@rossazza03:

Ross Azza
Ross Azza
Open In TikTok:
Region: ID
Friday 19 September 2025 12:10:02 GMT
254
16
0
2

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @rossazza03, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

👉👉​ዘኬዎስን ዛፍ ላይ እንዲወጣ ያደረጉት ሦስት መንፈሳዊ ምክንያቶች 👉​1. ዓይኖቹን ክርስቶስን ለማየት ናፍቀዋል ​
👉👉​ዘኬዎስን ዛፍ ላይ እንዲወጣ ያደረጉት ሦስት መንፈሳዊ ምክንያቶች 👉​1. ዓይኖቹን ክርስቶስን ለማየት ናፍቀዋል ​"ኢየሱስንም የትኛው እንደ ሆነ ሊያይ ይሻ ነበር፤ ቁመቱም አጭር ነበረና ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ አቃተው።" (ሉቃስ 19፥3) ​ዘኬዎስ ክርስቶስን ለማየት የነበረው ጉጉት ዝም ብሎ የሰውን ዝና ለመስማት የመጣ የዋዛ ፍላጎት አልነበረም። እርሱ የነፍሱን መድኃኒት፣ የሕይወቱን ቀያሪ ለማየት ጓጉቶ ነበር። ቁመቱ አጭር መሆኑና የሕዝቡ ብዛት እንቅፋት ቢሆኑበትም፣ ፍቅሩና ናፍቆቱ ግን ካጋጠሙት እንቅፋቶች በላይ ነበሩ። እኛም ዛሬ በሕይወታችን ያሉትን የፈተና፣ የትዕቢትና የኃጢአት "እልፍኝ ሕዝቦች" አልፈን ክርስቶስን ለማየት የሚናፍቅ መንፈሳዊ ዓይን ሊኖረን ይገባል። 👉👉​2. ጆሮቹ የክርስቶስን ድምጽ ለመስማት ጓጉተዋል ​"በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል።" እንዳለ(ዮሐ 10፥27) ​ዘኬዎስ በደመነፍስ ዛፍ ላይ ቢወጣም፣ ልቡ ግን የእረኛውን ድምፅ ለመስማት ተዘጋጅቶ ነበር። ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዛፉ ሥር ደርሶ ቀና ብሎ ሲመለከተውና "ዘኬዎስ ሆይ፥ ዛሬ በቤትህ ልውል ይገባኛልና ፈጥነህ ውረድ" (ሉቃስ 19፥5) ብሎ በስሙ ሲጠራው፣ ዘኬዎስ ያንን ድምፅ በደስታና በታዛዥነት ተቀበለው። ስሙን የሚያውቀውን፣ ማንም ሳይወደው የወደደውን የጌታን ድምፅ ለመስማት የነበረው ጉጉት ወዲያውኑ ከዛፉ ላይ አውርዶታል። 👉👉​3. ክርስቶስ ወደ ቤቱ ከመግባቱ በፊት ቀድሞ ወደ ልቡ ጋብዞታል ​"እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።" (ራእይ 3፥20) ​ኢየሱስ ወደ ዘኬዎስ ቤት ከመሄዱ በፊት፣ ዘኬዎስ አስቀድሞ በልቡ ዝግጅት አድርጎ ነበር። ጌታ "በቤትህ ልውል ይገባኛል" ባለው ጊዜ፥ መጽሐፉ "ፈጥኖም ወረደ በደስታም ተቀበለው" ይላል (ሉቃስ 19፥6)። ​ጌታን በደስታ መቀበል የሚቻለው አስቀድሞ በልብ ዙፋን ላይ ሲነግሥ ነው። ዘኬዎስ ጌታን ወደ ልቡ ስላስገባው፣ ውጫዊው ሕይወቱ ወዲያውኑ ተቀየረ። የሰረቀውን አራት እጥፍ ለመመለስ፣ ከሀብቱ እኩሌታውን ለድሆች ለመስጠት የወሰነው ጌታን በልቡ ስለገዛውና እውነተኛው የሰማይ ሀብት ስለገባው ነው። 👉👉ዘኬዎስ ለእኛ ያለው ትምህርት ምንድነው ​የዘኬዎስ ታሪክ ለእኛ ለክርስቲያኖች ትልቅ የተግሣጽና የብርታት ምንጭ ነው። ዛሬ እኛ ክርስቶስን ለማየትና ድምፁን ለመስማት ምን ያህል እየተጋን ነው?

About