@musictube369: "ጉድ ፈላ"🤌🥹 ✨ከዚህ በፊት ይሄንን ነገር ብዬዋለው የጂጂ የ1993ቱ "ጉድ ፈላ" አልበም ቅርስ ነው እንደ ሙዚቃ አይደለም መደመጥ ያለበት እንደ መፅሀፍ ነው መነበብ ያለበት በሬድዮ አይደለም መደመጥ ያለበት በሙዚየም ነው መጎብኘት ያለበት በሙዚቀኞች አይለም መተንተን በምሁራን ነው መከተብ ያለበት ግጥሞቿ የታሪክ ድርሳናትን ይመስላሉ ደሞም የፈላስፎችን ሀሳብ ኢትዮጵያን ይመስላሉ ደሞም ዓለምን የሚመስሉ አለማዊ ይመስላሉ ደግሞም ፍፁም ባህታዊ ውድ ቤተሰቦቼ ስለ ጂጂ መናገር ይከብዳል ሁሉንም ሰው የምታስማማ ዕንቁ ነች በኢትዮጵያ ሙዚቃ እንደተወርዋሪ ኮከብ በዘመናት አንዴ የተፈጠረች አታወዳድሯት ነገር እሷን መሳይ የሌላት ርቃ የተሰቀለኝ ኮከብ ነች🥰🙌 ታዲያ ለዛሬ ከዚህ ቅርስ ከሆነ አልበሟ ላይ "ጉድ ፈላ"ን የአልበሙ መጠሪያ የሆነውን ሙዚቃዋን ጋብዣቹ ጥቂት እሷን ደሞ እንድናወሳት እንድናመሰግናት ወደድኩኝ☺️ የህይወት፣ የሙያ ጉዞዋ፣ ዝናዋ፣ የስራዎቿ ተደራሽነት ከተወለደችበት ትንሽዬ የገጠር ከተማ ተነስቶ እስከ አሜሪካ ድረስ ይዘረጋል፤ ብሎም መላ ዓለምን ያካልላል፤ ዘፈኖቿ በተለይም ግጥምና ዜማዎቿ ፍጹም ኢትዮጲያዊ ናቸው፡፡ ሙዚቃዋ ግን ዓለማቀፋዊ! ወቅቱ ሙዚቃን በሙሉ ባንድ መስራት እየከሰመ በአንድ ጠባብ ክፍል ውስጥ በኦርጋን ብቻ ማቀናበር የተጠናከረበት 1980ዎቹ መጨረሻ፤ 1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ ነው፡፡ አንዲት ድምጻዊም በኢትዮጲያ የሙዚቃ ሰማይ ላይ እንደ ፀሃይ ልትደምቅ ‹‹ፀሐይ›› የተሰኘ አልበሟን በ1989 ዓ/ም ይዛ ብቅ አለች፡፡ የእጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የመጀመርያ ስራ የሆነው፤ ፀሐይ አልበም እንደልፋቷና ድካሟ አልተደመጠላትም ነበር፡፡ እንደ ማለዳ ጸሃይ የአልበሟ ጨረሩ ብቻ ነው የታየው፡፡ ቀስ በቀስ፣ ቀን ቀናትን ሲወልድ ግን መድመቁ አልቀረም፡፡ ይህን አልበሟን ለመስራት ብዙ መስዋትእነት እና ድካምን ከፍላበታለች፡፡ የራሷን ግጥም ጽፋ ዜማ ደርሳ፣ እሯሷን ሆና በመምጧቷ ፣ደፍሮ ሊያሳትምላት የሚችል ሰው አላገኘችም ነበር፡፡ ሁኔታውን ለ“ኢትዮጵ” መጽሄት በ1994 ዓ.ም የጥር ወር እትም ስትገልጽ እንዲህ ብላ ነበር፦ ‹‹ምን ያልገጠመኝ ነገር አለ ብለህ ነው፤ ያልረገጥኩት የሙዚቃ ደጃፍ የለም፡፡ ኦኦ ይቅር ይቅር፡፡ ሁሉንም ነገር ልዝለለው እና ወደ መጨረሻው ልምጣ፡፡ ከለማ ድማሙ ጋር ተገናኘን፡፡ ለማ ኦርጋኒስት ነው፡፡ ከርሱ ጋር በመሆን ነው አልበሜን የሰራሁት፡፡ አሬንጅመንቱ የሱ ነው፡፡ ኦ እንዴት ለፍቷል መሰለህ፡፡ በዚህ ስራ ላይ ከኔ በላይ የደከመው ለማ ነው በጣም ባለውለታዬ ነው፡፡ አልበሙን ለመስራት ከአንድ አመት በላይ ወስዷል፡፡ ቀን ብቻ እንዳይመስልህ ሌሊቱንም ጭምር እንቅልፍ አልነበረም፡፡ ትዕግስት፣ እውቀት፣ ችሎታና ጉልበት ይህን ሁሉ በገፍ የጠየቀ ስራ ነው፡፡›› ጂጂ የተወለደችው በቀድሞ አጠራሩ ጎጃም አገው ምድር አውራጃ በቻግኒ - ሰጋዲ ሚካኤል የገጠር ቀበሌ ነው፡፡ ገና በልጅነቷ በእናቷ አሰልጣኝነት ከእህቶቿና ከጎረቤት ልጆች ጋር በመሆን ቴያትር እየሰሩ ያቀርቡ ነበር፡፡ 🤍በ16 ዓመቷ አዲስ አበባ መጣች፡፡ ሴንት ሜሪ ትምህርት ቤት ገባች፡፡ የጂጂ ነፍስ ሙዚቃ በሚሉት ወጥመድ ተይዞ ስለነበር ትምህርቱን ችላ አለችው፡፡ ቀሪ ስታበዛ፤ ተባረረች፡፡ የማታ ትምህርት ቀጠለች፡፡ ትንሽ ቆይቶ ግን የሙዚቃ ልክፍቷ አገርሽቶ ወደ ኬንያ ተሰደደች፡፡ ለቤተሰቦቿ ሳትናገር - በድብቅ፡፡ ኬንያ ከጉዞው ጀምሮ አስቸጋሪ- ኑሮውም ከባድ ቢሆንም በስተመጨረሻ “ባቲ” የተሰኘ ባንድ እስከ ማቋቋም ደረሰች፡፡ እጅጋየሁ፤ ለኢትዮጵ መጽሄት ስለዚሁ ባንድ ስትናገር ‹‹ባቲ ነበር የባንዱ ስም፡፡ አንድ ዛየራዊ፣ታንዛኒዊ እና ሌሎችም ኢትዮጵያዊያን ነበሩበት፡፡ ቦውሊንግ ግሪን የሚባል ሆቴል ውስጥ መስራት ጀመርን፡፡ ይገርምሃል የምናቀርበው ሙዚቃ ሁሉ ተወዳጅ እየሆነ መጣ፡፡ ነገር ግን የኛን ስራ በቅንነት ለማየት የተቸገሩ ሰዎች ተፈጠሩ፡፡ ባንዱን የሰራሁት እኔ ነኝ፡፡ የራሴ ባንድ ነው፡፡ እነርሱ ግን የፖለቲካ መጠቀሚያ ሊያደርጉት ፈለጉ፡፡ እኛ ደግሞ አላማችን ሙዚቃ ነው፡፡ እና ሌላ ነገር ውስጥ መግባት አልፈለኩም፡፡ ስለዚህ ባንዱ ቆመ፡፡ ተበተነ፡፡›› ጂጂ በኬንያ ቆይታዋ ትምህርትም ጀምራ ነበር፡፡ በድጋሚ ግን አቆመችው፡፡ የሙዚቃ ፍቅሯ ሌላ ነገር እንድትሰራ ፈጽሞ ፋታ አይሰጣት፣ አያላውሳትም ነበር፡፡ ካሴት ልትሰራ ግጥምና ዜማ አዘጋጅታ ለአቀናባሪ ከፈለች፡፡ አቀናባሪው ግን ገንዘቧን በልቶ ጠፋ፡፡ ይሄኔ ነው ወደ ሃገሯ ተመልሳ የመጀመሪያ ካሴቷ “ፀሐይ” የወጣው😍፡፡ ☺️እጅጋየሁ ሽባባው፤ ወደ አሜሪካ የተጓዘችው አልበሟ ከመከፋፈሉ አስቀድሞ ነበር፡፡ በአሜሪካ ቆይታዋም፤ “አንድ ኢትዮጲያ”፣ “ጂጂ (ጉራማይሌ)”፣ “አቢሲኒያን ኢንፋናይት”፣ “ሰምና ወርቅ” የተሰኙትን አልበሞቿን አወጣች፡፡ በአጠቃላይ 7 ያህል አልበሞችን ለህዝብ አድርሳለች፡፡ እንደ ሲኤን ኤን(CNN) የመሰሉ ታላላቅ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች፤ ስለ ጂጂ ዘግበዋል፣ “አፍሮ ፖፕ ወርልድ”፣ “ሪትም” የመሰሉ መጽሄቶች ስለ እሷ ጽፈዋል፡፡ የጂጂ ሙዚቃ በዓለም ላይ ለመደመጡ ቅንብሩና ቀረጻው ደረጃውን የጠበቀ መሆኑ፤በተለይም የቀድሞው ባለቤቷ እውቁ ሙዚቀኛ፤ የቢል ላስዌል ሚና ቀላል እንዳልነበር ይነገራል፡፡ ሌሎች፤ ጂጂን ወደው የሚያደምጧት የሚያደንቋት በድምጽ ውበት፣ በሙዚቃው የዜማ ጣእም ነው፡፡ የግጥሞቿን ትርጉም ለሚረዱት ደግሞ እንዴት ትንግርት የሆነች ድምጻዊ ለመሆኗ ከዘፈኖቿ አንዱን ብቻ በማድመጥ መረዳት ይቻላል፡፡ ጂጂ ግጥሞች ሃገርን፣ ናፍቆትን፣ ፍቅርን፣ አንድነትን፣ ታሪክን ሲገልጹ፤ መነሻዋ እድገቷ ነው፡፡ የኖረችበትን ባህል እና ትውፊት! ያየችውን፣ የኖረችውን መከተቧ፡፡ ብዙ ሰው ልብ ያላለውን ጉዳይ እሷ ትኩለዋለች፡፡ ነፍስ ትዘራበታለች፡፡ ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ባበረከተችው ደማቅ አስተዋጽኦ ታሪክ ሲነሳት ይኖራል ጂጂ ሙዚቃን ኖራት እኛንም በፍቅር ስባ ወስዳናለች በኛ ዘመን ሆና እሷን መስማት እራሱ አድለኛነት ጂጂያችን🥰 ፈጣሪ ዕድሜ እና ጤና ጨምሮ የስጥሽ ባለሽበት ሰላም ሁኚልን☺️ እጅግ ተወዳጆቹን ዘመን አይሽሬ ሙዚቃዎችሽን ስላደረሽን እናመሰግናለን እንወድሻለን ክበሪልን🙏🙏 ታዲያ እኔም ለዛሬ እዚህ ጋር ላብቃ ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡🙌 @musictube 🇪🇹 #fyp #ጂጂ #ጉድፈላ #ethiopianmusic #musictube369

🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
Open In TikTok:
Region: ET
Tuesday 30 September 2025 21:18:08 GMT
37407
2838
41
166

Music

Download

Comments

tizitanegash
Luuna🌙✨ :
ባለቅኔዋ ቀለማችን ነች ጂጂዬ❤❤❤
2025-10-01 21:32:10
1
tewodros183
Tewodros183tedy!!!! :
እናመሰግናለን 1993=የ2ተኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ😂🤔👍🙏!
2025-10-01 03:59:24
4
ashutohbiuse
ashutho bluse and jazz :
እስቲ የዚህን ሙዚቃ አልበም ሙዚቃ አቀናባሪዎች በደንብ ንገረን.
2025-10-01 11:45:16
2
mela11734
መla :
follow ged new 🥰🥰🥰
2025-10-01 10:33:56
4
alimohammed39009
👑Ãlĩ Shãýé👑 :
ድምጿ ከአየሩ ጋር እኩል ነው ሚነፈሰው🥰
2025-10-01 07:08:53
6
remember2114
𝓱𝓪𝓶𝓲😍 :
Master piece 😊
2025-10-01 21:57:20
1
leouzersiv
leouzersiv :
overated musician
2025-10-01 09:26:21
1
fani_830
fani 🔵 :
እንደሷ አንድ ሰው ይጥፋ ልብ የሚሰርቅ
2025-10-01 06:43:16
3
selam.niguesa1
selamnigusa :
jijia
2025-10-01 14:30:21
2
mdameen315
M/dAmeen :
Gooooood
2025-10-01 07:00:45
1
wondesen.tadese5
wondesen Tadese :
ንግስትዋ🥰🥰🥰🥰
2025-10-01 09:19:55
1
anwarabdu806
anwarabdu806 :
ተው ይሉኛል ወዳጅ ዘመዶቼ ክረምት ለሙቀት እና ለእረፍት ከምትመጣ ልጅ ይሉኛል።እኔም ልብ የለኝም እና ስትመጣ እስዋም ከእኔ እኔም ከስዋ አንለያይም ነገርግን ክረምቱ አልቆ መስከረም ሲመጣ ሀዘን ብቻ
2025-10-01 14:01:00
1
dawamarley
@Dawa Marley :
ሙዚቃን እሷ ትሞዝቃት 👸👸👸
2025-09-30 21:34:40
5
its.kall20
its kall :
Princess👸GIGI 🥰🥰
2025-09-30 23:01:40
2
godayms1
Fasika :
ንጉስቷ ክፉ አይንካሽ
2025-10-01 15:39:04
0
muller.175
John 17 :
it's dereje's arrangement
2025-10-01 14:30:06
0
constable.shambel
constable shambel :
የኔ ነፍስ ጂጂጂጂጂጂጂጂጂጂጂጂጂዬ
2025-10-01 07:52:29
1
amare.shitahun59
Amare Shitahun :
wow 👌 jij
2025-10-01 14:04:43
0
liyateshome2
Liya 📖 :
My favorite ever 👌❤
2025-10-01 16:23:03
0
tutu6184
Tutu :
የተዉኩትን ነገር ተመክሬ
2025-10-01 15:19:42
0
senaf1
Senaf 😍 :
💗💗💗💗💗
2025-10-01 08:58:42
1
tegish7
Tsga Tsga :
🥰🥰🥰🥰🥰
2025-10-01 05:34:52
1
ms937312
ms olds :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2025-10-01 01:36:07
1
ermiyas_t
Ermiyas_t :
👍👍👍
2025-09-30 21:43:21
1
lidiyamelese
Lidiya 👸 :
❤
2025-10-01 22:27:38
0
To see more videos from user @musictube369, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About