@_meqi23: አሁን ቆይ ከሴት ጋ ተጋድሜ ዲቁናዬን አፈረስኩ ነው ምላቸው?ይስ ከዚ በኋላ መቀደስ አቁሜያለሁ?? ባልናገርስ???ዝም ብዬ ብቀድስስ ማን ያውቃል?? ከራሴ ጋር እየተሟገትኩ ነበር አሳዳጊዬ የኔታዬ ወደሆኑት አባ ስብሐት ቤት የደረስኩት፡፡አስተዳደጌን ያውቃሉ፡፡ተምረህ ካህን ትሆናለህ እያሉም ይተማመኑብኝ ነበረ፡፡ እኔ ነኝ እንጂ ክብሬን ለአንዲት ሴት በፍቅር ሰበብ አስረክቤ እየተደባበቅኩ የምኖር....እኔ ነኝ እንጂ ቅዳሴ ሰአት ሲደርስ ቀድስ እንዳልባል የምሰወር... እኔ ነኝ እንጂ.... ምን ሆነካል ካሌብ ንገረኝ እንጂ(በሀሳብ ናውዤ በተቀመጥኩበት የአባ ድምፅ አባነነኝ አይ እንደው አባቴ ይቅር በሉኝ...ከእግዜርም ከእርሶም ሀሳብ አፈንግጫለሁ እኮ ምን አድርገህ??በል እንጂ ንገረኝ...ሀጥያት ደሞ ከካህን ይደበቃል እንዴ?? አባ ክህነቴን አፍርሻለሁ!!ከሴት ጋ ተኝቻለሁ!! በወጣትነት ፈተና ወድቄያለሁ!! ይቅር በሉኝ አባቴ...(አንገቴን አቀርቅሬ በሀፍረት እነተንተባተብኩ ውይ ለሱ ነው እንዴ ታድያ ምን ችግር አለው(ወደጎን ገልመጥ አድርገውኝ የግርምት ሳቅ እየሳቁ አባ ዲቁናዬን አፈረስኩ ከሴት ጋ ተኛሁኝ እኮ ነው ያልኩት እናሳ....በቃ አንዴ ሁኗል ሚስጥሩ በኔና ባንተ ይሁንና መቀደስም ከሆነ ትቀድሳለህ አረ በስመአብ!!!አባ እንዴት አፍርሼ ከሴት ተኝቼ ቀድሳለሁ??በቃ ከእንግዲህማ.. ኤድያ አትፍራ ስልህ!!??ባንተ አልተጀመረ!!ሁሉስ ይበድል የለ??እንዲያውም ነገ በለሊት መጥተህ እንድትቀሽረው....አሁን ግባ እና ተዘጋጅ ...በል ሂድ አይዞህ ምሰማው ነገር ከአባ ስብሐት መሆኑ እራሱ ተአምር ሆኖብኝ አፍጥጬ አየኋቸው፡፡ለብዙ ካህናት ዲያቆናት አርአያ መማርያ ነበሩ ትሁት ነበሩ ውሸትን የሚጠየፉ ነበሩ።እኮ ታድያ ግሳፄያቸው ስንቱን መልሶ ዛሬ እንዴት እንዲ ይሉኛል??ምን ማለታቸው ነው??ሊያስቀፅፉኝ ነው?? (በውስጤ እያብሰለሰልኩ ቤተ ገብቼ ተኛሁ፡፡አባ እንዳትቀር ያሉኝ አስሬ እየመጣ ቢከነክነኝም ከጠሉኝም ይጥሉኝ ብዬ ቅዳሴውን ቀርቼ ጠዋት ምእመናን ሲወጡ እንደለመድኩት አቀርቅሬ ቤታቸው ሔድኩ አንተማ አልታዘዝ ብለካል...ለመሆኑ ለምን ቀረህ(በረንዳቸው ላይ አቀርቅረው እግራቸውን እየታጠቡ... በኮቴዬ ጭምር የሚያቁኝ ነገራቸው ይገርመኛል አልሆን አለኝ አባ...ፈራሁ...ረክሼ እንዴት ቤተ መቅደስ.. ችግር የለውም እኔ ሚስጥርክን ጠብቃለሁ አልኩኝ አደል እንዴ አባ እርሶማ ከሰው ነዋ...ከእግዜር ቁጣ ማን ያመልጣል እና አሁን አልቀድስም እያልክ ነው?? በፍፁም አባ...በፍፁም... አባ እግራቸውን ታጥበው ጨርሰው እንደተነሱ...ወደራሳቸው አቅርበው እያቀፉኝ)ጎሽ.. ጎሽ ...ጎሽ.. አሁን ገና መልካም ነገር አወራህ፡፡አየህ ትላንት መጥተህ ቀድስ ስልህ ልብህን ልፈትን ነበር፡፡አንተም አላሳፈርከኝም ቀረህ፡፡ልጅ ካሌብ... ሴትኮ እስካላገባካት ድረስ የካህን ፆም ናት፡፡አንድ ካህን ከተሾመ ወድያ ከሚስቱ ውጪ ቢደርስ ክህነቱን ያጣል አንተም የሠራከው ነገር በጎ አደለም፡፡እግዚአብሔር አምኖብህ መርጦ የሠጠክን ክህነት ለጊዜያዊ ስሜት ማጥፋትህ ከቶ ጥፋት ነው፡፡ግን ደሞ ሰው ንሰሀ ከመግባቱም በላይ በዚያ ሀጥያት ተመልሶ ላለመግባት መወሠኑ እራሱ ትልቅ ፅድቅ ነው፡፡እኔ በአገልግሎት ዘመኔ ብዙ ዲያቆናት በፍትወት ወድቀው ድንግልናቸውን አጥተው ህጉን ተላልፈው ሲቀድሱ አውቃለሁ፡፡ስለዚህ አንተ ዛሬ ለሊት የቀረከው "ከቅዳሴ ሳይሆን ከሀጥያት ነው"አንዳንዴ ፅድቅ የሚመስሉ መርገሞች በረከት የሚመስሉ መቅሰፍቶች አሉ ለሚዳፈሩቱ የሚባላ እሳት ለሚፈሩቱ ደሞ መማርያ መመለሻ ነው... እየውልህ...አንድ ዲያቆን ክህነቱን በአንድም በሌላ ሲያፈርስ ''ያፈረሰ ዲያቆን" ይባላል፡፡ነገር ግን ክህነቱን አፍርሶ በማን አለብኝነት የሚቀድስ ከሆነ"የፈረሰ ዲያቆን" ይባላል፡፡ልክ እንደዚሁም ምእመናን የተጣለባቸውን ግዴታ ሳይፈፅሙ፤ፆም ሲገድፉ፤ንሰሐ ሳይገቡ ሲቀሩ"የፈረሱ ምእመናን"ይባላሉ፡፡ምክንያቱም የድፍረት ሀጥያት ሰውነታችንን ሳይሆን ልጅነታችንን ክብራችንን ፅድቃችንን ማንነታችንን ሳይቀር ትነጥቀናለች፡፡ ልጅ ካሌብ "ንሰሐ መግባት ማለት ካለፈው ሀጥያት መቅረት ለወደፊት ስህተት ደሞ መፀፀት ማለት ነው"እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ንሰሐ ይገባል ፍፁም የሚወደው ሚታመንለት ከሆነ ደሞ ከለመደው ሀጥያት ይቀራል፡፡ዛሬ ብዙ ሰወች ካለፈው ሀጥያት መቅረት አቅቷቸው በሀጥያት ላይ ሀጥያት የሚደርቡት ልባቸው ፍፁም ለጌታ ስላላደላ ነው፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር መሀሪ ነው፡፡የመቅደሱ ቅዳሴ ቢቀር በትህትና ቅኔ ማህሌት ሰአታትና ማህሌት በመቆም፤ ቀዳሾችን ከውጪ በመራዳት አገልግል፡፡ህጉን አክብረሀልና እግዚአብሔር ከከፋ ሀጥያት ይጠብቅህ እንዳከበርከው ያስከብርህ ቀሪ ዘመንህን ባለህ ፀጋ ለማገልገል ብርታት ይሁንህ በል ተነስ ፀሎት ተቀበል(አባ መስቀላቸውን ከውጥ ኪሳቸው አውጥተው እያማተቡ ''ንሰሐ መግባት ማለት ካለፈው ሀጥያት መቅረት ለወደፊት ስህተት ደሞ መፀፀት ማለት ነው" #እግዚአብሔር_ብርሃኔና_መድኀኒቴ_ነው🙏 #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ፀንታ_ለዘለዓለም_ትኑር
መቅዲ☦️💒❤
Region: SA
Friday 10 October 2025 08:23:46 GMT
Music
Download
Comments
🇯🇲𝓪𝓫𝓮𝓵🗡⚔️ :
ዲያቆን ነበርኩኝ ከማለት እግዚአብሄር ይሰውረን😔
2025-10-11 06:17:57
892
kb :
የራሴን ታሪክ ማን የሚያውቀኝ ሠው ነው የፃፈው ብየ ባየው አላውቅህም ግን የኔ ታሪክ ነው ይሄ ንስሐ አባቴጋ ሄጀ ንስሐ ገብቸ ነስሐህን ጨርስና ቀድስ አሉኝ ንስሐየን ከጨረስኩ ቡኋላ ገብቶ መቀደስ ውስጤ አልፈቅድ አለኝ
2025-10-11 05:35:24
255
liul :
እስኪ እንደኔ ጠመስጦ ያነበበ ላይክ
2025-10-11 09:12:02
966
$$ura :
አረ ዉይይይይይ አሁንስ ዲያቆን መሆኔ እየጸጸተኝ ነዉ
ብዙ ፈተናወች ገጥመዉኛል ከነዛ ፈጣሪ ጠብቆኛል ።ወደፊትም ምን እንደምሆን አላዉቅም 😓😓😓 እሱ ይጠብቀን 🙏🙏🙏
2025-10-18 15:02:59
49
🦋Hanun༒ :
ንሰሀ ልገባ ነው አበረታቱኝ🥺🙏
2025-10-17 06:03:15
83
ግሩማን :
በዚህ ዘመን እንደ ዲያቆን የሚፈተን አለ ወይ
2025-10-12 09:17:14
108
𝕬𝖒𝖊𝖓 ☄️ :
ዲያቆን አፈረሰ የሚባለው ምን ምን ሲያደርግ ነው?
2025-10-14 16:47:46
6
Yuri :
ድኅረ ልቡናሁ ጼወወ ፍቅረ አሐቲ ብእሲት ለዘወፅአ ረድእ እምኃይማኖት
ዘመሐርክምዎ በዕሥራ እለት
መሐሩኒ ሥላሴ ነገሥት😔
2025-10-11 07:30:07
67
እመ አምላክ የኔ አማላጅ🙏🙏🙏💚💛❤ :
የኔን ታሪክ ነው ግልፅ አድርገህ የተነተንከው ግራ ግብት ብሎኛል😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
2025-10-13 04:13:28
16
ፓስተሩ meme 👽 :
በዚ ከቀጠልክ ገና አንተም ትፈርሳለክ😏
2025-10-11 20:58:08
0
Dawit Tesfaye :
ፈጣሪ ያክብርልኝ ተምርያለዉ ብዙ ነገር
2025-10-10 21:15:45
1
አልዬ :
😢😢😢😢ይህ ለሁላችንም ይሆናል ቃለ ህይወት ያሰማልን
2025-10-10 22:05:45
1
ዘገብርኤል ንጉሤ :
ግሩም ነው
2025-10-10 17:02:24
2
Nama :
ከኔ ህይወት ገር አንድ ነው
2025-10-10 14:05:11
3
✝️💟💒❤ :
ወንድሞቼ.እህቴች
እየገባችሁ ቪዲዮ ላይክ ኣረጉኝ 🙏🙏
2025-10-11 08:58:55
1
kal Art(የሴት ልጅ) :
ድንቅ አስተማሪ መልእክት ሳትሰለቹ አንብቡት ትማሩበታላችሀሁ🙏
2025-10-11 08:32:59
2
ስለ ሁሉምነገር እግዚአብሔር ይመስገን :
ቃለ ህይወት ያሰማልን አሜን በጣም አስተማሪ ታሪክ ነው እናመሰግናለን🙏🥰
2025-10-10 17:25:52
1
ሰዉ ሁን :
መልካም
2025-10-10 18:23:16
1
@ በእምነት ጽና በፍቅር ተመላለስ🫶♥️🌹🥀 :
በእውነቱ ቃለህይውት ቃለበረከት ያስማልን 🥰🥰🥰🥰
2025-10-10 14:20:50
1
dejen :
ግሩም ነው ልጂነቴን አስታወስከኝ ተባርክ
2025-10-10 17:08:17
0
Zad ነኝ የእመቤቴ ልጅ :
🥰❤️
2026-07-30 17:53:04
0
KB (አግናጢዎስ)🧑🏻🎤🇨🇦🇨🇦🇨🇦 :
kale hiywet yasemaln
2025-10-11 01:16:36
0
wonde man :
🥰🥰🥰
2025-10-10 09:09:17
2
ብርቴ የተዋሕዶ ልጅ⛪❤🙏 :
🙏🙏🥰🥰❤❤
2025-10-10 13:08:53
2
ዘማሪት✝️መቅደስ✝️ማርዩ✝️እግዚኦ ሰምዓኒ ጸሎት :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2025-10-10 09:31:42
2
To see more videos from user @_meqi23, please go to the Tikwm
homepage.