@kebadweku: ❤አባ ገሪማ (ይስሐቅ ) ማን ናቸዉ። ✍️ወር በገባ በ17 የአባ ገሪማ ዘመደራ ወርኀዊ መታሰቢያ በዓላቸው ነው:: ✍️አባ ገሪማ (ይስሐቅ) ዘመደራ አቡነ ገሪማ የተወለዱት በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ሮም ውስጥ ነው:: ✍️ ወላጆቻቸው መስፍንያኖስና ሰፍንግያ እግዚአብሔርን የሚወዱ የሮም ከተማ ንጉሥና ንግሥት ነበሩ:: ልጅ በማጣታቸው እመቤታችንን ለመኑ:: ✍️እመ ብርሃንም ደግ ፍሬ ሰጠቻቸው:: ስሙን ይስሐቅ ብለው አሳደጉት:: ገና በልጅነቱ አባቱ ድንገት በመሞቱ ይስሐቅ በዙፋኑ ተተክቶ ነገሠ:: ለ7 ዓመታት ሕዝቡን በፍትሕ እያስተዳደረ : መጻሕፍትንም እያጠና ኑሯል:: ✍️አንድ ቀን ግን ከግብፅ በርሃ የተላከ ደብዳቤ ደረሰው:: ላኪው አባ_ዸንጠሌዎን ሲሆኑ መልዕክቱ "ምድራዊ ንግሥና ምን ያደርግልሃል? ይልቁኑስ በሰማይ ለዘለዓለም እንድትነግሥ ወደ በርሃ ና" የሚል ነበር:: ✍️ንጉሥ ይስሐቅ አላመነታም ሌሊት ተነስቶ ወደ ፈጣሪው ጸልዮ በለበሳት ልብስ ብቻ ዙፋኑን ጥሎ መነነ:: ድንገት ግን ቅዱስ_ገብርኤል ደርሶ በቀኝ ክንፉ ነጥቆ ግብፅ አባ ዸንጠሌዎን በዓት ላይ አኖረው:: ✍️እርሳቸውም ተቀብለው ፍኖተ አበውን አስተምረው አመነኮሱትና ዘጠኝ ሁነው ወደ ኢትዮዽያ መጡ:: ተስዓቱ ቅዱሳን በሃገራችን ብዙ ሲሰሩ አንዱና ታላቁ አባ ይስሐቅ (ገሪማ) ናቸው:: ሰውነታቸውን በገድል ቀጥቅጠውት ቆዳና አጥንታቸው ተጣብቆ ነበር:: ✍️አንድ ቀን አባ ይስሐቅ በልቶ ቀደሰ ብለው ነግረዋቸው አባ ዸንጠሌዎን አዘኑ:: ልምከር ብለው "ልጄ ይስሐቅ የሰማውብህ ነገር አለና ሰዎችን አርቅልኝ" አሉ:: አባ ይስሐቅ ግን "ሰዎች ብቻ አይደሉም:: ዛፉም እንጨቱም ገለል ይበል" ቢሉ የቤተ ክርስቲያኑ አጸድ አንድ ምዕራፍ ተጠራርጎ ሸሸ:: ✍️ይሕንን የተመለከቱት አባ ዸንጠሌዎን "ወልድየ ይስሐቅ ገረምከኒ" (ልጄ ይስሐቅ ገረምከኝ) አሏቸው:: ከዚያ ጊዜ ጀምሮም "አቡነ_ገሪማ" ተብለው ቀሩ:: ✍️አቡነ ገሪማ ወደ መደራ ሲሔዱ እነዚያ የሸሹ ዛፍና ድንጋዮች "ገሪማ ለእኛም ግሩም ነህ" እያሉ በዝማሬ ተከትለዋቸዋል:: ይህም የተደረገው በዚህች ቀን (መስከረም 30) ነው:: ✍️ጻድቁ ወንጌልን : ገዳማትን ከማስፋፋት ባለፈ ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል:- 1ኛ.ስንዴ ጠዋት ዘርተውት በ9 ሰዓት ያፈራ ነበር:: ነግሃ ይዘርዕ ኪነቶ:: ወሠርከ የዓርር ገራኅቶ::" እንዲል:: 2ኛ ጧት የተከሉት ወይን በ9 ሰዓት ያፈራ ነበር:: 3ኛ አንድ ቀን ምራቃቸው ቢወድቅ ጸበል ሆኖ ዛሬም አለ:: 4ኛ.ብዕራቸው ወድቃ አብባ አፍርታለች:: 5ኛ.አንድ ቀን ድርሳን እያደረሱ (ወንጌለ ዮሐንስን ሲጽፉ) ሊመሽ በመሆኑ ፀሐይን አቁመዋታል:: ✍️ከእነዚህ ሁሉ ዘመናት በሁዋላ ጌታችን ተገልጦ በማይዋሽ ንጹሕ አንደበቱ ቃል ኪዳን ሰጣቸው:: "ስምሕን የጠራ : መታሰቢያህን ያደረገ : እስከ 12 ትውልድ እምርልሃለሁ:: አንተ ግን ሞትን አትቀምስም" ብሏቸው ተሰወረ:: ያን ጊዜ መላእክቱ በሠረገላ ጭነው እየዘመሩ ብሔረ_ሕያዋን አድርሰዋቸዋል:: ✍️ቸሩ አምላካችን ከታላቁ ቅዱስ ጸጋ በረከት ይክፈለን:: በምልጃቸውም ይቅር ይበለን:: ✍️ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ:: ግርማው በእሥራኤል ላይ : ኃይሉም በደመናት ላይ ነው:: ✍️እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው::የእሥራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን : ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል:: እግዚአብሔርም ይመስገን:: (መዝ. 67:34) @ወስብሓት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክብር ይ..!አሜን
kebad butik
Region: ET
Monday 27 October 2025 03:43:52 GMT
Music
Download
Comments
samson Tamaghe :
በረከታቸው ይደርብን
2025-10-27 03:54:26
0
To see more videos from user @kebadweku, please go to the Tikwm
homepage.