@yetariekimahideri: ሞት ሰራቂው ሞተ "ሞት ሰራቂው ሞተ" በጣም የሚደንቅ ታሪክ! በአንድ ወቅት አንድ ሰው የፈጣሪን ተአምር ለመመስከር እሩቅ አገር ለመሔድ ከተሳፋሪዎች ጋር በአውቶብስ ጉዞ ይጀምራል። ጉዞ ከተጀመረ በኋላ ግን መንገድ ላይ አንድ ከተማ ውስጥ ተሳፋሪው በሙሉ ምሳ ለመብላት ይወርዳል። ......ከተሳፋሪዎቹ መሐከልም አንዱ ወደ አንድ ምግብ ቤት ይሔድና ምሳውን ከበላ በኋላ ለመክፈል ቦርሳውን ሲፈልግ ያጣዋል። ......መሰረቁንም ከተረዳ በኋላ ለምግብ ቤት ባለቤቱ የደረሰበትን ስርቆት አስረድቶ በነበረበት ከተማ የሚያውቀው ዘመድ ስለነበር ገንዘብ አምጥቶ እንደሚከፍል ተናግሮ ገንዘብ ይዞ መጥቶ ይከፍልና ወደ አውቶብሱ ሲሔድ አውቶብሱ ለካ ጠብቆ ጠብቆ የደረሰበትን ነገር ስላላወቀ ትቶት ሔዷል። ........ ሠውየውም ገንዘቡም ተዘርፎ አውቶብሱም ጥሎት መሔዱ እየገረመው "#ይሄ_ፈተና_ነው_ሰይጣን_እፈር እኔ እንደሆነ ከአገልግሎት አልቀርም ብሎ ብዙ ከተንከራተተ በኋላ በሌላ አውቶብስ ተሳፍሮ ጉዞ ይጀምራል። . ...... በመንገድ ላይም አንድ ትልቅ ገደል ውስጥ የገባ አውቶብስ ያያል። ከተሳፋሪዎቹም የተረፈ ሰው አለመኖሩ ይመለከታል። ደነገጠ። ....በጣም አዝኖ እያለም ወርዶ አውቶብሱን በደንብ ሲያየው እርሱ ተሳፍሮባት የነበረችውና ጥላው የሔደችው አውቶብስ መሆንዋን ይረዳል። ....በጣም ገርሞት ለካ አውቶብሱ ጥሎኝ የሔደው #ለበጎ_ነው በሚል ፈጣሪውን እያመሠገነ ጉዞ ይጀምራል። የሚያገለግልበት ቦታ ደርሶም ስለተደረገለት ነገር ለአንድ ሣምንት እዛው ፈጣሪውን ሲያመሰግን ሰንብቶ ወደ ቤቱ ሲመለስ መኖሪያ ቤቱ ድንኳን ተተክሎ ያያል። .....ምን ተፈጥሮ ይሆን? በሚል ጠጋ ብሎ ሲመለከት ለቅሶ ነው። ጎረቤቶቹ በሙሉ ደንግጠው እርሱን ሲያዩት ያያል። ሠውየውም "ማን ነው የሞተው?" ብሎ ይጠይቃል። እነርሱም "አንተ" ይሉታል። እርሱም እንዴት እኔማ ይሄው አለሁ አይደል። ይላል። የእርሱን በሕይወት መምጣት የሰሙ ቤተሰቦቹም ማመን አቅቷቸው እየመጡ ይጠመጠሙበታል። ሐዘኑም ወደ ደስታ ይለወጣል። ሰውየውም ቤተሰቡም ጎረቤቱም ረጋ ብለው ስለተፈጠረው ሁኔታ ያወራሉ። ...ለካ አውቶብሱ ሲገለበጥ አደጋው የከፋ ስለነበር የሰዎቹ ማንነት በመልክ መለየት ስላልተቻለ የሟቾች ኪስ ፓሊስ እየበረበረ ማንነታቸውን መለየት ሲጀምር የሰውየውም የጠፋው ቦርሳ አንዱ የሰረቀውና አንዱ ሟች ኪስ ውስጥ ይገኛል። ...ፓሊስም በመታወቂያው መሠረት ለሰውየው ቤተሰቦች መርዶ ይነገራል። ለቤተሰቡም በተዘጋጀ አዲስ የመቃብር ቦታ ይቀብሩታል። ለካ ሠውየው ነው ተብሎ የተቀበረው #ሌባው ነው። ሁሉም ሠው ይህን ሲሰማ ይገረማል። ከሰወችም መካከል አንዷ ልጁ "የአንተ አዲሱ መቃብር የተቀበረው ሌባው ነው። አንተ መቃብር ላይ ሌባ አይቀበርም። #ይውጣ።" ስትል ....ሠውየው አንድ አስገራሚ ነገርተናገረ " አይሆንም ሌባውን ሞቴን የወሰደልኝ ሞቴን የሰረቀኝ ባለውለታየ ነው። እርሱ ቦርሳየን ሰርቆኝ ለምሳ መክፈያ ብር ፍለጋ ባልሔድ ኖሮ አውቶብሱ አያመልጠኝም ነበር። እኔም ሟች ነበርኩ። አትንኩት።" ነበር ያለው። ፈጣሪ ሲፈቅድ ለካ ሞትም ይሰረቃል። አይገርምም? የሰውየው ንግግር በጣም ይገርማል። "ነገር ሁሉ ለበጎ ነው። "ሁሌም በመንገዱ ፈጣሪውን ያስቀደመ አያፍርም! #creatorsearchinsights

የታሪክ ማህደር
የታሪክ ማህደር
Open In TikTok:
Region: ET
Wednesday 17 September 2025 06:56:35 GMT
6061
271
5
95

Music

Download

Comments

love.l164
(ስቕታ ጥንካረ እዩ💪👌) :
ዋው የሚገርም ነው🥰🥰
2026-05-08 12:27:50
1
jemal.jemal017
◊ማ◍ራ◎ኪ◉ዉ➥ :
2
2026-03-21 11:15:01
0
abdulshukur770
እመን እንጂ አትፍራ :
❤️❤️❤️
2026-04-27 16:23:16
1
batii122
BAATii❤️ያHalaba💚qalii ነኝ♥️🌶️ :
🥰🥰🥰
2026-01-24 15:35:04
0
baeletaasefaa
Zu 23🔒 :
😭😭😭
2026-06-26 18:00:07
0
To see more videos from user @yetariekimahideri, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About