@afendi1978: ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ ------- ልዑል ራስ ተፈሪ መኮንን (የኋለኛው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሤ) ከልደቱ እስከ ሞቱ ድረስ ያለው የህይወት ታሪኩ በአግራሞት የተመላ ነው። በርካታ ጸሓፊዎች በታሪኩ ላይ ይወዛገቡበታል። አንዳንዶች ምንም ማስረጃ የሌላቸውን ጭብጦች ከርሱ ጋር ለማያያዝ ይሞክራሉ። የርሱን ታሪክ ለመቅበር እና ስብእናውንም ለማዋረድ ይሞክራሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ እርሱ የሰራቸውን ክፉ ድርጊቶች እየዘለሉ ደግ ደጉን ብቻ ያወሩለታል። ከዚህ ፈቅ የሚሉት ኢትዮጵያ በረጅም ክፍለ ዘመናት ያበቀለችው “ሙሉእ በኩለሄ” የሆነ ብቸኛ ንጉሧ ተፈሪ መኮንን እንደሆነ ይሰብካሉ። አልፎ ተርፎም “በሰው አምሳል የተፈጠረ አምላክ ነው” በማለት እርሱን የሚያመልኩ ወገኖች አሉ። በዚህች አጭር ሐተታ የተፈሪ መኮንንን ሙሉ የህይወት ታሪክ ይቅርና የሩቡን ሩብ እንኳ ላወጋችሁ እንደማልችል ይታወቀኛል። ሆኖም በሀረር ከተማና በሌሎችም የምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች በተፈሪ መኮንን ዙሪያ የሚነገሩ አፈ-ታሪኮችንና በሰነድ የተመዘገቡ እውነተኛ ወሬዎችን በጥቂቱ ላጋራችሁ እችላለሁ። ***** ***** ***** በተፈሪ ላይ ከሚነገሩት አፈ-ታሪኮች መካከል አንዱ ልደቱን የሚመለከተው ነው። ልጅ ተፈሪ ብስል ቀይና መልከ መልካም ከመሆኑም በላይ ከአባቱ ከራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጋር የመልክ መመሳሰል አይታይበትም። በዚህም የተነሳ የህንዳዊው ሙሐመድ ዓሊ ልጅ መሆኑ እስከ አሁን ድረስ ይነገራል። በርካታ ማሕበረሰቦች አፈ-ታሪኩን ለማስረገጥ እንደ ማስረጃ የሚመዙት ልደቱ የተፈጸመበትን ስፍራ ነው። ተፈሪ መኮንን ሀምሌ 16 ቀን 1884 ዓ.ል. ኤጀርሳ ጎሮ በተባለችው አነስተኛ ከተማ (ከሀረር በስተሰሜን ምስራቅ 45 ኪ.ሜ ያህል ራቅ ብላ የምትገኝ) ነው የተወለደው። ልዑል ራስ መኮንን በዘመኑ የሀረርጌ ገዥ የነበሩ ሲሆን ተቀማጭነታቸውም በሀረር ከተማ ነው። ታዲያ “የራስ መኮንን መቀመጫ በሀረር ከተማ ሆኖ እያለ ልጅ ተፈሪ ኤጄርሳ ጎሮ የተወለደው በምን ምክንያት ነው?” የሚል ጥያቄ ሲቀርብ በታሪክ ጸሐፊያን የሚሰጠው ምላሽ “ራስ መኮንን ሀገር ለማረጋጋት ወደ ጃርሶ ወረዳ (ኤጀርሳ ጎሮ) ተጉዘው እያለ ከርሳቸው ጋር የነበረችው ባለቤታቸው ምጥ ያዛትና ተፈሪን እዚያ ወለደችው” የሚል ነው። አንዳንድ የአፈ-ታሪክ ምንጮች እንደሚሉት ግን ተፈሪ በኤጀርሳ ጎሮ የተወለደው እናቱ (ወ/ሮ የሺ እመቤት ዓሊ) ከራስ መኮንን ጥቃት ለማምለጥ ከጃርሶ ኦሮሞዎች ዘንድ በጥገኝነት ገብታ በነበረበት ጊዜ ነው። እነዚሁ ምንጮች እንደሚሉት የተፈሪ እናት የራስ መኮንን ወዳጅ ከነበረው ህንዳዊው ሙሐመድ ዓሊ ጋር ድብቅ ግንኙነት ነበራት። ከዚህም ግንኙነት ልጅ ተፈሪ መኮንን ተጸነሰ። እያደር ሆዷ እየገፋ ሲመጣ ግን መሸበር ጀመረች። “ራስ መኮንን ከነቃብኝ ያጠፋኛል” ብላ ስለገመተችም ቅሌን ጨርቄን ሳትል ብንን ብላ ጠፍታ ወደ ጃርሶ ኦሮሞ የጎሳ መሪዎች ኮበለለች። ነፍሷንና ልጇንም ከራስ መኮንን ጥቃት እንዲታደጓቸው ተማጸነች። “ሞጋፈቻ” በሚባለው ባህላዊው የኦሮሞ ህዝብ ደንብ መሰረትም የጎሳው አባል ሆነች። የጎሳው መሪዎች ጉዳዩን ከራስ መኮንን ጋር በእርቅ እስኪጨርሱት ድረስም እዚያው መኖሩን መረጠች። ሽምግልናው ከመገባደዱ በፊት ምጥ ስለመጣባት አንድዬና ብቸኛ ልጇን እዚያው ተገላገለች። ራስ መኮንን በሚስታቸው ሁኔታ በእጅጉ ቢናደዱም ሽማግሌዎች ላቀረቡት ማግባቢያ እሺታቸውን ገለጹ። ሚስታቸውም ከኤጀርሳ ጎሮ ተመልሳ ወደ ቤታቸው እንድትገባ ፈቀዱላት። ህጻኑንም ልጅ እንደ ልጃቸው ተቀብለው ማሳደግ ጀመሩ። እያደር በልጁ ላይ በሚያዩት ለየት ያለ ብሩህነት እጅግ መመሰጥ ጀመሩ። በመሆኑም “ይህ ልጅ እኔን ይተካል” የሚል ትንቢት ተናገሩ። በዚህም የተነሳ ሀገሬው በሙሉ ልጁን በአትኩሮት ማየት ጀመረ። ***** ***** ***** ይህ በዝርዝር ያወጋኋችሁ ታሪክ በሰነድ አይታወቅም። ሆኖም “ተፈሪ የሙሐመድ ዓሊ ልጅ ነው” የሚለው አጽመ-ታሪክ ተፈሪ በህይወት እያለ እንኳ በሹክሹክታ ይነገር እንደነበር በርካታ ምንጮች ይጠቁማሉ። በጣሊያን ወረራ ዘመን ደግሞ አንድ ግለሰብ ተፈሪ የሙሐመድ ዓሊ ልጅ ነው የሚል ሐተታ በጋዜጣ ጽፎ ነበር። ይሁንና ሐተታው በዘመኑ ምሁራን ብዙም አልተዘመረለትም። ይብስ ብሎም በወቅቱ ለጣሊያኖች በባንዳነት አድረው “የቄሳር መንግሥት መልዕክተኛ” የተሰኘው ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ለመሆን ከበቁት ነጋድራስ አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ ከፍተኛ ተቃውሞ ነው የቀረበበት። ነጋድራስ አፈወርቅ “ወይ አብዶ ወይ ሰክሮ ካልሆነ በስተቀር ማን ነው ተፈሪ የመኮንን ልጅ መሆኑን የሚክደው?” በማለት ጸሐፊውን እንደዘለፉት የያኔውን ኩነት በቅርበት የታዘቡት አምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ “ቄሳርና አብዮት” በሚለው መጽሐፋቸው ገልጸዋል። እኔ የዚህ መጣጥፍ ጸሓፊም “ተፈሪ የራስ መኮንን ልጅ ናቸው” ከሚሉት ወገኖች ጋር እስማማለሁ፡፡ ህንዳዊው መሐመድ ዓሊ ጸጉሩ ሉጫ ከመሆኑ ውጪ ከተፈሪ ጋር የመልክ መመሳሰል የለውም፡፡ በሌላ በኩል ሙሐመድ ዓሊ የሀረር ነዋሪ የሆነው ልጅ ተፈሪ ከተወለደ ከዓመታት በኋላ ነው፡፡ ደግሞም የልጅ ተፈሪ እናት ወይዘሮ የሺእመቤት ዓሊ በጣም መልከ መልካም እንደነበረችና ተፈሪም እርሷን እንደሚመስል ሶስት የሀረሪ ሽማግሌዎች አጫውተውኛል፡፡ ሌሎች ምንጮችም ይህንን ይመሰክራሉ። ስለዚህ ራስ ተፈሪ በሰራቸው በርካታ ጥፋቶች ባልወደውም የራስ መኮንን ልጅ በመሆኑ ላይ ጥርጣሬ የለኝም፡፡ -------- ተፈሪ መኮንን መጀመሪያ ላይ ለጋብቻ ያጫት ሴት “አስቴር” የምትባል የእቴጌ ጣይቱ ዘመድ ነበረች፡፡ ነገር ግን አቤቶ እያሱ (ልጅ እያሱ) ስልጣን ሲይዝ ልጅ ተፈሪ በብርቱ ሊቀናቀነው እንደሚችል ገመተ። በመሆኑም በዲፕሎማሲያዊ ጋብቻ ሊሸብበው ወሰነ። በዚህም መሰረት ተፈሪ “አስቴር”ን ትቶ የእህቱ (የወይዘሮ ስሒን ሚካኤል) ልጅ የነበረችውን መነን አስፋውን እንዲያገባ ጠየቀው፡፡ ተፈሪም ጋብቻውን ተቀበለ። ይህ በሚወሰንበት ወቅት ወይዘሮ መነን ራስ ልዑል ሰገድ ከሚባል ባላባት ጋር በሞቀ ትዳር ላይ ነበረች። ብዙ ልጆችም ነበራት። የጋብቻው ዕለት ሲደርስ ወይዘሮ መነንን ለመውሰድ አራት ሺህ የደጃ/ች ተፈሪ አጃቢ ከሀረር ወደ አዲስ አበባ ተልኮ ነበር። ታዲያ የተፈሪ አጃቢዎች አዲስ አበባ ደርሰው ወ/ሮ መነንን ከትዳራቸው እስኪነጥሉ ድረስ እርሷም ሆነች ባለቤቷ ራስ ልዑል ሰገድ በተፈሪና በእያሱ መካከል ስለተደረገው ስምምነት አንድም መረጃ ያልነበራቸው መሆኑ ነው። ------- አፈንዲ ሙተቂ ሰኔ 11/2005 ዓ.ል. ተጻፈ። ሀረር- ምስራቅ ኢትዮጵያ

Afendi Muteki
Afendi Muteki
Open In TikTok:
Region: ET
Tuesday 30 September 2025 17:15:10 GMT
18169
466
20
35

Music

Download

Comments

bossfendisha
bossfendisha :
የራስ ልዑልሰገድና የእቴጌ መነን ልጆች አምቦ ቤተመንግስት እንዳደጉና የጠቅላይ ሚንስትር የታምራት ላይኔ እናት ወ/ሮ ሳህሊቱ መላኩ ባለሟላቸው እንደነበሩ ሰምቻለሁ
2025-10-04 17:09:01
2
shaka.zulu33
Shaka zulu :
what kifu things has he ever done
2025-11-05 13:38:47
0
miftahhajiburai
Miftah Haji :
good to read this
2025-10-01 11:19:24
2
user9067261210672
Temesgen Degu :
waan gaariifi jaalali afaan keetii yoom ba,a? guddaa xiqqeesun kuun yoomuma sii dhisa?gad antumaan dhibedha bakkii ittii yaalaman hin jiru haga barcaan bakka teessuti siin demuut
2025-11-22 06:25:27
0
bruh57703
BIRUH ABERA :
gobez sew!!!!
2025-10-02 10:51:44
0
tesfuashenafi7
tesfuashenafi7 :
ትንሽ አይቀፍህም አንተ እያልክ ስታወራ???
2025-09-30 20:05:39
4
bekan.ab3
Bekan Abdulwasi :
🥰🥰
2025-10-04 09:43:55
0
nejuvera
nejuvera :
👍👍👍
2025-09-30 17:49:18
0
user32148655698000
user32148655698000 :
ትንሽ ነውርን ብናውቅ መልካም ነው። የልጅነት (ከ13 ዓመታቸው ጀምሮ በሞግዚትም ቢሆን) ኢትዮጵያን ከ40 ዓመት በላይ ያስተዳደሩ የመሩ የገዙ ወደድንም ጠላንም ትልቅ ባለታሪክ የነበሩትን ከፍ ዝቅ አድርጎ በአንተነት ማቅረቡ የተጠቀሰው" አፈታሪ" እውነትነት ቢናኖረው እንኳንም ተገቢ አይደለም! ከዚያም በላይ አገር የማቅናት የተበታተነን አስተዳደር ወደአንድነት አምጥቶ በአንድ አገራዊ ስም ሥር ማሰባሰብ፣ማጠቃለል የዚያን ዘመን ታሪካዊ እነታ ነበር።(አንዱን ቢያስደስትም ሌላውን ቢያስከፋም)።ሌላው የአፈታሪኩ መሠረተቢስነት ከመነሻው የአንድ ኢትዮጵያዊ ታላቅ የጦር መሪ ሚስትን ምንነቱና ማንነቱ ከልታወቀ ሰው ውቅያኖስን አሻግሮ አምጥቶ ማጣመርና ከሕንዳዊ ፀነሰች አረገዘች ወለደች ብሎ መተረክ ማውራት እጅግ ፀያፍ ነው። ምነው አቶ አፈንዲ ከጦር አዛዡ ከአንዱ የቤት አሽከራቸው ወይም ከአንድ ወታደራቸው ወይም ከአካባቢው የኦሮሞ ማህበረሰብ ሠርጎ የገባ መልከ መልካም ጎረምሳ አረገዘች ወለደች ወዘተ ቢባል እኮ ትንሽም ቢሆን ውሃ ያነሳ ነበር። አልፎ አልፎም ቢሆን (ሲያጋጥመኝ) መጣጥፎችህን አነብልሀለሁ፤ ደግሞስ አሁን በዚህ ጊዜ ኃይለ ሥላሴ ከማን ተወለዱ እንዴት ተወለዱ ብሎ ማውራቱ ለማን ሊጠቅም ወይ ሊጎዳ?።እርሳቸው እንደሁ 44 ዓመታትን ቀጭ አድርገው አልፈዋል።......... ጤና ይስጥልኝ!
2025-10-01 19:20:01
5
kemalhassenaman7
Kemal Hassen Aman :
በነገራችን ላይ ራስ መኮንን ወደ ሐረርጌ ባቀኑበት ወቅት ሐረርን ማዕከል ከማድረጋቸው ቀደም ሲል የመጀመሪያ ዋና መቀመጫቸው ኤጀርሳ ጎሮ ሆኖ ወደ ምሥራቅ በዳሪሙና ግሪ ቆጨር የነበረውን አምስት የፊታውራራ ማዘዣ ጣቢያዎችን ይመሩ የነበሩት ከኤጀርሳ ጎሮ ነበር ።በነገራችን ላይ ሐረር ኤጀርሳ ጎሮ የአውቶቡስ ትራንስፖርት ማመላለሻ ካምፓኒ የነበራት ትልቅ ከተማ ነበረች ኤጀርሳ ጎሮ/የዛሬን አይበለውና/።ራስ መኮንን ከስድስቱ የጃርሶ ጎሳ መካከል ከ"ወላቡ" ጎሳ ጋር ሰጥቆ ነበራቸው ለዚህ ትልቁ ማስረጃ የኢቱ ጎሳ በሚበዛበት በዛሬው የምዕራብ ሐረርጌ ዋና ከተማ ላይ በአፄ ኃይለሥላሴ በደሚናነት ሹመት የተሰጣቸውን የወላቡ ጎሳ ተወላጅ የሆኑትን አመድ አሊ ጠሴን እንደማስረጃ መውሰድ ይቻላል።
2025-09-30 17:43:50
5
user5202781579008
user5202781579008 :
ተስፋዬ ገ/አብ ደሞ ተፈሪ መኮንን ከወ/ሮ የሺመቤት አሊ ተወለደ የተባለው ውሸት ነው / የሺመቤት የሚሏት የኦሮሞ ጎሳ ተወላጇን ለግዜው ስሟን ዘነጋሁት ከሷ ነው ይላል በተጨማሪም የተፈሪ ውልደት በጣም ተአምራዊ ነበረ እናቱ ሾተላይ ስለነበረባት በተደጋጋሚ ወልዳ ሞቶባት በመጨረሻ ነው እሱን የወለደችው ወልዳ ሳትታቀፈው ነው ወደ ሌላ ቦታ ተወስዶ ያደገው ወዘተ ,,, የሚልታሪክም አንብቢያለው ይሄስ ?
2025-09-30 19:08:57
1
blacksheepzi.ta
zi ta :
የምርቃና ወሬ ቸክቻኪ
2025-11-13 05:19:43
1
ms24874
ms :
ቅዱስ መፅሓፋችን እንደሚለው 'የሰው ልጅ ለሚናገረው ከንቱ ነገር በፍርድ ቀን መልስ ይሰጥበታል' ሰው ሆይ አንተ ማን ነህ በሌላው የምትፈርድ, እግዚአብሔርን እንፍራ
2025-10-01 06:35:42
2
ahmu5850
BIN IMAM :
ስለ አፄ ሀይለ ስላሴ እናት የ አብዱል ጀሊል ን ንግግር በደንብ አዳምጡት You will gain the Fact 😎😎😎
2025-09-30 21:36:38
0
mohammed.kema.l29
Mohammed kemal129 :
ለይክ
2025-11-30 19:33:30
0
To see more videos from user @afendi1978, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About