተካተቱት ስንኝ እንዲህ ይላል። “ተናደጂ ልታገስ ቁጣሽን ላብረደው እዳው ተችሎነው ሰው የሚወደደው በዚህ ስንኝ ውስጥ ያለው መልእክት ለኔ እንደሚገባኝ በሚፈልጉት ውስጥ ያለን የማይፈለግ ነገር መቀበል ነው የማፈቀር መለኪያው! ለምሳሌ ፈጣሪ የሰውን ልጅ ሲወድ እዳውን ችሎነው የወደደው። ሌላው ቀርቶ ከባንክ ስንበደር እንኳ እዳውን ችለነው የወደድነውን ብድር የምንወስደው! በሌላ የቴድሮስ ታደሰ የ1981 ስራ ውስጥ “የጎኔ ባላ ማገር” በተሰኘው ስራ ውስጥ "ቢቀጥንም አንገት ነው እራስን ከቻለ" ይላል። የስራን ታላቅነት በራስ መተማመንን ለመግለፅ ከዚህ የተሻለ ስንኝ ፈልጌ አጣሁ ፤ ስለ ይልማ የበርካታ አመታት የሙያ ብቃትና ቆይታ ሳስብ ሁሌ የምገረመው እስከዚህ ዘመን ክብሩን ጠብቆ ደረጃና አቅሙ ሳይዋዥቅ ከሙሉቀን መለሰ"ይረገም" እስከ ቴዎድሮስ ካሳሁን ፀባየ ሰናይ መዝለቁ ነው። ምክንያቱም 35 ዓመት በሞያ ከነብቃት መቆየት ቀርቶ በህይወት መኖር ከባድ የሆነበት ዘመን መሆኑን ልብ ይሏል። ሁሌም ይህን ሳስብ ስለ ይልማ ታላቅነት እገረማለሁ።... ስለ ታላቁ ይልማ ገና አላበቃሁም እመለሳለሁ🙏 ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡 #fyp #ቴዎድሮስታደሰ #አየበጅምወይ #musictube369 #ethiopianmusic

About