@may.fano.19: ሰበር ዜና! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ዛሬም ለ5ኛ ቀን ድል በድል ሁኖ ቀጥሏል። 5ተኛ ቀኑን የያዘው ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) በታላቅ ድል ታጅቦ እንደቀጠለ ነው። ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር እና መብረቅ ክፍለ ጦር የተውጣጡ አሃዶች ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 9ኛ ሳሙኤል አወቀ ክፍለ ጦር አሃድ ጋር በመቀናጀት ትናንት ለዛሬ ሌሊት በመካነሰላም ግንባር የጠላትን ኃይል በመደምሰስ፣ በማቁሰል፣ በመበተን እና በመማረክ ከጥቅም ውጭ አድርገው መካነሰላም ከተማን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር አውለዋል:: በኦፕሬሽኑ የአድማ ብተና 23ተኛ ክፍለ ጦር በርካታ ኃይል የተደመሰሰ ሲሆን የመካነሰላም ከተማ አስተዳደር ሚሊሻ ፅ/ቤት አመራር የሆነው አቶ ሰይድ አብዬን ጨምሮ ሌሎች ባንዳዎች እስከወዲያኛው ተሸኝተዋል:: በድምሩ ከ45 ያላነሰ ጠላት የተደመሰሰ ሲሆን በርካቶች ቆስለዋል:: ውጊያው ሲጀመር ራሱን ለመከላከል አስቦ በአየር ማረፊያ፣ በለገአማራ ወንዝ እና በከተማይቱ መሀል በቡድን መሳሪያ የታገዘ ውጊያ የከፈተው ጠላት የጀግኖችን ክንድ ቀምሶ ከጥቅም ውጭ ሆኗል:: መካነሰላም ከተማ ውስጥ የሚገኘው የቦረና ማረሚያ ቤትን በመክበብ ፋኖ ባደረገው ትንቅንቅ በርካታ እስረኞችን ማስለቀቅም ተችሏል:: በዚሁ በመካነሰላም ግንባር ከትናንትት በስቲያ የኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር ጥላሁን ፈንታው ብርጌድ ኮሎኔል ሀብታሙ አሰፋን ጨምሮ ሌሎች 3 ባንዳዎችን መማረኩም ይታወሳል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 👉መስከረም /18/01/2018 ዓ.ም/አማራ/ኢትዮጵያ)
may fano 19)
Region: ET
Sunday 28 September 2025 14:15:26 GMT
Music
Download
Comments
There are no more comments for this video.
To see more videos from user @may.fano.19, please go to the Tikwm
homepage.