@teshet4all: #creatorsearchinsights #creed ሁሉ በሚችል ሰማይንና ምድርን፣ የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ አንድ አምላክ በሚሆን በእግዚአብሔር አብ አምናለሁ። እርሱ ብቻ የአብ ልድ በሚሆን፣ ዓለም ሳይፈጠር ከአብ በተወለደ፣ ከአምላክ በተገኘ አምላክ፣ ከብርሃን በተገኘ ብርሃን፣ ከእውነተኛ አምላክ በተገኘ እውነተኛ አምላክ፣ በሕልውና ከአብ ጋር አንድ በሆነ፣ በተፈጠረ ሳይሆን በተወለደ፣ ሁሉ በእርሱ በሆነ፣ ስለ እኛ ስለ ሰዎች ስለ ድኅንነታችንም ከሰማይ በወረደ፣ በመንፈስ ቅዱስ ከድንግል ማርያም ሥጋ ነሥቶ ሰው በሆነ፣ በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመንም ስለ እኛ በተሰቀለ፣ መከራ በተቀበለ፣ በሞተ፣ በተቀበረም፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም እንደ ተጻፈ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ በተነሣ፣ ወደ ሰማይም በወጣ፣ በአብ ቀኝ በተቀመጠ፣ በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ዳግመኛ በክብር በሚመጣ፣ ለመንግሥትም ፍጻሜ በሌለው በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ። ከአብና ከወልድ ጋር በሚሰገድለትና በሚከበር፣ ከአብና ከወልድ በሚሠርጽ፣ በነቢያት በተናገረ፣ የሕይወት ጌታና ሰጪ በሆነ፣ በመንፈስ ቅዱስም አምናለሁ። የሁሉም በሆነች በአንዲት ቅድስት የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያንም አምናለሁ። ለኃጢአት ማስተሰረያ በአንዲት ጥምቀትም አምናለሁ። የሙታንንም ትንሳኤና ገና የሚመጣውን ዓለም ሕይወትም እጠባበቃለሁ። አሜን!!
Teshe Ewnetlehulu
Region: ET
Wednesday 08 October 2025 09:54:40 GMT
Music
Download
Comments
Daba Ejeta :
እኔም አምናለሁ🙏
2025-10-17 16:56:42
1
ኤዶንያስ እግዚአብሔር አምላክ ነው hifdv68 :
በተቀበረ የሚለውን ዘለህዋል
2025-12-21 20:39:24
0
sema mare :
አሜንንንንንንን❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
2026-03-05 15:51:08
0
Tsinu :
99999999999999999999999999999
2026-04-10 14:31:05
0
Anjon :
Amen🥰🥰
2025-10-08 12:50:41
0
meluka :
Amen aminalehu🙌
2025-10-09 10:18:00
0
Goaner duoth chuol :
🥰🥰🥰
2025-10-11 15:43:34
0
Mihret Alemu :
👍👍👍👍
2025-10-09 13:25:39
0
meluka :
❤❤❤
2025-10-09 10:17:34
0
zeko asefa :
🥰🥰🥰
2025-10-09 09:48:33
0
Mekdes Mekuria :
❤❤❤
2025-10-08 14:04:17
0
yared mekuria :
🥰🥰🥰
2025-10-08 12:04:24
0
user2127 Tayech Getu :
🙏
2026-07-17 10:51:37
0
To see more videos from user @teshet4all, please go to the Tikwm
homepage.